አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

በኦሮሚያ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት 740 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ያገኛሉ

12 Aug 2017
223 times

አዳማ ነሐሴ 6/2009 በኦሮሚያ ክልል በአዲሱ በጀት ዓመት ከ740 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጠር የክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራና የከተሞች ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ገለጸ።

የሥራ ዕድል ከሚፈጠርላቸው ዜጎች መካከል 550 ሺህ የሚሆኑት በቋሚነት ቀሪዎቹ ደግሞ በጊዜያዊነት ወደ ሥራ የሚገቡ መሆናቸው ተመልክቷል።

የክልሉ የሥራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጄንሲ ኃላፊ አቶ አወሉ ከድር ለኢዜአ እንደገለጹት የክልሉ መንግስት የወጣቶችን የሥራ ዕድል ይፈጠርልን ጥያቄ ለመመለስ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ ነው።

ለዚህም "በበጀት ዓመቱ 740 ሺህ የሚሆኑ ዜጎችን በቋሚነትና በጊዜያዊነት ወደ ሥራ ለማስገባት ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ተገብቷል" ብለዋል።

እንደኃላፊው ገለጻ፣ ወጣቶቹ በሚሰማሩባቸው የሥራ መስኮች ውጤታማ እንዲሆኑ ከ40 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት ለመስሪያና መሸጫ ቦታ ለመስጠት ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው።

ከተዘዋዋሪ ፈንድ በተጨማሪ  የክልሉ መንግስት ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ለመስጠትና ከ2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ የገበያ ትስስር ለመፍጠር በመስራት ላይ ይገኛል።

ለ555 ሺህ  ዜጎች በቋሚነት የሥራ ዕድል ይፈጥራሉ ተብለው በጥናት ከተለዩት የሥራ አማራጮች መካከል ማኑፋክቸሪንግ፣ ግንባታ፣ ግብርና፣ የማዕድን ልማት፣ የእንስሳት እርባታና ማድለብ ሥራ፣ ንግድና የአገልግሎት ዘርፍ ዋና ዋናዎቹ ናቸው ።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክልሉ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጠሩንም አቶ አወሉ አስታውሰዋል።

መንግስት በ2009 በጀት ዓመት በተዘዋዋሪ ፈንድ ለክልሉ ከመደበው 3 ነጥብ 2 ቢሊዮብ ብር ወስጥ 660 ሚሊዮን ብር እንዲሁም  ከመደበኛ ፕሮግራም 2 ነጠብ 5 ቢሊዮን ብር ለጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ብድር መሰጠቱንም አስታውቀዋል።

ለመስሪያና መሸጫ፣ ለእንስሳት ዕርባታና ማድለብ፣ ለእርሻ፣ አገልግሎትና ለንግድ የሚውል መሬትን ጨምሮ 50 ሺህ ሄክታር መሬት በዚሁ ዓመት ለማህበራቱ መተላለፉንም ጠቁመዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን በህገ ወጥ መንገድ በኪራይ ሰብሳቢ ባለሃብቶች ተይዞ የነበረ ከ14 ሺህ ሄክታር በላይ የእርሻና የማዕድን መሬት ለወጣቶች መሰጠቱን ነው ያመለከቱት።

የሥራ ዕድል ከተፈጠረላቸው ወጣቶች መካከል ወጣት ወንድማገኝ ታደሰ፣ አምስት ሆነው በማህበር በመደራጀት ከመንግስት ባገኙት 1 ሚሊዮን ብር ብድር በወንጂ ኩሪፍቱ በእንስሳት ማድለብ ሥራ መሰማራታቸውን ተናግሯል ።

በአሁኑ ወቅትም 48 የደለቡ ከብቶችን ለገበያ ለማቅረብ መዘጋጀታቸውንና በምትኩ 100 ከብቶችን ወደ ማድለቢያ ለማስገባት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ገልጿል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ