አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452
Items filtered by date: Saturday, 09 September 2017

አዲስ አበባ ጳጉሜ 4/2009 የኢህአዴግ ምክር ቤት የድርጅቱንና የመንግስትን የ2009 ዓ.ም ስራዎች አፈፃፀም በመገመገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ማስቀመጡን  የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ የኢህአዴግ ምክር ቤት ከጳጉሜ 3 እስከ 4 ባካሄደው ስብሰባ የድርጅትና የመንግስት ስራዎች ዕቅድ አፈፃፀምን በጥልቀት ገምግሟል። የቀጣይ  የትኩረት አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል።

ምክር ቤቱ ባለፈው ዓመት በነሃሴ የተጀመረው በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ የሚገኝበትን ሁኔታ፤ በተሃድሶው የተገኙ ውጤቶችና በቀጣይ ሊተኮርባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን በዝርዝር መገምገሙን ጠቁሞ፤ በሁሉም ደረጃዎች በተካሄዱ መድረኮች በተዛቡ አመለካከቶች ላይ ነጻ፣ ግልጽና መተክላዊ ትግል መደረጉን መፈተሹን መግለጫው አመልክቷል።

ስልጣንን ለግል ጥቅም ማዋል፣ የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካ መገለጫ የሆኑት ትምክህተኝነት፣ ጠባብነት፣ የሐይማኖት አክራሪነት፣ ብልሹ አሰራርና ሙስና እንዲሁም በፌዴራል ስርዓቱ ላይ የሚታዩ የተዛቡ አመለካከቶች ላይ ጠንካራ ትግል መደረጉን ምክር ቤቱ መገምገሙን መግለጫው አመልክቷል።

 

 

ምክር ቤቱ የተሃድሶ ሂደት በአባላት ዘንድ ተቀዛቅዞ የነበረውን የእርስ በርስ መተጋገል ማጠናከሩን  ገምግሟል።

በኢህአዴግ አባላትና ብሔራዊ ድርጅቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን አላስፈላጊ መጠራጠር በማስወገድ የትግል አንድነት እንዲፈጠር ማስቻሉንም ተመልክቷል፡፡

በጥልቀት የመታደስ እንቅስቃሴም የነበሩ ጉድለቶችን በዝርዝር ከመፈተሽ ጀምሮ የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ ውጤቶችን መመዝገባቸውንም መመልከቱን ጽህፈት ቤቱ የላከው መግለጫ ያብራራል፡፡

የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታን  በተመለከተ የመድበለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ከማጎልበትና ምህዳሩን ከማስፋት አኳያ በዓመቱ ተግባራት መከናወናቸውን ያስታወሰው ምክር ቤቱ፤ በተለይ ከአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የተጀመረው ድርድርና ክርክር ተጠቃሽ መሆኑን አመላክቷል።

ምክር ቤቱ በ2009 ዓ.ም በጥልቅ ተሃድሶው ሂደት የተገኙ መልካም ውጤቶችን በዝርዝር በማየት ያጋጠሙ ችግሮችንም በውል በመለየት በመጪው አዲስ ዓመት የተጀመረው የጥልቅ ተሃድሶ እንቅስቃሴ ይበልጥ እንዲጠልቅ እንደሚሰራ ገልጿል።

የፈጣን ልማት፣ የሰላምና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደቱን አጠናክሮ በማስቀጠል የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ሶስተኛው ዓመት ማሳካት የ2010 ዓ.ም ቁልፍ ተግባር መሆኑን ገልጿል።

የድርጅቱ አባላትና አመራር እንዲሁም መላው የአገሪቷ ሕዝቦች ይህንኑ በመገንዘብ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲያበረክቱ ምክር ቤቱ ጥሪ ማስተላለፉን መግለጫው ያትታል፡፡