አርዕስተ ዜና

የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ነዋሪዎች ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ለህዳሴ ግድብ ድጋፍ አደረጉ

388 times

መቀሌ የካቲት 6/2010 የትግራይ ምዕራባዊ ዞን ነዋሪዎች የታላቁ ህዳሴ ግድብ ችቦ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች መዘዋወሩን ተከትሎ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።

የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ የሺ ታረቀኝ እንደገለጹት  ነዋሪዎቹ ለግድቡ ግንባታ የሚሆነውን ድጋፍ በቦንድ ግዢና በስጦታ ያበረከቱት ችቦው በዞኑ በተዘዋወረባቸው አራት ቀናት ውስጥ ነው።

በዞኑ በዚህ ዓመት 10 ሚልዮን ብር በቦንድ ፤በስጦታና ብድጋፍ መልክ እንደሚሰበሰብ ህብረተሰቡ ቃል መግባቱን ያስታወሱት ኃላፊዋ ችቦው በዞኑ በተዘዋወረባቸው በነዚህ ቀናት ውስት አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ገልጸዋል።

በዞኑ የሰቲት ሑመራ ነዋሪ አቶ ሚኪኤለ ንጉሰ ለህዳሴው ግድብ ግንባታ የሚውል ለሶስተኛ ጊዜ ቦንድ መግዛታቸውንና ግንባታው እስከሚያልቅ ድረስም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

በሦስቱም ዙሮች 10 ሺህ ብር ድጋፍ ማረጋቸውን ገልጸው አሁንም አንድ ሺህ ብር በስጦታና የወር ደመወዛቸውን በቦንድ ግዢ እንደሚያበረክቱ ገልጸዋል።

በንግድ ስራ የተሰማሩት ወይዘሮ ሰሚራ አልሃጂ በበኩላቸው፣በየዓመቱ የአንድ ሺህ ብር ቦንድ  በመግዛት ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

አሁንም እስከ የግድቡ ግንባታ መጠናቀቁ እስከሚረጋገጥ ድረስ በየዓመቱ የአንድ ሺህ ብር ድጋፍ እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።

በትግራይ በዚሁ ዓመት ከህብረተሰቡ፤ከነጋዴዎች፣ከባለሃብቶችና ከመንግስት ሰራተኞች ከ83 ሚልዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የክልሉ የታላቆ ህዳሴ ግድብ ተቀዳሚ ዳይሬክተር አቶ ሃይለኪሮስ ጠዓመ  ናቸው።

በክልሉ የግድቡን ግንባታ ከተጀመረበት ወቅት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ  ከ469 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቦ ገቢ መደረጉን ተናግረዋል።

Rate this item
(0 votes)

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን