አርዕስተ ዜና

በክልሉ ጥራትን ታሳቢ ያደረገ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ ለማካሄድ ዝግጅት ተደርጓል

06 Jan 2017
978 times

ባህር ዳር ታህሳስ 28/2009 በአማራ ክልል በህብረተሰብ ተሳትፎ የሚካሄደው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ጥራትን፣ ዘላቂነትንና የህብረተሰብ ተጠቃሚነትን መሰረት ተደርጎ እንደሚከናወን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

ከጥር 1 ቀን 2009 ዓመተ ምህረት ጀምሮ የዚህ ዓመት የተፈጠሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ በይፋ እንደሚጀመር ተገልጿል።

የቢሮው ሃላፊ ዶክተር ተሾመ ዋለ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጠት መግለጫ በክልሉ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ የህልውና ጉዳይ ሆኖ እየተከናወነ ይገኛል።

ባለፉት ዓመታት በተከናወነው የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራም በተለያዩ የሰብል አይነቶች ከ21 በመቶ እስከ 88 በመቶ ምርታማነትን ማሳደግ እንደተቻለ ገልፀዋል።

እንዲሁም የአፈር መከላትን ከ75 በመቶ እስከ 90 በመቶ ማስቀረት እንደተቻለ በጥናት መረጋገጡን ጠቁመዋል።

ቀደም ሲል የተገኘውን የአሰራር ልምድና የህዝቡን የተነቃቃ የስራ ባህል ግለቱን ጠብቆ በማስቀጠል ከመጭው ጥር 1 ቀን 2009 ዓመተ ምህረት ጀምሮ 6 ሺህ ተፋሰሶች መሰረት በማድረግ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር በሚሸፍን መሬት ላይ ልማቱን ለማካሄድ ዝግጅት መጠናቀቁን አመላክተዋል ።

በዝግጅቱ ስራውን ለሚመሩ ከ5 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ባለሙያዎችና ለ76 ሺህ ግንባር ቀደም አርሶ አደሮች በመሬት ልኬትና ቅየሳ ፣በእርከን ፣ ክትርና ውሀ ማስረጊያ ጥራት ቁጥጥር ላይ ያተኮረ በተግባር የተደገፈ  ስልጠና መሰጠቱንም ገልፀዋል ።

ለልማት ስራው ማካሄጃ የሚያገለግሉ 2 ነጠብ 6 ሚሊዮን በላይ አነስተኛ የእርሻ መሳሪያዎች ተሰብስበው መዘጋጀታቸውን ጠቅሰዋል ።

በአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራው 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን አርሶ አደሮች እንደሚሳተፉ ተናግረዋል 

የተደረገው ዝግጅት  የሚከናወነው የአፈርነው ውሃ ጥበቃ ስራ ከዚህ ቀደሙ በተሻለ ጥራትን፣ ዘላቂነትንና የህብረተሰብ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጥ መንገድ እንዲከናወን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል ።

የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራው እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ የሚለያይ ቢሆንም የጉልበት ብክነትን በመቀነስ ለመነሻነት ከ20 ቀናት ላላነሰ ጊዜ እንደሚቆይ ዶክተር ተሾመ አመላክተዋል።

በክልሉ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በተከናወነው የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ የደን ሽፋኑን ከ7 በመቶ ወደ 14 በመቶ ማደጉን ታውቅል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ