አርዕስተ ዜና

በሂርና ከተማ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ተጠናቀው ለአገልግሎት በቁ

460 times

ጭሮ 5/2010 በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ሂርና ከተማ 17 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መንገድና ሌሎች የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ተጠናቀው ለአገልግሎት በቁ፡፡

የከተማዋ አስተዳደር ከንቲባ  አቶ እስክንድር አህመድ እንደገለጹት በአንድ ዓመት ውስጥ የተገነቡት  እነዚህ መሰረተ ልማቶች ከህብረተሰቡ ጥያቄ በመነሳት ነው፡፡

በዚህም አስር  ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ ጠጠርና ሰባት  ኪሎ ሜትር ጥርጊያ መንገድ እንዲሁም የከተማዋ የመንገድ ዳር መብራት ዝርጋታና  የፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ ግንባታዎች ተከናውነዋል፡፡

ለግንባታዎቹም  ከአራት ሚሊዮን ብር በላይ  ወጪ መውጣቱን  ያመለከቱት ከንቲባው የድሬደዋ ከተማ አስተዳደርም የግንባታ ማከናወኛ መሳሪዎችን ድጋፍ እንዳደረገላቸውም ጠቅሰዋል፡፡

በየዞኑ የከተማ እና ቤቶች ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አድማሱ ቀነዓ በበኩላቸው መንግስት የከተሞችን መሰረተ ልማት ለማሟላት የሚያደርገውን ጥረት ህብረተሰቡ በመደገፍ የበኩሉን  እንዲወጣ ጠይቀዋል።

በቀጣይም ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ምላሽ ለመመለስ   ጥረት እንደሚደረግም ጠቅሰዋል፡፡

የከተማዋ ነዋሪ  አቶ መሀመድ ኢዲሪስ በሰጡት አስተያየት በክረምት ወቅት መንገዱ እየጨቀየ  ለመንቀሳቀስ ይቸገሩ እንደነበርና አሁን ተሰርቶ ለአገልግሎት በመብቃቱ  እፎይታ እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል፡፡

ሌላው ነዋሪ አቶ አህመድ ጂብሪል በበኩላቸው ከተሀድሶው በኋላ  የልማት ጥያቄያቸው ምላሽ እያገኘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

Last modified on Tuesday, 13 February 2018 16:52
Rate this item
(0 votes)

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን