አርዕስተ ዜና

የጅቡቲ የወደብ አገልግሎት ዋጋ 45 በመቶ ቅናሽ ተደረገበት Featured

07 Dec 2017
507 times

ጅቡቲ ህዳር 28/2010 የጅቡቲ ወደብ አገልግሎት ዋጋ የ45 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን የአገሪቱ መንግስት አስታወቀ።

የጅቡቲ ደረቅ ወደብ አስተዳደር ለኢዜአ እንዳስታወቀው የጅቡቲ መንግስት በሁሉም የወደብ አገልግሎቶች ላይ የዋጋ ቅናሽ አድርጓል።

የአገሪቱ የደረቅ ወደብ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዋሂብ ዳሂር ኤደን እንዳሉት ከአንድ ሳምንት በፊት በጅቡቲ  መንግስት ውሳኔ መሰረት የዋጋ ማስተካከያዎቹ ተደርገዋል።

በዚህም የዋጋ ቅናሽ የተደረገባቸው ሁሉም የካርጎ፣የደረቅ ወደብና የተሽከርካሪ አገልግሎቶች መሆናቸውን ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት  በዱራሌ ዘርፈ ብዙ ወደብ የጅቡቲ መንግስት ዘመናዊ  አሰራር እየዘረጋ በመሆኑም ለተጠቃሚዎች ጊዜና ገንዘብን እንደሚቀንስ አስረድተዋል።

በጥቂት ግዜ ውስጥ በሚጠናቀቀው የባቡር መስመር ዝርጋታ ከወደቡ ጋር የሚያገናኝ የአንድ ኪሎ ሜትር የባቡር ሐዲድ ግንባታ እንደሚቀር አመልክተው ከስድስት ወር በኋላ አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ገልጸዋል።