አርዕስተ ዜና

ዳያስፖራው በግማሽ ዓመቱ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ከሁለት ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ አድርጓል Featured

17 Feb 2017
400 times

አዲስ አበባ የካቲት 10/2009 በተለያዩ የዓለም አገራት የሚኖሩ ዳያስፖራዎች ባለፉት ስድስት ወራት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በቦንድ ግዢና በስጦታ ከሁለት ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የግድቡ ግንባታ የተጀመረበትን 6ኛ ዓመት አስመልክቶ የዳያስፖራውን ተሳትፎ ለማሳደግ የተለያዩ የድጋፍ መርሃ ግብሮች ተዘጋጅተዋል።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ የግድቡ ግንባታ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ ድጋፍ የሚጠይቅ መሆኑን ጠቁመው፤ ዳያስፖራው ይህንን ጨምሮ አገሪቷ በምትከውናቸው የልማት ስራዎች ግንባር ቀደም ተሳታፊ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በግማሽ ዓመቱ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በአፍሪካና በአንዳንድ የአውሮፓ አገራት የሚኖሩ ዳያስፖራዎች ለግድቡ ግንባታ ከ2 ሚሊዮን ዶላር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸውን በመግለጽ።

ዳያስፖራዎቹ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች አማካኝነት በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ባተኮሩ 199 የውይይት መድረኮች መሳተፋቸውንም ተናግረዋል።

እንደ አቶ ተወልደ ገለጻ ዳያስፖራው የትውልድ አገሩን በገንዘቡና በዕውቀቱ እንዲደግፍ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ቅስቀሳ እያካሄዱ ነው።

ኤምባሲዎቹ ዳያስፖራው በሚኖርባቸው አገራት ከደመወዝ ክፍያ፣ ከኢንሹራንስ፣ ከህግ ከለላና ከመሳሰሉት ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታትም ጥረት እያደረጉ ነው ብለዋል።

በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት 8 ሺህ 400 የሚሆኑ ዳያስፖራዎች ያጋጠሟቸውን ችግሮች መፍታት እንደተቻለ አስታውቀዋል።

በተለያዩ አገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ሚሲዮኖች የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲውን ለማጠናከር ባከናወኗቸው ተግባራት በግማሽ ዓመቱ 19 ትላልቅና 325 በመካከለኛና አነስተኛ ደረጃ የሚንቀሳቀሱ ኩባንያዎች የቅድመ ኢንቨስትመንት ጉብኝት ለማድረግ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን ገልጸዋል።

ባለሃብቶቹ ከቻይና፣ ከቱርክ፣ ከሞሮኮ፣ ጀርመንና ከሌሎች አገራት የተውጣጡ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን

 

የውጭ ምንዛሪ መቀየሪያ