አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

የፍቼ ከተማ አስተዳደር ህገ ወጥ የንግድ ድርጅቶችን እያሸገ ነው

13 Sep 2017
420 times

ፍቼ  መስከረም 3/2010 ፍቼ  ከተማ  አስተዳደር  ህገ  ወጥ ንግድን  በሚያንቀሳቀሱ  የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ  እየወሰደ መሆኑን አስታወቀ ።

በህገወጥ  ንግዱ  የከተማ  አስተዳደሩ  ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ  ማጣቱም  ታውቋል፡፡

የአስተዳደሩ  ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አዳነ ረታ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለፁት በከተማው ቀረጥና ግብር ሳይከፍሉ በህገወጥ መንገድ የሚነግዱ ከ1ሺህ 6ዐዐ በላይ ግለሰቦች እንደሚገኙ ባለፈው ዓመት በተካሂደ ጥናት ተረጋግጧል፡፡

ህገወጥ ነጋዴዎቹ በህጋዊ ነጋዴዎች ላይ  አሉታዊ ተፅእዕኖ ከማሳደራቸውም ሌላ ባለፈው በጀት ዓመት መንግሥትና ህዝብ ከግብር ማግኘት የነበረባቸውን ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲታጣ አድርገዋል፡፡ ህገወጥ ነጋዴዎቹ በከተማው ከግብር  እና ቀረጥ ለመሸሽ  አመቺ ጊዜ እየጠበቁ በመፈራረቅ እንደሚንቀሳቀሱ ያመለከቱት  አቶ አዳነ "በአብዛኛው በአዲስና ልባሽ ጨርቆች፣ በቤት ውስጥ የመገልገያ ቁሳቁሶች ፣በወተት ማሰባሰብና ማከፋፈል ፣በሴራሚክ ችርቻሮና  በአሸዋና ጠጠር ንግድ ስራ የተሰማሩ ናቸው" ብለዋል ።

 ከነጋዴዎቹ መካከል አንዳንዶቹ  እስከ 250 ሺህ ብር ድረስ እንደሚያንቀሳቅሱ ጠቅሰው ተመክረውና ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ባለመስማታቸው ጽህፈት ቤቱ እርምጃ ለመውሰድ መገደዱን አስታውቀዋል።

 እስከ አሁንም ቋሚ አድራሻ እያላቸው በህገወጥ መንገድ ሲሰሩ የተገኙና ወደ ህጋዊ የግብር መረብ እንዲገቡ በተደጋጋሚ ተጠይቀው ፈቃዳኛ ያልሆኑ 344 ድርጅቶች እንዲታሸጉ ተደርጓል ።

 የጽህፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊው እንዳሉት  ግብር ላለመክፈል  ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩና አድራሻ እየቀያየሩ የሚሰሩ ህገ ወጥ ነጋዴዎችን  መልክ ለማስያዝም ከተደጋጋሚ  ማስጠንቀቂያ በኋላ ሲሸጥ የተገኘ ዕቃ  የሚወረስበት አሰራር ተመቻችቷል፡፡

 ድርጅታቸው ከታሸገባቸው መካከል በወለል ንጣፍና ሴራሚክ ንግድ የተሰማሩት አቶ በሽር ኑረዲን በሰጡት አስተያየት ህጋዊ ፍቃድ ለማውጣት ቢሞክሩም በርካታ መስፈርቶችን ስለሚጠይቁ ህጋዊ መሆን እንዳልቻሉ ነው የተናገሩት፡፡

 ከመኖሪያ መታወቂያ አንስቶ አቅማቸውንና ሥራቸውን በማይመጥን የሂሣብ መመዝገቢያ ማሽን፣ ደረሰኝና ማህተም እንዲያሰሩ በመጠየቃቸው ግብር ሊጭኑብኝ ነው በሚል ስጋት ንግድ ፈቃድ ሳያወጡ መቆየታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

 ሌላው አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ ጌጤ   በቀለ  በበኩላቸው  ወተት ከነጋዴዎችና አቅራቢዎች  ተረክበው የትርፍ ትርፍ   ለማግኘት እንደሚሰሩ ገልፀው አቅማቸው አነስተኛ በመሆኑ የብድር አገልግሎት ካልተመቻቸላቸው ፈቀድ አውጥተው ለመስራት እንደሚቸገሩ ገልጸዋል፡፡

 በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ንግድ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ መከተ ደባልቄ "ህገ-ወጥ ነጋዴዎች በህብረተሰቡና በመንግሥት ላይ የሚሳድሩትን ተጽዕኖ ለማስቆም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅተን በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን " ብለዋል።

 በከተማው የሚታየው የላላ ቁጥጥርና ክትትል ህገ-ወጥ ነጋዴዎቹን ከዕለት ወደ ዕለት እንዳበራከታቸው ጠቅሰው ነጋዴውም ሆነ ህብረተሰቡ  ህግና ስርዓትን በማክበር  መንቀሳቀስ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ