አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452
Items filtered by date: Thursday, 03 August 2017

አዲስ አበባ ሀምሌ 27/2009 አሜሪካ በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ዕርዳታ የሚውል 137 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጓን አስታወቀች።

የገንዘብ ድጋፉ ለድርቅ ተጎጂ ዜጎች የምግብ እርዳታ፣ ለንጹህ መጠጥ ውሃና ለጤና አገልግሎቶች አቅርቦት እንደሚውል የአሜሪካ ኤምባሲ ለኢዜአ በላከው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

ዕርዳታው ሦስት ሚሊዮን ለሚጠጉ ዜጎች የሚውል 111 ሺ ሜትሪክ ቶን የምግብ እርዳታን ያካትታል።

ይህም የአሜሪካ መንግስት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ አቅርቦትን ለማሳደግና የምግብ እጥረት ተጎጂ ህጻናት የተመጣጠነ ምግብ ለማቅረብ ለሚያደርገው ጥረት እገዛ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የገለጸው መግለጫው፤ "እርዳታው በወሳኝ ወቅት የተደረገ ነው" በሚል ገልጾታል።

ተጎጂዎቹ አስቸኳይና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ካልተደረገላቸው ለአስከፊ ርሃብ፣ ለአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት መስፋፋትና መፈናቀል ችግሮች እንደሚጋለጡም አመልክቷል።

በሌላ ዜና አሜሪካ ሁለት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ዜጎቿ በድርቅና ግጭት ምክንያት ለምግብ ዋስትና እጦት ችግር ለተጋለጡባት ኬንያም የ33 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ይፋ አድርጋለች።

ዕርዳታው እኤአ 2017 አሜሪካ ለኢትዮጵያና ለኬንያ የለገሰችውን የሰብዓዊ ዕርዳታ መጠን ወደ 458 ሚሊዮን ዶላር ያደርሰዋል።

በሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀዳሚውን ስፍራ የያዘችው አሜሪካ፤ ለኢትዮጵያና ለኬንያ ከፍተኛ የሰብዓዊ ዕርዳታ ከሚለግሱ አገሮች መካከል አንዷ መሆንዋን መግለጫው አመልክቷል።

Published in ማህበራዊ

ባህር ዳር ሀምሌ 27/2009 በአማራ ክልል የአርሶአደሩን የምርጥ ዘር አቅርቦት እጥረት ለመፍታት በምርምር የተገኙ የሰብል ዝርያዎችን መልቀቁን የክልሉ ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት አስታወቀ። 

የኢኒስቲትዩቱ የሰብል ልማት ዳይሬክተር አቶ ፍቅረማርያም አሳርገው እንደገለጹት፣ አዲስ የተለቀቁት የሰብል ዝርያዎች ከስድስት እስከ ስምንት ዓመት ምርምር ሲደረግባቸው የቆዩ ናቸው።

በኢንስቲትዩቱ ስር ከሚገኙ አራት የግብርና ምርምር ማዕከላት የተለቀቁት የጤፍ፣ ማሽላ፣ ቦሎቄ ፣ አተር ፣ የምግብ ገብስና የነጭ አዝሙድ ዝርያዎች መሆናቸውንም ተናግረዋል።

አቶ ፍቅረማርያም እንዳሉት ዝርያዎቹ በአነስተኛ እርጥበት በሽታና ድርቅን ተቋቁመው ፈጥነው በመድረስ በሄክታር ከ22 እስከ 47 ኩንታል ምርት መስጠት ይችላሉ።

ከአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል የተለቀቀውና "ሕብር-1" የሚል ስያሜ የተሰጠው ነጭ ጤፍ በሄክታር 25 ኩንታል ምርት መስጠት የሚችል ነው።

ምርታማነቱ በአካባቢው ከሚገኘው ዝርያ በ11 ነጥብ 7 ኩንታል ብልጫ ያለው ሲሆን፣ ከሰቆጣ ዞን በስተቀር በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ላለው አየር ንብረት ተስማሚ መሆኑን አስረድተዋል።

ከስሪንቃ ግብርና ምርምር ማዕከል የተገኘውና "አለነ" የሚል ስያሜ የተሰጠው የማሽላ ዝርያም ምርታማነቱ በሄክታር 47 ነጥብ 2 ኩንታል መሆኑን አመልክተዋል።

ከአካባቢው ዝርያ በ19 ኩንታል ብልጫ እንዳለውና ፈጥኖ እንደሚደረስ የገለጹት አቶ ፍቅረማርያም፣ ዝርያው እንደቆቦ፣ ጨፋና ሌሎች ተመሳሳይ እርጥበት አጠር ለሆኑ ወረዳዎች ተስማሚ መሆኑን አስታውቀዋል።

"የዋግ-ነሽ" የሚል ስያሜ የተሰጠውና ከሰቆጣ ግብርና ምርምር ማዕከል የተለቀቀው የአተር ዝርያም በሄክታር 22 ነጥብ 9 ኩንታል ምርት መስጠት እንደሚችል ተመልክቷል።

አሁን በአካባቢው ካለው የአተር ዝርያ በሄክታር በ10 ነጥብ 3 ኩንታል ብልጫ ያለው ሲሆን ለሰሜን ወሎ፣ ለዋግ-ህምራና ተመሳሳይ የአየር ፀባይ ላላቸው አካባቢዎች ተስማሚ መሆኑን አስረድተዋል።

በሁሉም ገብስ አብቃይ በሆኑ የክልሉ ደጋማ ወረዳዎች ተስማሚ እንደሆነ የተነገረለት "ደባርቅ-1" የተባለው አዲሱ የገብስ ዝርያም ኢኒስቲትዩት በምርምር ካገኛቸው የሚጠቀስ ነው። 

በሄክታር ከ22 እስከ 25 ኩንታል ምርት መስጠት የሚችሉ ሁለት አዲስ የነጭ አዝሙድ ዝርያዎችም ከጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል መገኘታቸውንም ጠቁመዋል።

አቶ ፍቅረማርያም እንዳሉት፣ በብሔራዊ ዝርያ አጽዳቂ ኮሚቴ ፀድቀው የተለቀቁት የሰብል ዝርያዎችን በተያዘው የመኽር እርሻ በአርሶአደሩ ማሳ ላይ በማላመድ ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ ዘራቸውን የማሰራጨት ሥራ ይጀመራል።

በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ኢንስቲትዩቱ 250 የሰብል ዝርያዎች በምርምር በማውጣትና በማላመድ የአርሶደሩን የዘር አቅርቦት ዕጥረት ለማቃለል አቅዶ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ኢንስቲትዩቱ በስሩ በሚገኙ የምርምር ማዕከላት 69 አዳዲስ የሰብል ዝርያዎችን በምርምር በማውጣት ወደአርሶአደሩ እንዲገቡ ማድረጉን የዘገበው ኢዜአ ነው።

አዲስ አበባ ሀምሌ 27/2009 ፓርቲዎቹ አገር አቀፍ እና ክልላዊ ፓርቲ ለመመስረት መሟላት ባለባቸው ጉዳዮች ላይ እየተደራደሩ ነው።

በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 573/2000 ላይ የጀመሩትን ዝግ ድርድር ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ያካሄዱት አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው።

ፓርቲዎቹ ከአዋጁ አንቀፅ አንድ እስከ 31 የተዘረዘሩት የፖለቲካ ፓርቲዎች አመሰራረት፣ ምዝገባና ሰነዶች፣ የአባላት መብትና ግዴታን በተመለከቱና ይሻሻሉ ባሏቸው አንቀፆች ላይ እየተደራደሩ ነው።

በዛሬ ድርድራቸውም አዲስ ፓርቲ ለመመስረት በሚያስፈልጉት የመስራች አባላት ቁጥር ፣ የሰነድ አያያዝና ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ስለማቋቋምና በመንግስት የሚደረግን የፋይናንስ ድጋፍ ጨምሮ በበርካታ ጉዳዮች ላይም ድርድር አካሂደዋል።

የድርድሩ የሚዲያ ኮሚቴ ሰብሳቢና የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ህብረት /ኢዴህ/ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ገብሩ በርሄ ለኢዜአ እንደገለፁት አገር አቀፍና ክልላዊ ፓርቲ ለመመስረት መሟላት ያለባቸውን ጉዳዮች ለማሻሻል ነው ድርድሩ እየተካሄደ ያለው።

ፓርቲዎቹ በምዝገባ አዋጁ አንድ አገር አቀፍ ፓርቲ ለመመስረት 1 ሺህ 500 መስራች አባላት ያስፈልጋሉ በሚለው አንቀፅ አምስት፤ የአባላቱ ቁጥር 2 ሺህ 500፣ 3 ሺህ እና 5 ሺህ ሊሆን ይገባል በሚሉ ሃሳቦች ድርድር አካሂደዋል።

በምዝገባ አዋጁ አንቀፅ 6 የክልል የፖለቲካ ፓርቲ ለመመስረት 750 መስራች አባላት ያስፈልጋል የሚለውን ወደ 1 ሺህ 500 ለማሳደግም እንዲሁ።

አገር አቀፍ ፓርቲ ለመመስረት 3 ሺህ ፣ የክልል የፖለቲካ ፓርቲ ለመመስረት ደግሞ 1 ሺህ 500 መስራች አባላት ያስፈልጋሉ በሚል አንቀፆቹ እንዲሻሻሉ አብዛኞቹ ፓርቲዎች ተመሳሳይ አቋም መያዛቸውን አቶ ገብሩ ገልፀዋል።

በአዋጁ “ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ የፖለቲካ ስራውን ለማካሄድ በአገር ውስጥ በየትኛውም ቦታ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ሊያቋቁም ይችላል” የሚለውን አንቀጽ 17 እንዲሻሻልም ተስማምተዋል ነው ያሉት።

በዚሁ መሰረት አንድ የሚመሰረት አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤቱን ጨምሮ በፌዴራል ደረጃ ሁለት እና በክልሎች አራት  በድምሩ 6 ጽህፈት ቤቶች ይኖሩታል በሚል የቀረበው ሃሳብ የተባበረ የድምፅ ድጋፍ እንዳለውም ተናግረዋል።

በምዝገባ አዋጁ መንግስት ለፖለቲካ ፓርቲዎች ድጋፍ የሚያደርግበት አንቀፅ ይካተት የሚል ሃሳብም በድርድሩ ተነስቷል።

ፓርቲዎቹ ይሻሻሉና አዲስ ይካተቱ ያሏቸውን አንቀፆች ጨምሮ በአዋጁ ከ1ኛ እስከ 31ኛ አንቀፆች እያካሄዱት ባለው ድርድር ሙሉ በሙሉ ከስምምነት ደርሰው ለመቋጨት ለመጪው ማክሰኞ ቀጠሮ መያዛቸውን አቶ ገብሩ ተናግረዋል።

ፓርቲዎቹ ከሁለት ሣምንት በፊት ባካሄዱት ውይይት ለድርድር የፀደቁ 12 አጀንዳዎችን ቅደም ተከተል የወሰኑ ሲሆን አጠቃላይ ድርድሩን በ90 ቀናት ለማጠናቀቅም ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ገዥው ፓርቲ /ኢህአዴግ/ የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)፣ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ፣ አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት)፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ህብረት (ኢዴህ) እና የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ንቅናቄ /ኢዴአን/ ጨምሮ 17 ፓርቲዎች ናቸው በድርድር ላይ የሚገኙት።   

Published in ፖለቲካ

አዲስ አበባ ሀምሌ 27/2009 ዝናብ ሰጪ የሚቲዎሮሎጂ ገፅታዎች በሚቀጥሉት አስር ቀናት በክረምት ዝናብ ተጠቃሚ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ተነበየ።     

ሊጠናከሩ ከሚችሉ የደመና ክምችቶች ቅፅበታዊ ጎርፍና አልፎ አልፎም በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ሊከሰት እንደሚችልም ኤጀንሲው ገልጿል።   

በዚህ መሰረት ከኦሮሚያ ክልል ምሥራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ጅማ፣ ኢሉአባቦራ፣ ምዕራብና ሰሜን ሸዋ፣ የአርሲና የባሌ ዞኖች፣ አዲስ አበባ፣ የጋምቤላና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች፣ ከአማራ ክልል ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ የባህዳር ዙሪያ፣ አዊ ዞን፣ የሰሜንና የደቡብ ጎንደር ዞኖች መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚያገኙ ይጠበቃል።   

በተመሳሳይ የትግራይ ዞኖች፣ ከደቡብ ክልል ደግሞ ሀዲያና ጉራጌ ዞኖች፣ የከፋና ቤንች ማጂ፣ የወላይታ፣ ሲዳማና ጌዲዮ ዞኖች በአብዛኛው መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ የሚያገኙ ይሆናል።   

ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብና ምሥራቅ ሐረርጌ፣ ከአፋር ክልል ደግሞ ዞን 3 እና ዞን 5፣ ከሶማሌ ክልል የጅግጅጋና ሲቲ ዞኖች፣ ድሬዳዋና ሐረሪ በአብዛኛው ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ እንደሚያገኙም ኤጀንሲው ጠቁሟል። 

በሌላ በኩል የደቡብ ኦሞና አጎራባች የሰገን ህዝቦች ዞኖች በአብዛኛው ደረቃማ የአየር ሁኔታ እያመዘነባቸው አነስተኛ ዝናብ ያገኛሉ ብሏል። 

በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምቱ ዝናብ በመጠንና በስርጭት ዝናብ በሚያገኙ ተፋሰሶች ላይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ኤጀንሲ ያስታወቀው።  

በዚህም በአብዛኛው ተከዜ፣ አባይ፣ ባሮአኮቦ፣ ኦሞጊቤ፣ የላይኛውና መካከለኛው አዋሽና ስምጥ ሸለቆ፣ የላይኛው ገናሌዳዋና ዋቢ ሸበሌ፣ ጥቂት የላይኛው አፋር ደናከል ተፋሰሶችም መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ይኖራቸዋል።

የታችኛው አዋሽ፣ ስምጥ ሸለቆና ባሮአኮቦና የመካከለኛው ዋቢ ሸበሌ ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል ሲል ኤጀንሲው ለኢዜአ በላከው መግለጫ አመልክቷል። 

የዝናብ ስርጭታቸው ከመደበኛ በላይና ከባድ ዝናብ በሚጠበቅባቸው አካባቢዎች የወንዞች ሙላት እንዲሁም የጎርፍና የመሬት መንሸራተት ሊከሰት ስለሚችል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም ኤጀንሲው አሳስቧል። 

ወሩ በአብዛኛው የመኸር አብቃይ አካባቢዎች ከእርጥበታማ እስከ በጣም እርጥበታማ የአየር ሁኔታ እንደሚያመዝን ያብራራው ኤጀንሲው ይህም ለተያዘው የግብርና ሥራ ገንቢ ሚና እንደሚኖረው ነው የገለጸው።  

 

 

 

Published in አካባቢ

አዲስ አበባ ሀምሌ 27/2009 ኢትዮጵያ በአፍሪካ በግብርና ልማት ቀዳሚና ፈር ቀዳጅ መሆኗን አዲሷ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ጸሃፊ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አዲሷን የኮሚሽኑን ዋና ጸሓፊ ቬራ ሶንግዌን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው በአህጉሪቷ ዕድገት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

ዋና ጸሓፊዋ ከውይይቱ በኋላ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፤ በወቅታዊ ዓለም ዓቀፋዊ ሁኔታ ውስጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት ምን እንደሚመስል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህም ኢትዮጵያ በግብርና ልማት ያካበተችውን ልምድ ለሌሎች የአፍሪካ አገሮች በምታካፍልበት ስልት ላይም መወያየታቸውን ነው የገለጹት።

ዋና ጸሓፊዋ ኢትዮጵያ የአየር ንብርት ለውጥንም ለመከላከል በዓለም ቀዳሚውን ስፍራ ይዛ እየሰራች መሆኑንም ገልጸዋል።

የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን እንደአንጋፋነቱ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተባብሮ መሥራቱን እንደሚቀጥለ የገለጹት ዋና ጸሓፊዋ ''በአህጉሪቷ ኢኮኖሚ ሽግግርና በኢንዱስትሪ ዕድገት ረገድ በጋራ እንሰራለን'' ብለዋል።

ውይይቱን የተከታተሉት በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽንና በአፍሪካ ሕብረት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ዋህድ በላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ''የኮሚሽኑ ስራ ውጤታማ እየሆነ ስለ መምጣቱ ኢትዮጵያ እውቅና ትሰጣለች'' ማለታቸውን ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ ለአህጉሪቷ ውህደት ፣ ለንግድና ለመሠረተ ልማት መስፋፋት እንዲሁም ለጸረ ድህነት ስራዎች እያደረገ ያለውን ተግባር ውጤታማ መሆኑን "የኢትዮጵያ መንግስት ዕምነት አለው" ማለታቸውንም ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ እየተመዘገበ ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ዙሪያ ያወጣቸው ጥናቶችና ሪፖርቶች ለኢትዮጵያ በጎ ውጤት ያሳዩ መሆናቸውንም  ገልጸዋል ነው ያሉት።

በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኘውና የአፍሪካ ሕብረት የተመሠረተበት 'የአፍሪካ አዳራሽ' ተብሎ የሚታወቀውን ህንጻ በ57 ሚሊዮን ዶላር ለማደስ መታቀዱን ዋና ጸሓፊዋ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩም ፕሮጀክቱ ትልቅ መሆኑን ገልጸው፤ ኢትዮጵያም ለውሳኔው ትልቅ ምስጋና ታቀርባለች ማለታቸውንም ጨምረው ተናግረዋል።

ዋና ጸሓፊዋ ኮሚሽኑ የሰራተኞቹ መብት የሚከበርበት ስምምነት እንዲፈረም ጠይቀው በጠቅላይ ሚኒስትሩ አዎንታዊ መልስ ማግኘታቸውንም አምባሳደር ዋህድ አመልክተዋል።

Published in ኢኮኖሚ

አዲስ አበባ ሀምሌ 27/2009 ኢትዮጵያ ከኬንያና ጅቡቲ ጋር የህዝብ ትራንስፖርት መጀመር የሚያስችሏትን ቅድመ ዝግጅቶች በማጠናቀቅ ላይ መሆኗን የትራንስፖርት ባለስልጣን ገለጸ።

የአፍሪካ ኅብረት በአጀንዳ 2063 ካስቀመጣቸው ግቦች መካከል አፍሪካን እርስ በእርስ በማስተሳሰር የኢኮኖሚና ማህበራዊ ግንኙነቶችን ማሳለጥ ነው።

አፍሪካን በትራንስፖርት በማዋሃድ ሰዎች ወደ ማንኛውም የኅብረቱ አባል አገራት በነጻነት እንዲንቀሳቀሱና የእቃዎች፣ የአገልግሎትና  የገንዘብ ዝውውር እንዲኖር ማድረግም እንዲሁ።

በ2023 በአፍሪካ አገራት መካከል የሚኖረው ንግድ በተለይም እሴት በጨመሩ የግብርና ምርቶች በሶስት እጥፍ ይጨምራል፤ ለዚህም አፍሪካን በየብስ ትራንስፖርት ማስተሳሰር ወሳኝ ነው።

በዚሁ መሰረት ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር በመጋቢት 2009 ዓ.ም ድንበር ዘለል የየብስ ትራንስፖርት ጀምራለች።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ኃይለማርያም ለኢዜአ እንደገለጹት አገሪቱ ከሱዳን፣ ጅቡቲና ሱዳን ጋር ያላትን የጭነት ትራንስፖርት ግንኙነት ወደ ህዝብ ለማምጣት አየሰራች ነው።

መሰል ትስስሮችን ከጅቡቲና ኬንያ ጋር ለማድረግም ከጅቡቲ ጋር ስምምነቶች መደረጋቸውን ተናግረዋል።

ከአዲስ አበባ ጅቡቲ የህዝብ ትራንስፖርት ለመጀመር የትኬት መሸጫ ቢሮዎች፣ ከሁለቱም አገራት የሚያስፈልጉ አውቶቡሶችና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ነው የገለፁት።

ቀደም ሲል የየብስ ትራንስፖርት ለእቃ ማጓጓዣ ይውል የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአውቶቡስ ሱዳን ገብቶ ማደር ቀላል መሆኑን ነው የተናገሩት አቶ ካሳሁን።

አገሪቱ በ2009 ዓ.ም ካጓጓዘችው 15 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የወጪና ገቢ እቃ 99 በመቶ የሚሆነው በጅቡቲ፣ 100 ሺህ ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ ደሞ በሱዳን በኩል ገብቷል።

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቱ አገራቱ ድንበር ድረስ ተጉዞ ሌላ ትራንስፖርት መያዝን አስቀርቶ የአገራቱን ህዝቦች ቀጥታ የሚፈልጉበት አገር እንዲደርሱ ማድረጉ አዲስ ያደርገዋል።

 

Published in ኢኮኖሚ

ባህር ዳር ሀምሌ27/2009 በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ነጋዴዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።

የፌዴራልና የክልሎች የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ጥምረት 22ኛ መደበኛ የጋራ ጉባኤ ዛሬ በባህርዳር ከተማ ተጀምሯል።

 

ኮሚሽነር አሊ ሱሌማን በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት የሙስና ወንጀልን በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ ለመከላከልና ተግባሩንም ከምንጩ ለማድረቅ የሁሉንም አካላት ርብርብና ተሳትፎ ይጠይቃል።

ህብረተሰቡን እያማረሩ የሚገኙ የመልካም አስተዳደርና የሙስና ችግሮችን አስቀድሞ የመከላከልና የህግ ማስከበር ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በቅርቡም መንግስት ሙሰኞችን ለህግ ለማቅረብ በጀመረው የተጠናከረ እንቅስቃሴ ከ40 በላይ የስራ ኃላፊዎችና ነጋዴዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ለአብነት ጠቅሰዋል።

ይሄው ተግባር በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮሚሽነር አሊ ጠቁመው ክልሎችም የትግሉን አቅጣጫ እንዲከተሉ አስገንዝበዋል።

''የሚስተዋሉ የኪራይ ሰብሳቢነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቀነስ የፌዴራልና የክልል የፀረ-ሙስና ተቋማት ህዝቡን የትግሉ አጋር በማድረግ የመሪነት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል'' ብለዋል።

ተቋማቱ ከፍተኛ የልማት ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በመንግስት ግዥ፤ ሽያጭና በመሬት አስተዳደር ላይ ባከናወኗቸው ስራዎች የመንግስትና የህዝብ ሃብትን መታደግ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡

የጉባኤው ተሳታፊዎችም ያጋጠሙ ችግሮችን ለይቶ በማረምና በቀጣይ የፀረ-ሙስና ትግል ዕቅዶችን ከግብ ለማድረስ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን እንዲያስቀምጡ ኮሚሽነር አሊ አሳስበዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በበኩላችው ሀገሪቱ የጀመረችውን የህዳሴ ጉዞ ከዳር ለማድረስ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ሙስናና ብልሹ አሰራርን አምርሮ መታገል ያስፈልጋል።

 

''የክልሉ መንግስትም የስነ-ምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን ከማቋቋም ጀምሮ የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ በማጥናት ሶስት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችን ከፍቶ የፀረ ሙስና ትግሉ ህዝባዊ መሰረት እንዲይዝ እያደረገ ይገኛል '' ብለዋል።

''በአንድ ተቋም ጥረት ብቻ ሙስናን መከላከል አይቻልም'' ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ በየደረጃው ያሉ ተቋማትና ህብረተሰቡ በባለቤትነት ስሜት የተቀናጀ ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ዛሬ የተጀመረውና ለሶስት ቀናት በሚቆየው የጥምረቱ የጋራ ጉባኤ ላይ የፌዴራልና የሁሉም ክልሎች የፀረሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነሮችና ዳይሬክተሮች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

በቆይታቸውም በ2009 በጀት ዓመት ሀገር አቀፍ የፀረ ሙስና እንቅስቃሴና የመልካም አስተዳደር ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግ  ታውቋል፡፡

የጥምረቱ መደበኛ ጉባኤ በየስድስት ወሩ ይካሄዳል፡፡

Published in ማህበራዊ

ሐረር ሀምሌ 27/2009 በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ155 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ስዩም ደገፉ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በተጠናቀቀው የ2009 በጀት ዓመት በዞኑ 177 የትራፊክ አደጋዎች ደርሰዋል።

በእዚህም የ155 ሰዎች ሕይወት ሲጠፋ በ480 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል። ከእዚህ በተጨማሪ ከ8 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ንብረትም መውደሙን ነው የገለጹት።

እንደ ምክትል ኮማንደር ስዩም ገለጻ ፣ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር፣ የአካባቢው የመሬት አቀማመጥ ጠመዝማዛና ቁልቁለታማ መሆን ፣ የአሽከርካሪ ብቃት ማነስ ለአደጋዎቹ መከሰት በዋናነት የሚጠቀሱ ምክንያቶች ናቸው።

" ሜታ፣ ቀርሳ፣ ጎሮጉቱ፣ ደደር ወረዳዎችና የአወዳይ ከተማ አደጋውን በማስተናገድ በኩል ቀዳሚውን ሥፍራ መያዘቸውንም ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ የደረሰው የትራፊክ አደጋ ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በሁለት በመቶ ቢቀንስም የተመዘገበው ሞት ፣ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት በስምንት በመቶ መጨመሩን ኮማንድር ስዩም አስረድተዋል።

በዓመቱ አደጋውን ለመቀነስና ለመቆጣጠር በተደረገ ጥረት ሃያ ሰዎች በሐረማያ አካባቢና ኮምቦልቻ ከተማ ህገወጥ በሆነ መንጃ ፍቃድ እንዲሁም ከ200 በላይ ሰዎች መንጃ ፈቃድ ሳይኖራቸው ሲያሽከረክሩ ተይዘዋል።

ከእዚህ በተጨማሪ ያለእረፍት የሚያሽከረክሩ፣ የትራፊክ ህግና ደንብን የማያከብሩ አንዲሁም የተሽከርካሪ የቴክኒክ ምርመራ ሳያሟሉ  ሲያሽከረክሩ የነበሩ ሰዎች መያዛቸውን ገልጸዋል።     

ምክትል ኮማንደር ስዩም እንዳሉት  15 ሺህ በሚጠጉ ደንብ ተላላፊ አሽከርካሪዎች ላይ በተመሰረው ክስ ሰባት ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ  ለመንግስት በቅጣት ገቢ ተደርጓል።

Published in ማህበራዊ
Thursday, 03 August 2017 21:39

ሀይል ያጡ የሀይል መሪዎች!

 መብራህቱ ይበልህ / ኢዜአ መቀሌ/

ገድላቸውና አሁን ያሉበት  ሁኔታ ርቀቱ በጣም ይሰፋል።ወርቃማ ታሪካቸውና የአሁኑ ኑሮአቸው ፍፁም አይጣጣምም።እሳትን  አጥፍተው  ሞትን በጀግንነታቸው ድል አድርገው ለአሁኑ ልማትና ለህዝቦች እኩል ተጠቃሚነት አድርሰውናል።

 የእነሱ የህይወት ውለታና  ታሪክ የሚያስታውስ  ትውልድ አለ ወይ?  በየግላችን  ልንመልሰው  የሚገባ የአደራ ተረካቢ ትውልድ ጥያቄ በመሆኑ እኔ መልስ አልሰጥበትም።

 እነሱ እኩል ተጠቃሚ ስለመሆናቸው ግን ጥያቄም ጥርጣሬም ያጭራል።ያም ሆነ ይህ ግን ባለታሪኮቹ በታሪካቸው ያልደመቁበት ጊዜ  ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም።

 ታጋይ ታደሉ አይናለም ለትግሉ ሲባል ውድ ዋጋ ከከፈለ ቤተሰብ የፈለቀች ጀግና ናት ። ሁለት ወንድሞቿ በጀግንነት እየተዋጉ ተሰውተዋል ። እሷም ከባድ የአካል ጉዳት አስተናግዳለች ። የትግል ሂደቱና የተገኘው ውጤት ስታየው ግን ኩራት እንጂ  ለክቡር ዓላማ የተከፈለ ክቡር መስዋእትነት በመሆኑ የሚቆጫት ነገር የለም ።

ታጋይ ታደሉ አይናለም የህወሓትናብአዴን ታጋዮች በጥምርታ  ’’ዘመቻ ሰላም’’ የሚል ስያሜ የተሰጠው የቆቦ ግንባር ውግያ ድረስ የሀይል መሪ ነበረች።132 የሚሆኑ  ጀግኖችታጋዮች  ትመራነበር።ታዋጋለች።ፍልሚያው  መርታም ለድል አብቅታለች።ቆቦ ላይ በ1982 ዓም  እስከ ተካሄደው ውግያድረስ ታጋይ ታደሉ የየእለቱ ተልእኮዋን በድል ተወጥተዋለች።

ታጋይ ታደሉ የምትመራው የህወሓት ሀይልና ብአዴን ተጨማሪ አንድ  ሀይልሻምበልጣምራ ፈጥረው  ቆቦ ከተማ የሰፈረው የጠላት ሀይል ለመደምሰስ በቅድሚያ ከወልድያየሚያገናኝ መስመር መቆረጥ ነበረበትና ጎብየና ሮቢት የሰፈረውንየደርግ ወታደር ድል አደረጉት።የህወሓትና ኢህደን/ብአዴን/ ታጋዮች በጋራ ተዋጉ፣ በጋራ ተሰዉ። በጋራ ደግሞ አንድ ጉድጓድ ውሰጥ መቀበራቸውን ታጋይ ታደሉ  ታወጋናለች።

 ሁለቱም ከተሞች ነፃ ከወጡ በኋላስ ?ፊታቸው ወደ  ቆቦ ከተማ አዞሩ።ቆቦ ከተማ  ላይ የከተመው ግዙፍ የደርግ  ሰራዊት  ለመደምሰስ ሌላ  ግብግብ ገጠሙ። ያኔ ነበር ታጋይ ታደሉ ከሀይል መሪነትዋ ፣ከአዋጊነትዋ ሊያሰናክላት የቻለ ከባድ ጉዳት የደረሰባት።ከጉልበትዋ በላይ ባጋጠማት ከበድ የመቁሰል አደጋ አንድ እግሯ መቆረጡን ትናገራለች።ያኔ የነበራት ቁመናና ጀግንነት  ዛሬ ላይ በእድሜ ምንክንያት ቢደበዝዝም  ወኔዋ ግን አሁንም ድረስ ከውስጥ  አልጠፋም።

 እንደያኔው የጠላትን ሀይል ለማዳከም ከተራራ ወደ ተራራ በፍጥነት ለመሻገር ባትችልም  ሰው ሰራሽ የአካል ድጋፍ ተጠቅማ በትጋትትሰራለች።ድህነትን ለመዋጋት አሁንም  በቃኝ አላለችም።እሷን ጨምሮ ሌሎች በጦርነቱ አካላቸው የጎደሉ አራት ሴት ታጋዮች በጋራ ተሰብስበው  በመቐለ ከተማ ልዩ ስሙ አዲሓቂ ተብሎ በሚጠራ የገበያ ማእከል የክፍያ መጸዳጃ ቤት አገልግሎት ይሰራሉ።

 ታጋይ ታደሉ ወደ ትጥቅ ትግል ለመቀላቀል ምክንያት የሆናት ተጠይቃ ’’ በእርግጥ ሰፊ የመወሰንእውቀት አልነበረኝም።በተወለድኩበት አካባቢ የሴቶች ጭቆና ስመለከት ልቤ ይነካ ነበር።አርሶ አደሩምየመሬቱ ተጠቃሚ አልነበረም።የከተማ ሰውም ቢሆን ምንም ስራ አልነበረውም።ይህን ሁሉ ሳወጣ ሳወርድ ወደ ትጥቅ ትግሉ በ1976ዓም እንድቀላቀል ገፋፋኝና ሄድኩ።

በሂደት ግን ሰፊየፖለቲካ ትምህርት እየተሰጠን በትግሉ ፀንተን ለመሄድ አስችሎናል’’ትላለች  ።

 ከትጥቅ ትግሉ ምን ተጠቀማችሁ? የሚል ጥያቄ አስከተልኩባት። ታጋይ ታደሉ አይናለም’’’’በእርግጥ ህዝቡ ተጠቅሟል።በግሌ ግን የክፍያ መጸዳጃቤትአገልግሎት እየሰጠሁ ኑሮየን እመራሉሁ።በእርግጥ የትምህርት ደረጃችን ዝቅተኛ በመሆኑ ነው ወደ እዚሁ  ስራ የገባነው።

አለመማራችን ጎድቶናል።ቢሆንም  ይሀን ስራ አምነንና ወደን ነው የገባንበት’’ ትላለች።

 የትግራይ ህዝብ ከሌላው ህዝብ እላፊ ተጠቃሚ እንደሆነ የሚናገሩ ሰዎች እንደምትሰማ  የምትገልፀው ታጋይ ታደሉ፣ የትጥቅ ትግሉ መነሻና መድረሻ የህዝቦች እኩል ተጠቀሚነትን ማረጋገጥ ነው ትላለች።

 ከሌላው  ህዝብ በተለየ መንገድ ተጠቃሚ ብንሆን ኑሮ እኛ እዚህ ስራ ባልወደቅን  ነበር ። ትግላችን ለእኩል ተጠቃሚነት በመሆኑ ግን አሁንም በቀሪ አካላችን እየሰራን ኑሮአችንን እንመራለን የሚለውን የታጋይ ታደሉ ምላሽ ነው።

 አሁንም ድረስ ብዙ ህዝብ ያላወቀው ነገር ቢኖር ከኤርትራ  በሚያዋስነው ድንበር አካባቢ የሚገኝ ህዝባችን አንድ ቀንም  እረፍት አላገኘም።ሉአላዊነቱን ላለማስደፈር ከሻዕብያ ጋር እየተፋለመ ይገኛል። ሌላው  የኢትዮጰያ ህዝብ ያገኘው የተረጋጋ ሰላም እንኳን የትግራይ ህዝብ ማግኘት እንዳልቻለ  ትናገራለች።

 ሰሜን ወሎ መርሳ ከተማ አቅራቢያ በ1982 ዓም ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰበት ሌላው ታጋይ ገብረመድህን መረሳ የታጋይ ታደሉ ሀሳብን ያጠናክራል። ታጋይ ገብረመድህም  መቐለ ከተማ ውስጥ አዲ ሀቂ የገበያ ማእከል  በተጎሳቆለ  ሰፈር  ውስጥ  ትንሽ  በቆርቆሮ በተሰራ  ሱቅ  ሶፍት፣ከረሜላ፣ማስቲካና ሌሎች ትናንሽ የሸቀጥ እቃዎችን እየሸጠ

ይተዳደራል።ምን ያህል ገቢ ያገኛል ቢባል ግን እግዝአብሄር ይወቀው።

 ፅናቱ ግን አሁንም ድረስ አልደበዘዘም።የድሮ ጀግንነቱና አሁን የሚኖርበት ስፍራ ግን ለኔ የሚጣጣም አልሆነልኝም።ያኔው ሀይል መሪ አሁን ግን በኑረው የተጎሳቆለ ታጋይ።

 ታጋይ ገብረመድህን መርሳ ላይ በነበረው ከባድ ውግያ የአካባቢው አርሶ አደሮችን አሁንም ድረስ አይረሳቸውም።እነሱ ከጎናችን ሆነው አይዛችሁ ባይሉን ኑሮ ወደ ፊት መቀጠል አይችልም ነበር።ይባስ ብሎም ትግሉ ወደ ኋላ የማንሸራተት አደጋ ያጋጥመው ነበር ይላል።

 ታጋይ ገብረመድህን የደርግ መንግስት ለመደምሰስ  የከፈለው መስዋእትነትና አሁን ባለበት ሁኔታቅሬታ ይሰማው እንደሆነ  ጠይቄው ነበር።እንዲህም ይላል ።’’ምንም  ቅሬታ  የለኝም።እንዲያውም የትግላችን ውጤት የልማት ፍሬ አፍርቷል ባይ ነው ። ህብረተሰቡ  ተጠቃሚ ሆኗል የሚል አስተሳሰብ አለኝ።በእርግጥ ድህነታችን ባይወገድም ከፍተኛ ለውጥ መመዝገቡ ግን አምናለሁ’’ ይላል።

 ታጋዩ ከፍተኛ ለውጥ መመዝገቡን የሚያነፃፅርበት መንገድ አለው።በ1977ዓም ከአንድ የህወሓት ሻምበል ጋር ተቀላቅሎ ሌሎችን ለመደገፍ ወደ ምእራብ ኢትዮጵያ በተንቀሰቀሰበትወቅት ያየውን ሁሉ አሁንም ድረስ ከአእምረው አይጠፋም።

 እንዲህ በማለትም ትዝታው ያጋራል።’’ በእርግጥ እኔ ትግራይ ነው ያደኩት።መጥፎም ይሁን ጥሩ ልብስ ነበረኝ።ምእራብ ኢትዮጵያ በተንቀሳቀስኩበት ጊዜ ጫካ ውስጥ የሚኖሩ ልብስ የሌላቸው ህዝቦች በማየቴ በጣም ደነገጥኩ።አሁን ግን ሁኔታው ተለውጦና ታሪክ ሆኖ ስመለከት ደስታ ይሰማኛል፡፡መማራቸውን ሳይ ውስጤ በሀሴት ይሞላል’’ ይላል ታጋይ ገብረመድህን፡፡