አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

በምስራቅ ሸዋ 75 በመቶ የሚሆነው ምርት ተሰብስቧል

14 Nov 2017
471 times

አዳማ ህዳር 5/2010 በምሥራቅ ሸዋ ዞን ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በተካሄደው ዘመቻ በመኸር ከለማው ማሳ 75 በመቶ መሰብሰቡን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በጽህፈት ቤቱ የግብርና ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አስቻለው ዘነበ ዛሬ እንደገለጹት ከብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ በተገኘው ትንበያ መሰረት የዞኑ አርሶ አደሮች ሰብሉን ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብ ለማዳን የተጠናከረ ምርት የመሰብሰብ ስራ እያካሔዱ ነው።

ከመስከረም መጨረሻ ጀምሮ እስካሁን በዘመናዊ የእርሻ መሳሪያዎችና በሰው ሃይል በመታገዝ በተካሄደው እንቅስቃሴ በመኽር ወቅት ከለማው 438 ሺህ 356 ሄክታር መሬት ውስጥ በ328 ሺህ 767 ሄክታር መሬት ላይ የሚገኝ ሰብል ታጭዶ ተከምሯል።

ከሽንብራና ጓያ በስተቀር የአገዳ፣ ብርዕና ጥራጥሬ ሰብሎች መሰብሰባቸውን ገልጸው ቀሪውን ምርት የመሰብሰብ ስራ እስከዚህ ወር መጨረሻ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በምርት ማሰባሰቡ ስራ 26 ሺህ 830 ሴቶችን ጨምሮ ከ163 ሺህ የሚበልጡ አርሶ አደሮች በክላስተር ተቀናጅተው እየተሳተፉ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

በተለይ በምርት ማሰባሰብ ወቅት ብክነት እንዳይከሰት ቀደም ሲል ስልጠና የተሰጣቸው በዞኑ በየደረጃው የሚገኙ አስፈጻሚ አካላት ለአርሶ አደሩ በቅርበት ክትትልና ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን አመልክተዋል።

በዞኑ በተካሄደው ቅድመ ምርት ትንበያ ከለማው አጠቃላይ መሬት 15 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።

በዞኑ ከሚገኙ አርሶ አደሮች መካከል 74 በመቶ የሚሆኑት ሙሉ የግብርና ኤክስቴንሽን ፓኬጅ ተጠቃሚ መሆናቸውን የተናገሩት አስተባባሪው ዘንድሮ አማካኝ የሰብል ምርታማነትን በሄክታር 36 ኩንታል ለማድረስ ግብ ተይዞ መሰራቱን አውስተዋል።

በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ የዶኒ ጎምቤ ቀበሌ አርሶ አደር በዳዳ ረጋሳ በሰጡት አስተያየት በመኸር ወቅት በአምስት ሄክታር መሬት ላይ ያለሙትን ጤፍ በቅርቡ አጭደው በመውቃት 50 ኩንታል ምርት ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

በአዳማ ወረዳ መልካ አዳማ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ገዛኸኝ ተሾመ በበኩላቸው ምርታቸውን ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብ ለመከላከል በ2 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የዘሩትን ጤፍ ሙሉ በሙሉ አጭደው መከመራቸውን ገልጸዋል።

በቅርቡ ወቅተው ወደ ጎተራ ለማስገባት ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ