አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452

በአማራ ክልል 196 አነስተኛ የመስኖ ተቋማት ግንባታ እየተካሄደ ነው

19 May 2017
540 times

ባህር ዳር ግንቦት 11/2009 በአማራ ክልል  ግማሽ ቢሊዮን ብር በሆነ ወጪ 196 አነስተኛ የመስኖ ተቋማት ግንባታ እየተካሄደ ነው፡፡

በክልሉ ግብርና ቢሮ  የመስኖ መሰረተ ልማት  ዳይሬክተር አቶ እንዳገር ጌትነት ለኢዜአ እንደገለጹት የመስኖ ተቋማቱ ግንባታ እየተካሄደ ያለው ከጥር ወር 2009 ዓ.ም ጀምሮ ነው።

ከግንባታዎቹ መካከል አነስተኛ ግድቦች፣ የወንዝ ጠለፋና  ምንጭ ማጎልበት ይገኙበታል፡፡

እስካሁን በተካሄደው እንቅስቃሴ ከቁፈራ ስራ ጀምሮ እስከ 80 በመቶ ግንባታቸው የተጠናቀቀ መሆኑን የተናገሩት ዳይሬክተሩ "አብዛኞቹ እስከበጀት ዓመቱ መጨረሻ በማጠናቀቅ የክረምቱን ውሃ እንዲይዙ ይደረጋል" ብለዋል።

አነስተኛ ግድቦቹ 86 ሲሆኑ  በመጪው ክረምት ከሦስት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ ውሃ የመያዝ አቅም እንዳላቸውና  አንድ ሺህ 400 ሄክታር መሬት በመስኖ ማልማት ያስችላሉ፡፡

15 ሺህ የሚሆኑ አርሶ አደሮች በመስኖ ልማት ተጠቃሚ እንደሚያደርጉም ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ከ109 ሺህ በላይ የቤት እንስሳትም የመጠጥ ውሃ ግልጋሎት እንዲያገኙ የሚያደርጉ መሆናቸውንም አቶ እንዳገር አመላክተዋል፡፡

የመስኖ ተቋማቱ መገንባት በተለይም ከአየር ንብረት መለዋወጥ ጋር በተያያዘ እየተከሰተ ያለውን ድርቅ ለመቋቋም ያግዛሉ፡፡

በክልሉ መንግስትና በልማት አጋሮች ድጋፍ በሁሉም ዞኖች እየተገነቡ ያሉት የመስኖ ተቋማቱ በ91 ኢንተርፕራይዞች የተደራጁ 500 ማሃንዲሶች አማካኝነት እንደሆኑም  ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

ባለፈው ዓመት በ132 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነቡ  63 ግድቦች  ውሃ በማሰባሰብ  ድርቅን መቋቋም እንዳስቻሉም ተጠቅሷል፡፡

 

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ