አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

ኩባኒያው ከ20 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን ገለጸ

19 Jun 2017
330 times

ነቀምቴ ሰኔ 12/2009 ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ የተባለው ኩባኒያ በሀገሪቱ በከፈታቸው የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች ከ20 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን ገለጸ፡፡

ኩባንያው በምሥራቅ ወለጋ ዞን አርጆ ከተማ በ15 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባው የነዳጅ ማደያ በኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ትናንት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

በምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ታደሰ ጥላሁን በአርጆ ከተማ በ3 ሺህ 564 ካሬ ሜትር ላይ  ተገንብቶ ለአገልግሎት የበቃው  የነዳጅ ማደያ በአንድ ጊዜ ስምንት ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም ያለው ሲሆን የባንክና ሌሎችንም  አገልግሎቶች የሚሰጥ ነው፡፡

አቶ ታደሰ እንዳሉት  ኩባንያው የአሁኑን ጨምሮ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በከፈታቸው የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች ከ20 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡

በኢትዮዽያ የደን መመናመንን ችግር ለመከላከል የሚደረገውን  ጥረት ለመደገፍ ኩባኒያው ጭስ አልባ ቡታ ጋዝ የ35 በመቶ ቅናሽ በማድረግ እያሰራጨ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ማደያውን በመረቁበት ወቅት እንደገለጹት መንግሥት ለግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ለሀገሪቱ ልማት የድርሻውን እንዲወጣ የጀመረውን እንቅስቃሴ  አጠናክሮ ይቀጥላል።

የአርጆ ከተማ ነዋሪ አቶ ቀልቤሣ ሆርዶፋ በሰጡት አስተያየት የነዳጅ ማደያው  መሰራት የከተማው ማህበረሰብ ነዳጅ ፍለጋ ወደ ነቀምትና በደሌ ከተሞች በመጓዝ ይድርስበት የነበረውን  እንግልት እንደሚያስቀር ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ በጅቡቲ የሚገኘውን የኦይል ሊቢያ ኩባንያ ፣የነዳጅ ማደያና አየር ማረፊያ ዴፖ ከ450 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ መግዛቱንም ጠቁመዋል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ