አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

በቆዳና ሌጦ ግብይት ችግር ለኪሳራ እየተዳረግን ነው -አቅራቢ ነጋዴዎች

17 Jul 2017
1236 times

ደብረ ማርቆስ ሐምሌ 10/2009 የቆዳና ሌጦ ግብይት ስርአት ችግር ለኪሳራ እየደረጋቸው መሆኑን  በምስራቅ ጎጃም ዞን አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎች ገለጹ።

በሀገሪቱ የጫማና ቆዳ ማምረቻ ዘርፍ መስፋፋት ለቆዳና ሌጦ ገበያ አመቺ ቢሆንም የግብይት ሰንሰለቱ ፍትሀዊና ተጠያቂነት ላይ የተመሰረተ አለመሆኑ አቅራቢውን ለጉዳት እየዳረገው መሆኑን አስተያየት ሰጪዎቹ ገልፀዋል፡፡

በደብረማርቆስ ከተማ ቀበሌ02 ነዋሪና የዘርፉ ነጋዴ  አቶ አህመድ ኑር እንደገለፁት በዘርፉ ያለው የግብይት ስርአት ምርቱን በሚረከቡ ፋብሪካዎች ይሁንታ ላይ መመስረቱና የደላሎች ጣልቃ ገብነት እየሰፋ አቅራቢውን ትርፋማ እንዳይሆን አድርጎታል ።

በሚያዚያ ወር ገዝተው ወደ አዲስ አበባ ያጓጓዙትን ከ60 ሺህ በላይ ቆዳና ሌጦ ለፋብሪካዎች ቢያስረክቡም እስካሁን ገንዘቡን ማግኘት አለመቻላቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል ።

ከፍተኛ እርድ በሚፈጸምባቸው በዓላት   ቆዳና ሌጦውን ሰብስበው ለማስረከብ መቸገራቸውን አስረድተዋል።

ሌላው በዚሁ ከተማ  ቀበሌ 06 ነዋሪና  ነጋዴ አቶ ሊቀመንበር ካሳ እንዳሉት በቆዳና ሌጦ ንግድ ከተሰማሩ ከአስር አመት በላይ ቢሆናቸውም በዘርፉ የሚታየው ውሰብስብ የገበያ ስርአት መሻሻል አለማሳቱን ተናግረዋል።

ከአርሶአደሩ ጥራቱን ፈትሸው በመግዛት አዲስ አበባ  ለሚገኙ ፋብሪካዎች የሚያቀርቡት ቆዳና ሌጦ ዋጋው የሚተመነው በተረካቢ ፋብሪካዎች ብቻ በመሆኑ ለኪሳራ እንደዳረጋቸው ጠቅሰዋል ።

በተጨማሪም "አንዳንድ ህገ-ወጥ  ደላሎች ጣልቃ በመግባት ከወረዳዎች የሚሰበስቡትን ቆዳና ሌጦ ከፋብሪካዎች ጋር በመደራደር ዋጋ ቀንሰው  ስለሚያስረክቡ ህጋዊና ግብር ከፋዩን ነጋዴ ክውድድር ውጭ እያደረጉት ነው "ሲሉ በግብይቱ መማረራቸውን ገልፀዋል ።

"ተረካቢ ፋብሪካዎች የቆዳና ሌጦ ገበያውን የአስረካቢ ነጋዴው ጥቅም ብቻ አድርገው እያዩት ነው" ብል መሳሳት አይሆንም ያሉት ደግሞ በአነደድ ወረዳ የቀበሌ 01 ነዋሪ አቶ አስረስ አብነት ናቸው።

እሳቸው እንዳሉት  ለፋብሪካ ግብዓት እንዲሆን በጥንቃቄ መርጠው የሚገዙትን ቆዳና ሌጦ አጓጉዘው አዲስ አበባ ካደረሱ በኋላ ተረካቢ ፋብሪካዎች ከተገዛበት  ዋጋ በታች በመተመንና በጊዜው ስለማይረከቧቸው ለኪሳራ እየዳረጓቸው ነው ።

በዘርፉ የሚታየው የግብይት ችግር አቅራቢ ነጋዴውን ብቻ ሳይሆን በሂደት የዘርፉን ኢንዱስትሪ እድገት የሚጎዳ በመሆኑ መንግስት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈልግ አስተያት ሰጭዎቹ ጠይቀዋል ።

የዞኑ ንግድ ኢንዱስትሪና ገበያ ልማት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ሰለሞን አሞኘ ስለጉዳዩ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ነጋዴዎቹ ያቀረቡት ቅሬታ ትክክል መሆኑን ገልፀዋል፡፡

እንደ ምክትል ኃላፊው ገለፃ በዘርፉ ያለውን የግብይት ችግር ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነው ።

በዘርፉ ህገወጥ የንግድ እንቅሰቃሴን ለመከላከል በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ ከ78 በላይ የግብይት ማእከላት መገንባታቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል ።

ከዚሁ ጎን ለጎን ፋብሪዎች ከአቅራቢ ነጋዴዎች ለተረከቡት ቆዳና ሌጦ በወቅቱ ክፍያ ያልፈፀሙበትን ምክንያት አጣርቶ መፍትሄ  ለመስጠት ጥረት መደረጉን ተናግረዋል ።

"ፋብሪካዎች ባጋጠማቸው የኬሚካል እጥረት አምርተው መሸጥ ባለመቻላቸው የተፈጠረ ችግር በመሆኑ ገንዘቡ በቅርቡ ለነጋዴዎቹ የሚመለስላቸው መሆኑ ተረጋግጧል " ብለዋል ።

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትም የገበያ ትስስር መፈጠሩን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በዞኑ በበጀት አመቱ ከ150 በላይ በሚሆኑ አቅራቢ ነጋዴዎች ከ640 ሺህ በላይ ቆዳና ሌጦ ለፋብሪካዎች መቅረቡ ታውቋል ።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ