አርዕስተ ዜና

የስልጤ ዞን ነዋሪዎች ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 101 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ Featured

19 May 2017
608 times

አዲስ አበባ ግንቦት 11/2009 የስልጤ ዞን ነዋሪዎች ለታላቁ  የኢትዮጵያ  ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል የገንዘብና የተለያዩ ድጋፎች አደረጉ።

በዞኑ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ  ነዋሪዎች የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ በስጦታ የተላኩ አስር ሰንጋ በሬዎችን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ የሚሳተፉ ሠራተኞችን ለማበረታታት በስጦታ አበርክተዋል።

ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ነዋሪዎቹ ከ101 ሚሊዮን ብር በላይ በቦንድ ግዥ ድጋፍ አድርገዋል። ለግድቡ መጠናቀቅ ነዋሪው በገንዘብም በዓይነትም በቦንድ ግዥም ለመሳተፍ ተነሳሽነቱም አቅሙም እንዳለው ነው የተገለጸው።

የዞኑ ነዋሪ ሃጂ ሸኩር አህመድ እንደተናገሩት፤ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ እሚካሄድበት ቦታ ድረስ በመጓዝ በአካል መጎብኘታቸውና ድጋፍ ማድረጋቸው አስደስቷቸዋል።

የስልጤ ዞን ነዋሪዋ መምህርት ባዩሽ ጌታቸው በበኩላቸው፤ ''ግድቡን  ማየቴ የተለየ ስሜት ፈጥሮብኛል። ቀጣይም ድጋፌን እቀጥላለሁ'' ብለዋል።

በጉብኝቱ የተሳተፉትና ሌላው የዞኑ ነዋሪ አቶ አብድል ሃጂ አህመድ ደግሞ፤ ''ዛሬ በእኛ ዘመን  ባለን አቅም መገንባት መቻሉ የመነቃቃት ስሜት ፈጠሮብኛል'' ሲሉ ተናግረዋል።፡

የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ መዘረዲን ሁሴን እንደተናገሩት፤ የዞን ነዋሪዎች ግንባታው እስከሚጠናቀቅ ድረስ ድጋፋቸውን አጠናክረው ይቀጥላሉ።

እንደርሳቸው ገለጻ፤ የዞኑ ነዋሪ በገንዘብም በዓይነትም በቦንድ ግዥም መሳተፍ የሚችልበት ተነሳሽነቱም አቅሙም አለው።

ስድሰተኛው የግድቡ ግንባታ ከ57 በመቶ በላይ የተጠናቀቀ ሲሆን የግድቡ አርማታ ሙሌት ሥራም 72 በመቶ መጠናቀቁ ይታወሳል።

ከኅብረተሰቡ በተለያዩ መንገዶች እየተደረገ ያለው የገንዘብ አስተዋጽኦ ዘጠኝ ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር  መድረሱን  ከግድቡ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ