Items filtered by date: Sunday, 02 April 2017

ሃዋሳ መጋቢት 24/2009 " ታላቁ የህዳሴ ግድብ የአስተሳሰብ ለውጥ ያመጣና አንድነት እያጠናከረ የሚገኝ የአዲስቷ ኢትዮጵያ የጋራ ምልክት ነው" ሲሉ  የደቡብ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳደር  አቶ ደሴ ዳልኬ ገለጹ፡፡

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠበት ስድስተኛ ዓመት በክልል ደረጃ ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ በድምቀት ተከብሯል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በበዓሉ ላይ  እንዳሉት የክልሉ ህዝብ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚያደርገው  ድጋፍና ተሳትፎ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

" ለጋራ ተጠቃሚነት ሲባል መስዋዕትነት የሚከፍልና ታሪክ የሚሠራ ትውልድ እየተፈጠረ ነው " ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ዋንጫው በክልሉ ከገባበት ቀን  ጀምሮ ህዝቡ እያደረገ ያለው ከፍተኛ ድጋፍ የሚበረታታ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

" ታላቁ የህዳሴው ግድብ  ግንባታ የአይቻልም አስተሳሰብን  የሰበረና አንድነት እያጠናከረ የሚገኝ የአዲስቷ ኢትዮጵያ የጋራ ምልክት ነው" ብለዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ደሴ ህዝቡ ለግድቡ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

የደቡብ ህዝቦች ክልል የታላቁ ህዳሴ ግድብ  ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት  ዳይሬክተር አቶ ፋሲካ ጌታቸው በበኩላቸው  ዋንጫው በክልሉ መዘዋወር ከጀመረ ወዲህ 522 ሚሊየን  ብር መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡

የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በክልሉ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉንም ጠቅሰዋል፡፡

የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አስራት ጤራ ዋንጫው በዞኑ ቆይታ ባደረገበት ባለፉት 10 ቀናት  202 ሚሊየን ብር ድጋፍ መደረጉን ጠቁመው  ባለፉት ዓመታትም ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ህዝቡ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡

በንግድ ስራ የተሰማሩት የሶዶ ከተማ ነዋሪው አቶ ያዕቆብ አልታዬ " በራሳችን አቅም የምንሰራው የግድቡ ግንባታ ከግማሽ በላይ ተጠናቆ ስድስተኛ ዓመቱን ስናከብር ታላቅ ደስታ ይሰማኛል" ብለዋል፡፡

ግንባታው ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ ከሶስት ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ባድረጋቸውን የተናገሩት  አቶ ያዕቆብ ዋንጫው ዞኑ በገባበት ውቅትም  በተጨማሪ ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ መደገፋቸውን ጠቅሰዋል፡፡

አቶ ያዕቆብ እንዳሉት የግድቡ ግንባታ እስኪ ጠናቅ ድጋፋቸውን አጠናክረው  ይቀጥላሉ፡፡

በዓሉ የክልልና የዞኑ  ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ፣ የአካባቢው ህብረተሰብና የአጎራባች ዞን አመራሮች በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡

Published in ኢኮኖሚ

ግራር ጃርሶ  መጋቢት 24/2009  በአሁኑ ወቅት የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በኑሯቸው ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት መቻላቸውን በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ግራር ጃርሶ ወረዳ የሚኖሩ ሴት አርሶ አደሮች ገለጹ።

ሴት አርሶ አደሮቹ ያካበቱት ሃብትና የፈጠሩት ኢኮኖሚያዊ አቅም በራስ መተማመናቸውና የመደራደር አቅማቸውን እንዳጎለበተው መገንዘባቸውን በስፍራው ተገኝተው ጉብኝት ያደረጉ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ አመራር አባላት ተናግረዋል።

የኢህአዴግ (የኦህዴድ፣ ብአዴን፣ ህወሃትና ደኢህዴን) ሴቶች ሊግ አመራር አባላት በግራር ጃርሶ ወረዳ የሚገኙ ግንባር ቀደም የሆኑና ምርጥ ተሞክሮ ያላቸውን ሴት አርሶ አደሮች ጎብኝተዋል።

ግንባር ቀደም ሴት አርሶ አደሮቹ ለጎብኚዎቹ እንደገለጹት፤ በአገሪቷ ተግባራዊ እየሆነ ባለው የገጠር ልማት ፖሊሲ ተጠቀሚ ለመሆን ችለዋል። የሚሰጣቸውን የግብርና ፓኬጅ ትምህርቶች በሚገባ በመከታተልና ተግባራዊ በማድረግ በኑሯቸው ላይ ተጨባጭ ለውጥ አምጥተዋል።

ወይዘሮ ዓይናለም ጥላሁን እንደሚሉት፤ የግብርና ባለሙያዎች በሚሰጧቸው ምክር አማካኝነት ስራቸውን በማሻሻላቸው ቀድሞ ከሚያመርቱት የበለጠ ማምረት ችለዋል። ከዕለት ጉርስ ባለፈም ለገበያ በማቅረብ ገቢያቸውን አሳድገዋል።

አርሶ አደሯ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ያላቸው ሲሆን፤ በባንክም 80 ሺ ብር ቆጥበዋል።

በአሁኑ ወቅት “አደረጃጀቶችን በመጠቀም የፖለቲካ አቅም በማጎልበትና ሌሎች ሴቶች እንዲጠነክሩ በማድረግ የመሪነት ሚና እየተጫወትኩ ነው” ብለዋል።

በወረዳው እስከ አምስት መቶ ሺ ብር የሚገመት ሃብት ያካበቱና ጥሩ ተሞክሮ ያላቸው ሴት አርሶ አደሮችም ተጎብኝተዋል።

ሴት አርሶ አደሮቹ እንደሚናገሩት፤ ተግተው በመስራታቸው ጥሩ የመኖሪያ ቤት ገንብተዋል። ልጆቻቸውን እያስተማሩ ናቸው። ሌሎች የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ከማሟላት አልፈው ገንዘብ እየቆጠቡ ናቸው።

በአሁን ወቅት በገጠር ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ተረድቶ በአግባቡ ለተጠቀመ ለመለወጥ ሰፊ እድል መኖሩን ነው የሚናገሩት።

የብአዴንና ደኢህዴን ሴቶች ሊግ አመራር አባላት በወረዳው ተገኝተው የግንባር ቀደም ሴቶቹን የአኗኗር ዘዬ መቀየር በመመልከታቸው ጥሩ ልምድ ለመቅሰም ችለዋል።

ሴቶች በአካባቢያቸው ያለውን ሃብትና ጉልበታቸውን ተጠቅመው መለወጥ እንደሚችሉ የሚያሳይ ጥሩ ተሞክሮ መሆኑንም ነው የገለጹት።

እንደአመራር አባላቱ ገለጻ፤ ሴት አርሶ አደሮቹ በራስ መተማመናቸው ከፍ ያለ ነው። ይህ ደግሞ የፈጠሩት ኢኮኖሚያዊ አቅም ጠንካራ በመሆኑ የተገኘ ነው።

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ሊቀ መንበር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸው እንደገለጹት፤ እውነተኛ የሴቶች ነጻነት ማረጋገጫው የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እውን መሆን ነው።

የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተደራጀ መልኩ እንዲንቀሳቀሱና የቁጠባ ባህላቸውን እንዲያዳብሩም እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በገጠር ትራንስፎረሜሽን የሴቶች መለወጥ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው መደረጉን አመልክተው፤ “ለውጥ እየመጣ መሆኑን የዛሬ ባለ ጥሩ ተሞክሮ ሴቶች ህይወት ላይ ይንጸባረቃል” ብለዋል።

‘’ዛሬ ገጠር ውስጥ ገብተን ያየናቸው የሴቶቹ ቤትና የሚጠቀሙበት ቁሳቁሶች እየተለወጠ ያለውን የአኗኗር  ዘይቤ የሚያሳዩ ናቸው’’  ያሉት ሊቀ መንበሩዋ፤ ይህ ደግሞ ለአገሪቷ የለውጥ ሂደት ውስጥ ትልቅ ትርጉም ያለው ስኬት መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ ኢኮኖሚያዊ አቅም ሲጠነክር “ንቃተ ህልናቸው ስለሚለወጥ ፖለቲካ ላይ ያላቸው ተሳትፎና የመደራደር አቅማቸው ከፍ ይላል” ብለዋል።

የሊጉ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መጋቢት 28 ቀን 2009 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም ግምገማ የሚያደርግ ሲሆን፤ የዚህ ጉብኝት ዓላማም በተጨባጭ የተገኘውን ለውጥ መገምገም መሆኑ ታውቋል።

በነገው እለትም በዚሁ በሰሜን ሸዋ በማህበር የተደራጁ ውጤታማ ሴቶች ይጎበኛሉ።

ደብረማርቆስ  መጋቢት 24/2009  የህዝቡን የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ  ትግሉን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ብአዴን) አስታወቀ።

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት ስድስት ወራት መደበኛና በጥልቅ ተሃድሶ ንቅናቄው የደረሰባቸውን የግምገማ ውጤት ለአመራሩ ይፋ የተደረገበት መድረክ በደብረማርቆስ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ ላይ የብአዴን ጽህፈት ቤት ሀላፊ  አቶ አለምነው መኮነን እንዳሉት ከፍተኛ አመራሩ መላ ህዝቡን በማሳተፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለይቶ ደረጃ በደረጃ የመፍታት አቅጣጫ መከተል አለበት።

የመድረኩ አላማም ባለፉት ስድስት ወራት በመደበኛና በታሃድሶ ንቅናቄው የተደረሰባቸውን ድምዳሜዎችና ውጤቶች ለአመራሩ በማሳወቅ እስከ ታች ድረስ ለማውረድ መሆኑን ገልጸዋል።

በጥልቅ ታሃድሶው የኪራይ ሰብሳቢነትን ፣ የትምክተኝነት አመለካከትንና አስተሳሰብን በጠራ መንገድ ለመታገል የሚያስችል ቁመና ላይ መድረሱን ማዕከላዊ ኮሚቴው መገምገሙ ጠቅሰዋል፡፡

"ይህም የድርጅቱን መርሆዎች በመጨበጥ የህዝቡን የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎችን  ለመመለስ  አንድ ምዕራፍ የተሻገርንበት ነው" ብለዋል።

የመካከለኛ አመራሩ በቀጣይ የመሰረታዊ ድርጅትና የህዋስ አደረጃጀቶችን ዋና የመተጋገያ መድረክ ማድረግ እንደሚገባ አቅጣጫ መቀመጡን አመልክተዋል፡፡

ይህም ችግር ያለባቸውን አመራሮችን በየጊዜው ለማረም፣ በጥፋታቸው በህግ እንዲጠየቁ ለማድረግ፣ አድርባይነትን ለማስወገድ፣ የወጣቶች ስራ እድል ፈጠራን ለማቀላጠፍ የተቀመጠው ነው ተብሏል፡፡

የህዝቡን የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ ትግሉ ማጠናከር እንደሚያስፈልግም ተገልጿል፡፡

ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል የሰሜን ሸዋ ዞን የብአዴን ጽፈት ቤት ሀላፊ አቶ ተፈራ ወንድማገኝ እንደገለጹት መድረኩ  በጥልቅ ተሃድሶው የተሰሩ እና ያልተሰሩ ተግባራትን በመለየት እንዲሁም የተገኙ ውጤቶች ምን እንደሆኑ ለመገንዘብ አስችሏል።

" በቀጣይ ህዝብን በቅንነት በማገልገል፣ ችግሮችን ፈጥኖ በማረምና የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ በጥራት በማከናወን የመልካም አስተዳደርን ለማስፈን ቁርጠኛ አቋም እንድይዝ አግዞኛል "ብለዋል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ብአዴን ጽፈት ቤት ሀላፊ አቶ ከፍያለው ሙላቴ በበኩላቸው መድረኩ የተሰሩት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ ክፍተቶችን  ደግሞ እየለዩ ተከታትለው እንዲያስተካከሉ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።

"እንደ ዞኑ  ደግሞ ጥልቅ ተሃድሶው ማህበረሰቡ ከአመራሩ ጋር ተቀራርቦ እንዲሰራ ምቹ ሁኔታን መፍጠር መቻሉ ማየት የተቻለበት ነው" ብለዋል።

በደብረ ማርቆስ ከተማ ለሁለት ቀናት በተካሄደው  መድረክ ከ200 በላይ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስረዳደር አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

Published in ፖለቲካ

ሚዛን መጋቢት 24/2009 በሚዛን አማን ከተማ ከሚገኙ አምስት የትምህርት ተቋማት በጎ ፈቃደኞች  ከ270 በላይ ዩኒት ደም መለገሱን የጅማ ደም ባንክ አገልግሎት አስታወቀ ።

በጅማ ደም ባንክ አገልግሎት የደም ልገሳ አስተባባሪ አቶ መስፍን መካሻ ለኢዜአ እንደገለፁት ደሙ የተለገሰው በተያዘው ወር ለአራት ተከታታይ ቀን በተካሄደ ዘመቻ ነው ።

ደሙን ከለገሱት የትምርት ተቋማት ውስጥ የሚዛን አማን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ፣የሚዛን ሁለተኛና መሰናዶ ትምህርት ቤት፣ የአማን ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ይገኙበታል፡፡

እንደ አቶ መስፍን ገለፃ በትምህርት ተቋማቱ ከሚገኙ በጎ ፈቃደኞች የተለገሰው  ይሄው ደም  ለተለያዩ ሆስፒታሎች የሚያገለግል ነው ።

በሚዛን አማን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ የሁለተኛ ዓመት የክሊኒካል ነርሲንግ ተማሪ  መሳይ መኮንን በሰጠው አስተያየት በፍቃደኝነት ደም ሲለግስ የአሁኑ ለአራተኛ ጊዜ መሆኑን ተናግሯል፡፡

"በደም ዕጦት ሕይወታቸውን የሚያጡ ወገኖችን ለመታደግ በማደርገው የደም  ልገሳ የህሊና ሰላምና እርካታ ይፈጥርልኛል" ብሏል፡፡

"አንድም እናት በደም ዕጦት ምክንያት መሞት ስለሌለባት ደም ለግሻለሁ" ያለችው ደግሞ በዚሁ ኮሌጅ የአንደኛ ዓመት ተማሪ  ምንታምር ደኪቶ ናት፡፡

ደም ስትለግስ  የመጀመሪያዋና በዚህም ደስተኛ መሆኗን ተናግራለች፡፡

Published in ማህበራዊ

ፍቼ መጋቢት 24/2009 በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በአርሶ አደሩ የጉልበት ተሳትፎ በ91 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ተከናወነ፡፡

በዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራ ሂደት ባለቤት አቶ ነጋሽ በቀለ ለኢዜአ እንደገለፁት ስራው የተከናወነው በተዳፋትና በእርሻ ማሳ ዳርቻዎች ላይ ነው ።

በዞኑ 13 ወረዳዎች ላለፉት 35 ቀናት በተካሄደ ዘመቻ ከተከናወኑት ከእነዚህ ስራዎች መካከል የ80 ሺህ ኪሎ ሜት የአፈርና የድንጋይ እርከን፣ የ161 ሺህ ሜትር ኪዩብ የውሃ መቀልበሻ ቦይ ይገኙበታል ።

"የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ዋና አላማ በክረምትና በጋ ወራት በንፋስ፣ በጐርፍና በልቅ ግጦሽ የሚደርሰውን የአፈር መሸርሸርና ለምነት ማጣት ችግር አስቀድሞ ለመከላከል ነው" ብለዋል ።

በአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራው  ከተሳተፉ 400 ሺህ  የዞኑ አርሶ አደሮችና ሌሎችም ነዋሪዎች ውስጥ  155 ሺህ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።

በውጫሌ ወረዳ የቡሌ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ወንድሙ ቶላ ውሃ፣ አፈርና ደንን መንከባከብና መጠበቅ ለእርሻ ሥራቸው ውጤታማነት አስተዋፆ ያለው በመሆኑ ተሳትፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል ።

ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ በሄክታር ማሳቸው ውስጥ ባካሄዱት የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ በጎርፈ ተጠርጎ የሚሄደው አፈር በመቅረቱ ያገኙት የነበረው 12 ኩንታል የስንዴ ምርት በእጥፍ ማደጉንም አመልክተዋል።

በግራር ጃርሶ ወረዳ የቶርባን አሼ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ቢፍቱ ነገዎ በበኩላቸው በልማት ቡድን በመደራጀት በአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራው መሳተፋቸውን ጠቅሰዋል ።

ባለፉት ዓመታት በማሳቸው ውስጥ ባካሄዱት የአፈርና ወሀ ጥበቃ ስራ የሰብል ምርታማነታቸው እያደገ መምጣቱን ጠቁመዋል፡፡

Published in ኢኮኖሚ

ፍቼ መጋቢት 24/ 2009 በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ዓመታዊ የባህል ስፖርቶች ውድድር ዛሬ በፍቼ ከተማ ተጀመረ ።

የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት የስልጠናና ውድድር  ስራ ሂደት ባለቤት  አቶ መኮንን ተፈራ እንደገለፁት ለስድስት ቀናት በሚቆየው ውድድር  ከአስር ወረዳዎችና ከአንድ የከተማ አስተዳደር የተውጣጡ 350  የባህል ስፓርት ተወዳዳሪዎች ይሳተፋሉ ።

በውድድሩ ከሚካሄዱት የባህላዊ የስፖርት ዓይነቶች መካከል ገና ፣ ፣ገበጣ ፣ ኩርቦ ፣ የፈረስ ጉግስና ሸርጥ ይገኙበታል፡፡

የውድድሩ ዓላማ በዞኑ ያለውን የባህል ስፖርት ለማሳደግና በኦሮሚያ ደረጃ ለሚካሄደው ውድድር ዞኑን የሚወክሉ ስፖርተኞችን ለመምረጥ ነው፡፡

በፍቼ ሁለገብ ስታድየም ዛሬ በጀተመረው ወድድር በገና ጨዋታ  ግራር ጃርሶ  ወረዳ ደገም ወረዳን እንዲሁም ያያጉለሌ ወረዳ ሂደቡ አቦቴ ወረዳን  አንድ ለዜሮ በሆነ ተመሳሳይ ውጤት አሸንፈዋል ።

ውድድሩን ያስጀመሩት የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ አለምነሽ ሃይሉ ናቸው ።

Published in ስፖርት

አዲስ አበባ መጋቢት 24/2009 ሰባተኛው የከተማ አቀፍ የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል በየካ ክፍለ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

ከመጋቢት 19 እስከ መጋቢት 24 ቀን 2009 ዓም ሲካሄድ የቆየው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል የመዲናዋ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ባህል ስፖርት ፌደሬሽን በጋራ ያዘጋጁት ነው።

በዚህ ውድድር በገና ጨዋታ፣ በሴቶች የገበጣ ፣ በሻህና በፈረስ ሸርጥ ጨዋታዎች አሸናፊ የሆነው የካ ክፍለ ከተማ 56 ነጥብ በማግኘት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

ቦሌ ክፍለ ከተማ ባሳየው ስፖርታዊ ጨዋነት የጸባይ ዋንጫ ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል።

ፌስቲባሉ በአስር የባህል ስፖርት ውድድሮች የተካሄደ ሲሆን፤ የመዲናዋ ስምንት ክፍለ ከተሞች ተሳትፈውበታል።

የካ ክፍለ ከተማ ዛሬ በተደረገው የፍጻሚ የገና ጨዋታ ውድድር አዲስ ከተማን በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።

በተመሳሳይ በፈረስ ሸርጥ የተካሄደውን ውድድርም የካ ክፍለ ከተማ በበላይነት አጠናቋል።

በሴቶች በተደረገው የትግል ጨዋታ ማአዛ ጌታቸው ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ስታሸንፍ በወንዶች ደግሞ አምበሴ ካሳ ከየካ አሸናፊ መሆን ችሏል።

በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑ ስፖርተኞች የገንዘብ፣ የሜዳሊያና የሰርተፊኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

አዲስ አበባ ባህል ስፖርት ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ መስፍን ከበደ ውድድሩ ከማዝናናቱ ባለፈ ወጣት ስፖርተኞችን ለማፍራት ይረዳል ብለዋል።

በፌስቲቫሉ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ስፖርተኞች ከ20 ቀን በኋላ በአክሱም ከተማ በሚካሄደው አገር አቀፍ ውድድር ከተማዋን ወክለው የሚሳተፉ ይሆናል።

Published in ስፖርት

ጅማ መጋቢት 24/2009  ከጅማ አዲስ አበባ እና ከጅማ አጋሮ ደዴሳ ያለው መንገድ በአፈጣኝ እንዲጠገን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የመንገዱን ብልሽት ተዘዋውሮ ተመልክቷል ።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ  አቶ አበበ ክፍኔ እንደገለጹት ከጅማ አዲስ አበባና ከጅማ አጋሮ ደዴሳ ያለው መንገድ በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቷል ።

" መንገዱ ካለው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አንጻር የአጭር ጊዜ ፣ አስቸኳይና ከባድ የጥገና እቅድ ተዘጋጅቶለት መሰራት አለበት "ብለዋል፡፡

ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ደግሞ የመንገዱን ደረጃ በማሻሻል በአዲስ መልክ መስራት አስፈላጊ እንዲደሆነም ጠቁመዋል፡፡

የጅማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበዱልሃኪም ሙሉ ከአዲስ አበባ፣  ጅማ፣ አጋሮ፣ ደዴሳ ያለው መንገድ ለበርካታ ዓመታት ምንም አይነት ጥገና ስላልተደረገለት  ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ ለብልሽት መጋለጡን ተናግረዋል ።

መንገዱ ለዓመታት ተበላሽቶ መቆየት ከፍተኛ የህዝብ ቅራኔ እየፈጠረ መሆኑንም ጠቅሰዋል ።

"የችግሩ መንስኤ  የደቡብ  ምዕራብ  የመንገድ ባለስልጣን  መስሪያ ቤት ከአካባቢው የአየር ጻባይ ጋር የሚስማማ እቅድ ነድፎ መስራት ባለመቻሉ ነው "ብለዋል ።

መንገዱ ማዕከላዊ ኢትዮጵያን ከደብብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኝና ቡና ለአለም ገበያ የሚቅርብበት በመሆኑ አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጠው እንደሚገባወም ጠቁመዋል።

የአጋሮ ከተማ የአገር ሽማግሌ ሼህ ሙህዲን አባፊጣ ከደዴሳ አጋሮ ያለው የአስፓልት መንገድ ብልሽት ጉዳይ ትኩረት አለመሰጠቱ  እንዳሳዘናቸው ለቋሚ ኮሚቴዎቹ ገልጸዋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ መንገዶች ባለስልጣን ጽህፈት ቤት ተወካይ አቶ ቴዎድሮስ መኩሪያ ከአዲስ አበባ እስከ ደዴሳ  ያለው መንገድ ሳይጠገን የቆየው በአካባቢው የግብአት ችግር መኖሩ፣ የአየር ፀባይ አስቸጋሪነትና በማሽን እጥረት መሆኑን ምላሽ ሰጥተዋል 

በአገር ውስጥ የሚገኙ የግል የኮንስትራክሽን ድርጅቶች  በተመጣጣኝ ዋጋ ለመስራት ፈቃደኛ ካለመሆናቸውም በላይ ደፈርው የገቡ ተቋራጮችም አቋርጠው የወጡበት ሁኔታ እንዳለም ጠቅሰዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ  የጥገናው ስራ ያለ ኮንትራት ውል ለኢትዮጵያ መንገድ ስራ ኮርፖሬሽን  መሰጠቱን ጠቅሰው ኮርፖሬሽኑ ስራው በአስቸኳይ  ለመጀመር የሚያስችል ግብአትና የግንባታ መሳሪያዎች አሟልቶ   ወደ ስራ መግባቱን ለቋሚ ኮሚቴው ገልጸዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው መንገዱ ከጊዜያዊ ጥገና ባለፈ ዘላቂ መፍትሔ ሊመቻችለት እንደሚገባም  አሳስቧል ።

Published in ኢኮኖሚ

አዲስ አበባ መጋቢት 24/2009 "አባላቱ የድርጅቱን የልደት በዓል ሲያከብሩ ከፊታቸው የሚጠብቃቸውን ከባድ ትግል ለመወጣት ቃላቸውን ማደስ አለባቸው" ሲሉ የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ኦህዴድ/ኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጥሪ አቀረቡ

በአዲስ አበባ የድርጅቱ 27ኛ ዓመት የልደት በአል የከተማው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ከ10ሩም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ አባላት በተገኙበት ተከብሯል።

ከንቲባው ድሪባ ኩማ እንደተናገሩት፤ ድርጅቱ ባለፉት 27 ዓመታት የኦሮሞን ህዝብ በሁሉም መስኩ ተጠቃሚ ለማድረግ አበረታች ስራዎችን አከናውኗል።

በተለይ ባለፉት 15 ዓመታት በክልሉ ውስጥ በትምህርት፣ በጤናና በመሠረተ ልማት ረገድ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን አስታውሰዋል።

''በዚህ ወቅት ድርጅቱ ከባድና ፈታኝ የትግል ጊዜ ይጠብቀዋል'' ያሉት አቶ ድሪባ፤ ሁሉም አባል ቃሉን በማደስ ጠንክሮ ለህዝቡ ችግሮች መፍትሄ መስጠት እንደሚኖርበት ነው የተናገሩት።

በዚሁ መሠረት የድርጅቱ አባላት ቀጣይ የትግሉን አቅጣጫ በአግባቡ ተገንዘበው ለትግሉ ራሳቸውን ዝግጁ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በበዓሉ ላይ መልዕክት ካስተላለፉ እህት ድርጅቶች መካከል የህወሃት ተወካይ አቶ አለነ ገብሩ ኦህዴድ ለልማትና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ በቁርጠኝነት ሲንቀሳቀስ መቆየቱን አስታውሰዋል።

ተወካዩ ድርጅቱ በሕዝቦች መልካም ፈቃድና ወዳጅነት ላይ የተመሰረተችና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በከፍተኛ የዓላማ ጽናት ሲንቀሳቀስ መቆየቱንም ተናግረዋል።

"ኦህዴድ ይህን ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መስመር ጠብቆ እስከ ተጓዘ ድረስ የኦሮሞን ሕዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ይመልሳል" ያሉት ደግሞ የደኢህዴን ተወካይ አቶ ዋቸሞ ጴጥሮስ ናቸው።

አቶ ዋቸሞ፤ ኦህዴድ የኢትዮጵያን ህዳሴ ወደማይቀለበስበት ደረጃ ለማድረስ የሚችል ጠንካራ ድርጅት እንደሆነ እምነታቸውን ገልጸዋል።

የብአዴን ተወካዩ አቶ ቢንያም አደራ በበኩላቸው "ደርጅቱ በኢትዮጵያ ሕዝቦች የትግል ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ሚና የነበረው ነው" ብለዋል።

በመሆኑም ቀጣዩ ትግል ከባድ ስለሚሆን ድርጅቱ በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ የተሻለ የአመራርነት ሚና ሊጫወት እንደሚገባው ነው የጠቆሙት።

የበዓሉ ታዳሚዎች በበኩላቸው የድርጅቱ አባላት በዓሉን ከማክበር ባለፈ በአገሪቷ በሚከናወኑ ተግባራት ላይ የመሪነት ሚና ሊጫወቱ  እንደሚገባ ነው የገለጹት።

በተለይ ደግሞ የመልካም አስተዳደርና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮችን ለማቃለል አባላት ከደርጅቱ ጎን ሊቆሙ እንደሚገባ ተመልክቷል።

አባላቱ አገሪቷ የተያያዘችውን የእድገት ጎዳና ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስም ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በበዓሉ ላይ የድርጅቱን ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ የሚያመላክት የአቋም መግለጫም ተነቧል።

Published in ፖለቲካ
Page 1 of 3

ኢዜአ ፎቶ እይታ

በማህበራዊ ድረገፅ ይጎብኙን