አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452
Items filtered by date: Monday, 11 September 2017

ባህርዳር መስከረም 1/2010 የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ማህበር የዘመን መለወጫ በዓልን አስመልከቶ  ሁለት ሺህ ለሚጠጉ አቅመ ደካሞች፣ አረጋዊያን፣ አካል ጉዳተኞችና የጎዳና ተዳዳሪዎች ዛሬ የምሳ ግብዣ አደረገ።

የማህበሩ ሊቀመንበር ወጣት ፍፁም ደጀኔ በምሳ ግብዣ ወቅት እንደተናገረው ማህበሩ የምሳ ግብዣውን ያደረገው በአካባቢው የሚገኙ አጋር አካላትን በማስተባበር ባገኘው 80 ሺህ ብር ወጪ ነው።

የምሳ ግብዣውም በከተማዋ የሚገኙ ችግረኞች  በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ለማድረግ እንደሆነም ተናግረዋል።

ያለውን የመረዳዳትና የመተሳሰብ አኩሪ ባህልን  በቀጣይ ማህበሩ አጋር አካላትንና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በማስተባበር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።

ጧሪና ደጋፊ ስለሌላቸው በዓሉን ለብቻቸው ማሳለፍ ከብዷቸው እንደነበር የተናገሩት ደግሞ በምሳ ግብዣው ላይ የተሳተፉት  የ66 ዓመት እድሜ ያላቸው  አዛውንት ወረታ አያሌው ናቸው።

" ወጣቶች ባዘጋጁት የምሳ ግብዣ ላይ ተገኝቼ ብቸኝነት ሳይሰማኝ በዓሉን በደስታ ከወገኖቼ ጋር እንዳሳልፍ አስችሎኛል"ብለዋል፡፡

ወይዘሮ እትዋ ወርቁ በበኩላቸው ከስማዳ ወረዳ በችግር ምክንያት ከነልጃቸው ወደባህርዳር ከመጡ ገና ሁለት ወር እንደሆናቸው ገልጸዋል።

" የዘመን መለወጫ በዓልን በምን ሁኔታ ከእነልጄ ላሳልፍ ነው ስል ወጣቶች ባደረጉት ያልታሰበ የምሳ ግብዣ በዓሉን ተደስቼ እንዳሳልፍ አስችሎኛል "ብለዋል።

በተደረገላቸው የምሳ ግብዣ በዓሉን ብቸኝነትና ትካዜ ሳይሰማቸው በደስታ ማሳለፋቸውንም የተናገሩት ደግሞ አቅመ ደካማ የሆኑት አቶ ውበት መስፍን

Published in ማህበራዊ

አዳማ መስከረም 1/2010 የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችና ባለሀብቶች ችግረኞችን በመመገብና በማዝናናት የዘመን መለወጫ በዓልን ዛሬ በጋራ አከበሩ።

አመራሮቹና ባለሀብቶቹ  በዓሉን ያከበሩት አቅመ ደካማ አረጋዊያን ፣ የአካል ጉዳተኞች ፣ ወላጆቻውን ያጡ ህፃናትና የጎዳና ተዳዳሪዎች ጨምሮ ከሁለት ሺህ የሚበልጡ  ችግረኞችን በመጋበዝ ነው ፡፡ 

ለዚሁ ዝግጅት ባለሃብቶች ከ10 እስከ 70 ሺህ ብር ጥሬ ገንዘብ ሲዋጡ የአዳማ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ደግሞ ሁለት ሰንጋዎችን ለግሷል፡፡

በዚህም ችግሮቹን በመመገብና በ "ሴና ባንድ"  ታጅበው እንዲዝናኑ በመጋበዝ በዓሉን ከአመራሮቹና ከባለሀብቶቹ ጋር በጋራ ሆነው  በድምቀት አክብረዋል፡፡

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች ሀቢቤ በዚህ ወቅት "እርስ በርሳችን በመረዳዳት ችግራችንን እየፈታን መሄድ እንደሚቻል የከተማዋ ባለሃብቶች ያሳዩት በጎ ተግባር  ምስክር ነው" ብለዋል ።

በዓሉን ለአቅመ ደካሞችና ሌሎችም ችግረኞች  ፍቅር በማሳየት አብረው ማክበራቸው ደስታና ውስጣዊ እርካታ የሚሰጥ በመሆኑ ለወደፊቱም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል ።

የአዳማ ባለሃብቶች ቀደም ሲል በጉጂ ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን እርዳታ፣ ለከተማ የጎርፍ መከላከል ስራ ድጋፍና አሁን ደግሞ በዓሉን በማስመልከት ለችግረኞች  መስተንግዶ የሚውል ገንዘብና ቁሳቁስ በመለገስ  ላደረጉት አስተዋፅኦ ከንቲባዋ የምስጋና የምስክር ወረቀት አበርክተዋል ።

ከባለሃብቶች መካከል የአዳማ ቆርቆሮ ፋብሪካ ባለቤት አቶ አብዱልከሪም መሀመድ በአንድ በኩል የዜግነት ግዴታችንን ለመወጣት በሌላ በኩል ደግሞ ህዝባዊ ወገኝተኝነታችንን ለማረጋገጥ ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ባለሃብቱ" ከለገስነው ገንዘብ በላይ በአካል ተገኝተን ከተቸገሩ ወገኖቻችን ጋር አብረን ማሳለፋችንና ፍቅር ሰጥተን ፍቅር መቀበላችን ትልቅ እርካታ አግኝተንበታል "ብለዋል ። 

ባለሃብቱ ለበዓሉ ድግስ ካበረከቱት 69 ሺህ ብር ድጋፍ በተጨማሪ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 1ሺህ 200 ኩንታል በቆሎ ፣ ለአዳማ ከተማ ጎርፍ መከላከል ደግሞ  4ሚሊዮን ብር ጥሬ ገንዘብና ቁሳቁስ ለግሰዋል፡፡

እንዲሁም በ15 ሚሊየን ብር ወጪ የአንድ ክፍለ ከተማ ጽህፈት ቤት ሰርተው ለማስረከብ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ከከተማው አስተዳደር  የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

በግብዥው መስተንግዶ ከተሳተፉት መካከል የአካል ጉዳተኛው  አቶ አብዱጀባር ከድር በሰጡት አስተያየት "ከንቲባዋን ጨምሮ ትላልቅ ባለስልጣናትና ባለሃብቶች  በዓሉን አብረውን ማክበራቸው ከድግሱ በላይ የሞራል ስንቅ ሆኖናል" ብለዋል፡፡