አርዕስተ ዜና
Items filtered by date: Sunday, 04 February 2018

አዲስ አበባ ጥር 27/2010 "ኢትዮጵያ በበርካታ አገራት የማይታይ የኃይማኖትና የብዝሃነት መቻቻል ተምሳሌት ናት" ሲሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሚካኤል ራይነር ተናገሩ።

 አምባሳደሩ ይህን ያሉት የላሊበላ ቤተ ጎልጎታ-ሚካኤል ውቅር አብያተ ክርስትያን የጥገና ፕሮጀክት ትናንት በይፋ ሲጀመር ነው።

 የአሜሪካ አምባሳደሮች ፈንድ ለእድሳት ፕሮጀክቱ የ 580 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ማድረጉንም ተገልጿል።

 አምባሳደር ሚካኤል ራይነር ኢትዮጵያ የሚያኮራ እሴትና ባህል ባለቤት መሆኗን ዓለም ሊገነዘበው እንደሚገባ ተናግረዋል።

 ብዝሃነትና በብዝሃነት ውስጥ ያለው መቻቻል የኢትዮጵያን ባህል ልዩ ከሚያደርጉት እሴቶች መካከል አንዱ እንደሆነ የተናገሩት አምባሳደሩ፤ "ይህ ዓይነቱን እሴት በበርካታ አገራት አናገኘውም "ብለዋል።

 የኢትዮጵያን ባህላዊ እሴትን መጠበቅ ከሚፈጥረው ሠላምና መረጋጋት ባሻገር የበለጸገች አገር ለመገንባት ከፍ ያለ ድርሻ እንዳለው አምባሳደሩ ተናግረዋል።

 ኢትዮጵያ ያላትን ባህላዊና ኃይማኖታዊ ክዋኔዎች እንዲሁም የተለያዩ ተፈጥሯዊ ቅርሶች ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ለማጎልበት በምታደርገው ሥራ የአሜሪካ መንግሥት ከጎኗ እንደሚቆም አምባሳደሩ አረጋግጠዋል።

 የአሜሪካ አምባሳደሮች ፈንድ ኢትዮጵያ ውስጥ ቅርስን ለመጠበቅ እየተከናወኑ ባሉት ዘጠኝ ፕሮጀክቶች ላይ ድረጋፍ እያደረገ ነው ብለዋል።

አምባሳደር ራይነር ኢትዮጵያ ለዓለም ቱሪዝም መጎልበት ያበረከተችውን አስተዋጽኦም አድንቀዋል።

Published in ማህበራዊ

ሶዶ ጥር 27/2010 በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም ዛሬ በተካሄደው የሰባተኛዉ ሳምንት ብሄራዊ ሊግ የወንዶች እግር ኳስ ጨዋታ የወላይታ ሶዶ ከተማና ሃዲያ ሌሞ ዜሮ ለዜሮ ተለያዩ፡፡

በሁለቱም የጨዋታ ክፍሌ ጊዜ ኳስ አደራጅቶ በመጫወት፣ በመከላከል፣ የመሃል ሜዳ ብልጫ በመውሰድና በማጥቃት የሶዶ ከተማ እግር ኳስ  ቡድን የተሻለ ነበር፡፡

በአንጻሩ የሃዲያ ሌሞ እግር ኳስ ቡድን ወደ ኋላ በማፈግፈግ መከላከልን መሰረተ አድርጎ በመልሶ ማጥቃት የጨዋታ ፍልሰት ተጋጣሚውን ለማስጨነቅ ሞክሩዋል፡፡

የሃዲያ ሌሞ እግር ኳስ ቡድን አሰልጣኝ አዲሴ ተሻለ " የሶዶ ከተማ ቡድን በተለይ በሜዳው አጥቀቶ እንደሚጫወት ስለምናውቅ ከተቻለ አሸንፈን ካልሆነ ነጥብ ለማስጣል ነበር ዕቅዳች ተሳክቶልናል "ብለዋል፡፡

" አሸንፈን ነጥባችንን ከፍ ለማድረግ አጥቅተን ተጫዉተናል፤ያገኘናቸውን ዕድሎች ወደጎልነት መቀየር ባለመቻላችን ነጥብ ጥለናል ነው " ያሉት ደግሞ የወላይታ ሶዶ ከተማ እግር ኳስ ቡድን አሰልጣኝ ኃይለማሪያም ጳዉሎስ ናቸው፡፡

በውጤቱ ደስተኛ እንዳልሆኑና በቀጣይ መስራት እንዳለባቸው ያመለከተ ጨዋታ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ጨዋታውን በርካታ ተመልካቾች ተገኝተው ስፖርታዊ ጨዋነት በተላበሰ መልኩ ቡድናቸውን በማበረታታት ደግፈዋል፡፡

Published in ስፖርት

አዳማ ጥር27/2010 ባለፉት ስድስት ወራት ከ6 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው መድኃኒቶችና የህክምና መርጃ መሳሪያዎች ከውጭ መግባታቸውን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰምሶን አብረሃም በተለይም ለኢዜአ እንደገለፁት መስሪያ ቤታቸው  ከውጭ የሚገቡ የተለያዩ ምርቶች ላይ የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ ሰለ መሆናቸው ቁጥጥርና የቤተሙከራ  ፍተሻ ያደርጋል።

ባለፉት ስድስት ወራት በ19 መግቢያና መውጫ ኬላ በሮችና በሰባት የፍተሻ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተፈትሸው የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ ግምታቸው  ከ6 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ የሆኑ  መድኃኒቶችና የህክምና መርጃ መሳሪያዎች ከውጭ እንዲገቡ ተደርጓል፡

ከውጭ የገቡት እነዚህ መድኃኒቶችና የህክምና መርጃ መሳሪያዎች በጤና ተቋማት አገልግሎት ላይ እንዲውሉ መሰራጨታቸውን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡ 

ከዚህም ሌላ ባለፉት ስድስት ወራት የመድኃኒት የጥራት ደረጃቸውን ያላሟሉ ከ24  ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው መድኃኒቶችና የህክምና መርጃ መስሪያዎች ወደ ሀገር ለማስገባት ሲሞከር  በተደረገው ቁጥጥርና ፍተሻ ተይዘው እንዲወገዱ መደረጉን አመልክተዋል።

እንዲሁም  1 ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ  ሜትሪክ ቶን የምግብ ምርቶችና የምግብ ጥሬ እቃዎች የጥራት ደረጃቸውን ያሟሉ መሆናቸው ተረጋግጠጦ  ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ መደረጉንም ጠቅሰዋል።

በህብረተሰብ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ከ1ሺህ 600 ሜትሪክ ቶን በላይ የምግብ ምርቶችና የምግብ ጥሬ እቃዎች ተይዘው መወገዳቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የተወገዱትም ምንጩ ያልታወቀ፣የተመረተበት ቀንና ቦታ ትክክለኛ ያልሆኑ፣የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜ በውል ስለማይታወቅና የባለስልጣንኑ የጥራት ደረጃ ባለሟሟላታቸው ነው፡፡

ዳይሬክተሩ እንዳሉት 54 በሚሆኑ የምግብና መድኃኒት አስመጪዎች ላይ ከማስጠንቀቂያ ጀምሮ ለህግ እስከ ማቅረብ ድረስ  እርምጃ ተወስዷል፡፡

በኬላዎችና የፍተሻ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች አካባቢ የሚስተዋሉ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ለማስወገድ የማስተካከያ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑም አብራርተዋል፡፡

የሞጆ ደረቅ ወደብ ጤና ኳራንት አስተባባሪ አቶ ግዛው ካሳ በበኩላቸው አስመጪዎች የምግብ፣መድኃኒት፣መጠጥና የኮሲሞቲክስ ምርቶች ላይ የተመረቱበት ሀገርና ለጤና ተስማሚ መሆናቸውን የሚያሳይ ሰርተፊኬትና  ሰነድ ያላቸው መሆኑን ፍተሻና ቁጥጥር እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

 

 

 

 

 

Published in ማህበራዊ

 መቀሌ ጥር 27/2010 የተጀመረው የጥልቅ ተሃድሶ ስራ በክልሉ መንግስታዊ መስሪያ ቤቶችም ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል አስታወቁ፡፡

 ዶክተር ደብረጽዮን  ዛሬ በመቀሌ ከተማ በተጀመረው የክልሉ ምክር ቤት  ጉባኤ ባቀረቡት ያለፉት ስድስት ወራት ሪፖርት ላይ እንዳሉት የክልሉን መንግስት የሚመራው ህወሓት በአመራር ደረጃ  የጥልቅ ተሀድሶ ስራ መጀመሩ ይታወቃል፡፡

 ይሄው ተሃድሶ በክልሉ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተግባራዊ ማድረግ ያስፈለገው በክልሉ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥና ሌሎችንም ችግሮች ለመፍታት እንዲቻል ነው፡፡