አርዕስተ ዜና

በመተማና ሁመራ በኩል ከሁለት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

19 May 2017
627 times

ጎንደር ግንቦት 11/2009 ግምታቸው ከሁለት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ብር የሚበልጥ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የጎንደር ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ አስታወቀ።

የጣቢያው ተወካይ አቶ ፋሲል አፈወርቅ ለኢዜአ እንደገለጹት የኮንትሮባንድ እቃዎቹ የተያዙት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተደረገ ክትትል ነው።

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከልም  የተዘጋጁ አዳዲስ የሴትና የወንድ አልባሳት ፣የመዋቢያ ቁሳቁሶችና  የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ይገኙበታል።

በህብረተሰቡ ጥቆማና በፀጥታ አካላት ቁጥጥርና ክትትል የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያጓጉዙ የተገኙ 32 ተሸከርካሪዎችና 103 ግለሰቦች ተይዘው ጉዳያቸው ለህግ መቀረቡን አቶ ፋሲል አስታውቀዋል፡፡

በሱዳንና በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ የሚካሄደው የጋራ የኮንትሮባንድ ንግድ ቁጥጥር መጠናከር ህገ-ወጥ ድርጊቱ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም በግማሽ ሚሊዮን ብር እንዲቀንስ ማስቻሉንም ጠቅሰዋል።

የመተማ ዮሃንስ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ እሸቴ መልኬ በበኩላቸው " ኮንትሮባንድን ለመከላከል ከህብረተሰቡና ከጸጥታ አካሉ ተውጣጥቶ የተቋቋመው የጸረ-ኮንትሮባንድ ግብረ-ሃይል የተጠናከረ ክትትልና ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል"ብለዋል፡፡

ኮንትሮባንድ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ በሚያሳድረው አሉታዊ ተጽዕኖ ዙሪያ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መከናወኑንም አመልክተዋል፡፡

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ

<!-Foreign Exchange Rates widget - HTML code - fx-rate.net -->

<!-end of code-->

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ