አርዕስተ ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደንበኞች የበረራ አገልግሎትን የሚያቀላጥፍ መተግበሪያ ይፋ አደረገ Featured

04 Jan 2018
345 times

አዲስ አበባ ታህሳስ 25/2010 የኢትዮጵያ አየር መንገድ የደንበኞች የበረራ አገልግሎትን የሚያቀላጥፍ መተግበሪያ ይፋ አደረገ።

አየር መንገዱ መተግበሪያውን ከዛሬ ጀምሮ ስራ ላይ ማዋሉን በይፋ አሳውቋል።

መተግበሪያው ደንበኞች በየትኛውም ቦታ ሆነው በተንቀሳቃሽ ስልኮች የበረራ ትኬት ለመቁረጥ፣ ክፍያ ለመፈጸም እና የበረራ ወንበር ቁጥር መምረጥ እንደሚያስችላቸው ተገልጿል።

በአየር መንገዱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተሰራው ይህ መተግበሪያ አየር መንገዱ የሚሰጠውን አገልግሎት ያቀላጥፋል።

መንገደኞችም አማርኛን ጨምሮ እንግሊዝኛ፣ ጀርመንኛ፣ ፈረንሳይኛና ሌሎች የውጭ ሃገራት ቋንቋዎችን በመጠቀም አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም  የአገልግሎቱ መጀመር ለደንበኞች ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችል ተናግረዋል።

የአየር መንገዱ ደንበኞች  በሞባይል ባንኪንግ አልያም በኢንተርኔት ክፍያ በመፈጸም የበረራ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ