አርዕስተ ዜና
×

Warning

JUser: :_load: Unable to load user with ID: 452
Items filtered by date: Tuesday, 03 October 2017

ሃዋሳ መስከረም 23/2010 የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሀገሪቱ በዘርፉ እያስመዘገበች ያለውን ስኬት የሚያሳይ መሆኑን የሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ገለጹ ።

የምክር ቤቱ አባላት የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ዛሬ በጎበኙበት ወቅት ላነሷቸው ጥያቄዎችም ከኢንዱሰትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ከጉብኝቱ ተሳታፊዎች መካከል የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ሊቀመንበር አቶ አየለ ጫሚሶ እንደገለጹት ፓርኩ ለአካባቢው ወጣቶች የፈጠረው የስራ እድል መልካም አጋጣሚን ያመቻቸ ነው።

ከዚህ ባለፈ ግን ፓርኩ ከክልሉ በዝቅተኛ የሙያ ደረጃ ላይ ላሉትም  ሆነ በላቀ ደረጃ የሰለጠኑ ባለሙያዎችን በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚያሳትፍበት ሁኔታ ምን ገጽታ እንዳለው ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ሌላው የጉብኝቱ ተሳታፊ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ህብረት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ገብሩ በርሄ በበኩላቸው ፓርኩ ከውጭ ሃገር ባለሃብቶች ባለፈ የሃገር ውስጥ ባለሃብቶችን ለማሳተፍ እየተደረገ ያለው ጥረት ግልጽ ሊደረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢዴፓ/ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ አንዳርጋቸው አንዱዓለም በበኩላቸው የኢንዱስትሪ ፓርኩ በሃዋሳ ሃይቅ እና በአካባቢው ላይ ተጽዕኖ እንዳያደርስ የሚደረገው ጥረት በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጠይቀዋል።

የኢንዱሰትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ኦፕሬሽንና አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው ሰለሞን ለጉብኝቱ ተሳታፊዎች በሰጡት ማብራሪያ ፓርኩ የስራ እድሎችን እየፈጠረ ያለው ለሁሉም የሃገሪቱ ዜጎች ነው።

የምርት ሒደቱ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን የሚጠቀም በመሆኑም ከፓርኩ ውስጥ አካባቢን ሊበክል የሚችል ምንም አይነት ተረፈ ምርትም ሆነ ፍሳሽ እንደማይወጣ አብራርተዋል።

የኢንዱሰትሪ ፓርኮች ቀዳሚ ዓላማ ምርቶቹን ለዓለም አቀፍ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሪ ማስገኘት መሆኑን ገልጸው የአገር ውስጥ ባለሃብቶችን ለማሳተፍም ብድርን ጨምሮ የቴክኖሎጂ፣ የሎጅስቲክስና ሌሎች ማበረታቻዎችን ለማድረግ መንግስት ዝግጁ መሆኑን አስረድተዋል።

የአንድነት ለዴሚክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ፕሬዝዳንትና የጉብኝት ቡድኑ መሪ አቶ ትእግስቱ አወል እንዳሉት የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ እንደ መነሻ አገሪቱ በኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ እያስመዘገበች ያለውን ስኬት የሚያሳይ ነው።

በጉብኝቱም ስለ ኢንዱስትሪ ፓርኩ ያላቸውን ግንዛቤ ሊጨምር የሚችል ማብራሪያ እንዳገኙ ገልጸው በፓርኩ ውስጥ ያስተዋሉት ነገር ለሃገራችን ኢንዱስትሪ እድገት መነሻ ሊሆን የሚችል እንደሆነም ተናግረዋል።

መንግስት ሼዶች ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ እንዲገቡና የሀገር ውስጥ ባለሃብቶችም ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ ሰፊ ንቅናቄ መፍጠር እንደሚገባው ጠቁመዋል።

Published in ፖለቲካ

ሽሬ እንዳስላሴ መስከረም 23/2010 አረጋውያን በሁሉም ዘርፍ ተጠቃሚና ተሳታፊ እንዲሆኑ የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ ሊኖር እንደሚገባ የትግራይ ክልል የአረጋውያን ማህበር አስታወቀ።

ዓለም አቀፍ የአረጋውያን ቀን " የአረጋውያንን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የተከማቸ እውቀታቸውንና ችሎታቸውን በአግባቡ ተጠቅመን ነገን ለአረጋውያን የተመቸ እናድርግ " በሚል መሪ ቃል በክልል ደረጃ በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ በድምቀት ተከብሯዋል።

የክልሉ የአረጋውያን ማህበር ሊቀ መንበር አቶ አርአያ ገሰሰው በዚህ ወቅት እንዳሉት፣ በችግር ምክንያት አረጋውያን ወደ ጎዳና እንዳይወጡ እየተደረገ ያለው ድጋፍና እንክብካቤ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።

እነዚህ የሕብረተሰብ ክፍሎች በሁሉም የልማት ዘርፍ ተጠቃሚና ተሳታፊ እንዲሆኑ የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

የትግራይ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ኪሮስ ሐጎስ በበኩላቸው፣ ጽህፈት ቤቱ በራሱና የተለያዩ አካላትን በማስተባበር አረጋውያንን እየደገፈ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ በኩል በተለይ የትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት (ትዕምት) የክልሉን አረጋውያን ለመደገፍ በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ እንደሚመድብና ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተናግረዋል። 

በክልሉ የሚገኙ አረጋውያን አቅማቸው በፈቀደ በገቢ ማስገኛ ሥራዎች ተሰማርተው ራሳቸውን ለመቻል ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ በተጨማሪ ድርጅቱ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ትልቁን ደርሻ መውሰዱን አመልክተዋል።

እንደ ወይዘሮ ኪሮስ ገለጻ፣ የትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት አረጋውያንን ጨምሮ ጧሪ የሌላቸው የሰማዕታት ቤተሰቦችን ለመደገፍ በየዓመቱ ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።

በተመሳሳይ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶ ለዚሁ በጎ ተግባር የሚውል ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ መገኘቱን ኃላፊዋ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በየወረዳው ለሚገኙ ከ226 ሺህ በላይ አረጋውያን በሴፍትኔት ፕሮግራም ታቅፈው ቀጥተኛ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ነው ወይዘሮ ኪሮስ የገለጹት።

"አረጋውያንን መደገፍ ራስን መደገፍ ነው" ያሉት የቢሮ ኃላፊዋ፣ የአገር ክብር የሆኑትን አረጋውያን መደገፍና መንከባከብ የሁሉም ሕብረተሰብ ኃላፊነት መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

"አረጋውያን መነበብ የሚገባቸው ታላቅ መፃጻህፍት ናቸው" ያሉት ደግሞ በበዓሉ ላይ የተገኙት የክልሉ ሴቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር የትምወርቅ ገብመስቀል ናቸው።

በክልሉ ባሉት የአረጋውያን ማህበራት የሴት አረጋውያንን ተሳትፎ ለማጠናከር በትጋት እንደሚንቀሳቀሱ ተናግረዋል።

በትግራይ ክልል 192 ህጋዊ ሰውነት ያላቸው የአረጋውያን ማህበራት የሚገኙ ሲሆን ማህበራቱ በእንስሳት እርባታ፣ በእህል ወፍጮ፣ በመዝናኛ ማዕከላትና በሌሎች የገቢ ማስገኛ ሥራዎች ተሰማርተዋል።

ዓለም አቀፍ የአረጋውያን ቀን በዓል በጉብኝት፣ በፓናል ውይይትና በሩጫ ውድድር በሽሬ አንዳስላሴ ከተማ ተከብሯል ።

Published in ማህበራዊ

አዲስ አበባ መስከረም 23/2010 በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለኃብቶች መንግሥት አስፈጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ተናገሩ። 

2ኛው የአፍሪካ የፋሽን ሳምንት አውደ ርዕይ ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፍቷል።       

በአውደ ርዕዩ ላይ በጨርቃጨርቅና አልባት ዘርፍ እንዲሁም በቆዳ ውጤቶች ላይ የተሰማሩ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ኩባንያዎች እየተሳተፉ ነው።

የቱርክ፣ቻይና ፣ጀርመን፣ባንግላዲሽ፣ ጣሊያን ፣ጃፓን፣ ሕንድና ኢንዶኖዥያ ኩባንያዎች ከተሳታፊዎቹ መካከል ይገኙበታል። 

ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት የጨርቃጨርቅና አልባሳት ዘርፍ ሰፊ የሰው ሀይል፣ በእሴት ሰንሰለቱ በርካታ ተዋንያኖችን የሚሳትፉበትና ከተለያዩ አገራት ጋር ትስስር የሚፈጠርበት በመሆኑ ውጤታማ የሚያደርግ ዘርፍ ነው።   

የኢትዮጵያ መንግሥትም ጥቅሙን ከግምት ውስጥ በማስገባት ዘርፉ በፖሊሲና ስትራቴጂ መደገፉን ያብራሩት ፕሬዘዳንቱ በዘርፉ ለሚሰማሩ የአገር ውስጥና የውጭ ባለኃብቶችን ለመደገፍ መንግሥት ቁርጠኛ  መሆኑን ተናግረዋል።    

በኢትዮጵያ እየተገነቡ ያሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮችም መንግስት ዘረፉን ለማሳደግ እያደረገ ላለው እንቅስቃሴ አንዱ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል። 

 

የኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ለማ በበኩላቸው መሰል ኤግዚቢሽኖች የውጭ ኩባንያዎችን ባሳተፈ መልኩ መካሄዳቸው የአገር ውስጥ አምራቾች ልምድ እንዲቀስሙ የላቀ አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል።   

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ለውጦች እየተመዘገቡ ባለበት ወቅት ኤግዚቢሽኑ መካሄዱ ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር ነው ያስረዱት። 

የኤግዚቢሽኑ ተሳታፊ ወጣት ቢታኒያ ተክለጻዲቅ በኤግዚቢሽኑ ላይ ዘመናዊና ባህላዊ የሽመና ውጤቶች ይዛ ቀርባለች።

እንደ ወጣት ቢታንያ ገለጻ ኤግዚቢሽኑ የአገር ውስጥ አምራቾች በዘርፉ የደረሱበትን ደረጃ ለማሳየት የሚኖረው ጠቀሜታ ከፍ ያለ ነው።  

የፓኪስታኑ አል-ሀረም ኢንተርፕራይዝ ተወካይ ኩራም ሳጂድ የተለያዩ የጨርቃ ጨርቅ ውጤቶችን ይዞ መቅረቡን ገልጾ በኤግዚብሽኑ የተሻለ የገበያ ትስስር የሚያገኙበት እንደሚሆን ተስፋ አለኝ ብሏል። 

ኤግዚቢሽኑ ለአራት ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከ235 በላይ አምራቾችና ላኪዎች እየተሳተፉበት ነው።    

Published in ኢኮኖሚ

አዲስ አበባ መስከረም 23/2010 ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በአሜሪካ ላስቬጋስ  በንጹሃን ዜጎች ላይ በደረሰው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የተሰማቸውን ሃዘን ለአሜሪካ ህዝብ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንጹሃን ዜጎች ላይ በተከፈተው ተኩስ ምክንያት በደረሰው የሰዎች ሞትና የመቁሰል አደጋ የተሰማቸውን ሃዘን ለአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በላኩት የሃዘን መግለጫ፤ ኢ-ሰብዓዊ በሆነ መንገድ በተፈጸመው ጥቃት ጥልቅ ሃዘን የተሰማቸው መሆኑን ገልጸውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአሜሪካ ህዝብና መንግሥት እንዲሁም ህይወታቸውን ላጡና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች በኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸው መጽናናትን ተመኝተዋል።

በላስ ቬጋስ በተኩስ እሩምታ የሞቱት የሰዎች ቁጥር አስከ አሁን 59 የደረሰ ሲሆን ከ500 በላይ ደግሞ መቁሰላቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።

Published in ማህበራዊ

አምቦ/መቱ መስከረም 23/2010 በምእራብ ሸዋና በቡኖ በደሌ ዞኖች በክረምት ወራት 55 ሺህ 946 ሄክታር መሬት የለማ የእንስሳት መኖ ደርሶ ጥቅም ላይ እየዋለ መሆኑ ተገለፀ።

በዞኖቹ በክረምቱ ወራት 225 ሚሊዮን የእንስሳት መኖ  ችግኞች ተተክለው በአርሶ አደሩ እንክበካቤ ሲደረግላቸው ቆይቷል።

የምእራብ ሸዋ ዞን እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ፅህፈት ቤት ሃላፊ ወይዘሮ መሳይ አንየው ለኢዜአ እንደገለፁት የእንስሳት መኖ ልማቱ የተካሄደው እጥረቱ በሚታይባቸው ዝናብ አጠርና ደጋማ  ወረዳዎች ነው ።

የመኖ ልማቱ የክረምቱን ዝናብ በመጠቀም በእርሻ ማሳ ወሰኖችና በተዳፋት ቦታዎች ተካሄዷል።

በክረምቱ ተተክለው አሁን ላይ ለመኖነት እየዋሉ ያሉት  ዝሆኔ፣ ችብሃና ሳስባንያ የተባሉ የሳር ዝርያዎች ናቸው ።

የደረሱት መኖዎች ከንክኪ ነጻ ተደርገው ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

"አርሶ አደሩ ከተለምዶ የእንስሳት አመጋገብ ተላቆ ዘመናዊ አሰራርን እንዲከተል ለማድረግ ባለፉት አራት ዓመታት የተከናወኑና ውጤታማ የሆኑ ስራዎች ለማስፋፋት እየተሰራ ነው" ብለዋል።

የአምቦ ወረዳ ነዋሪ አቶ ሚልኪሳ ፈይሳ በሰጡት አስተያየት የእንስሳት መኖ ማዘጋጀት ከጀመሩ ወዲህ እንስሳትን በቤት ወስጥ አስረው በመቀለብ የወተት ምርታቸውን ማሳደግ እንደቻሉ ተናግረዋል።

በቡኖ በደሌ ዞን በበደሌ ወረዳ ዲገጃ ቀበሌ ነዋሪ አርሶአደር ብርሀኑ ምርከና በበኩላቸው በክረምት ወራት በአጭር ጊዜ የሚደርስ የሳር ዝርያ  በግማሽ ሄክታር ማሳቸው ላይ ማልማታቸውን ተናግረዋል ።

“የሳር ችግኞቹን ከተከልኩ ጀምሮ የዝናብ ስርጭት ባለመቋረጡ  በአሁኑ ወቅት ለከብቶቼ መኖነት ማዋል ጀምሬያለሁ " ብለዋል ።

የሳር ዝርያዎቹን በማልማቴ ከብቶቼን ወደ ግጦሽ ለማሰማራት የማጠፋውን ጊዜ በመቆጠብ ለሌላ ስራ ለማዋል እረድቶኛል " ያሉት ደግሞ አርሶ አደር ተፈራ ባቲ ናቸው ።

Published in ማህበራዊ

ነገሌ መስከረም 23/2010 የመኸር አዝመራው ዘግይቶ በሚጀመርበት ጉጂ ዞን 108 ሺህ 206 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ስራው አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

በዞኑ ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ ዘውዴ በቀለ እንደገለፁት በጉጂ አርብቶ አደሩ አካባቢ የመኸር አዝመራው ስራ የሚካሄደው ከሀምሌ ወር መጨረሻ እስከ መስከረም 30 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው።

በአካባቢው በአምስት ዋና ዋና ሰብሎች ለማልማት ከታቀደው 108 ሺህ 206 ሔክታር መሬት እስከአሁን  81 ሺህ 350 ሄክታር መሬት  በዘር ተሸፍኗል፡፡

በዘር ከተሸፈነው መሬት ውስጥ 13 ሺህ 276 ሄክታሩ በመስመር የተዘራ ሲሆን በልማቱ 72 ሺህ 309 አርሶና ከፊል አርብቶ አደሮች እየተሳተፉ ነው።

በዞኑ ሻኪሶ ወረዳ የመጋዶ ቀበሌ ነዋሪ አቶ አየለ ኢዴማ በሰጡት አስተያየት ለመኸር አዝመራው ካዘጋጁት 10 ሄክታር መሬት ግማሹን በቦለቄ ዘር መሸፈናቸውን ተናግረዋል።

በባለሙያዎች እገዛ አስፈላጊው ግብአት በመጠቀም ምርታማነታቸውን ለማሳደግ  እየሰሩ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።

በዝናብ እጥረት የበልግ አዝመራ በመጥፋቱ በመኸሩ አዝመራው ላይ ተስፋ መጣላቸውን የተናገሩት ደግሞ በሊበን ወረዳ የድቤ ጉቼ ቀበሌ ነዋሪ አቶ አብዲኑር አብዱረህማን ናቸው፡፡

በአካባቢያቸው ዝናብ የጀመረው መስከረም ከገባ በኋላ በመሆኑ ለአሁኑ አዝመራ ካዘጋጁት አንድ ሄክታር መሬት ላይ ገና የተወሰነውን ብቻ በቦለቄ ዘር እንደሸፈኑም አርሶ አደሩ አመልክተዋል፡፡

Published in ኢኮኖሚ

ደሴ መስከረም 23/2010 የአማራና አፋር ክልል ምክር ቤቶች በአጎራባች ወረዳዎች የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ባከናወኑት ሥራ ችግሮችን በውይይት የመፍታት ባህል እየዳበረ መምጣቱ ተጠቆመ።

 የአማራና አፋር ክልል ምክር ቤቶች የጋራ ፎረም በ2009 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምና በ2010 የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ትናንት በኮምቦልቻ ከተማ መክሯል፡፡

 የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ይርሳው ታምሬ እንደገለጹት፣ ፎረሙ በአጎራባች ወረዳዎች የተጠናከረ ቅንጅታዊ ሥራ በመስራቱ የሚከሰቱ ችግሮችን በውይይት የመፍታት ባህል እየዳበረ መጥቷል።

 በእዚህም የህዝቡ ሰላምና ፀጥታ ከጊዜ ወደጊዜ እየተረጋገጠ በመምጣቱ በአጎራባች ወረዳዎች የሚገኙ ነዋሪዎች የኢኮኖሚና የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

  ፎረሙ ከሕብረተሰቡ ጋር በመተባበር በአጎራባች ወረዳዎቹ ግጭት ሲፈጠር በግድያና በዘረፋ የተሰማሩ ግለሰቦች ለህግ እንዲቀርቡ በማድረግ፣ የተዘረፉ ንብረቶችን በማስመለስና እርቅ በማውረድ ያከናወናቸው ተግባራት የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

 እንደአቶ ይርሳው ገለጻ፣ አጎራባች ወረዳዎቹን በስድስት ክላስተር በማደራጀት ህገ ወጥ የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል በተሰራው ሥራም አበረታች ውጤት ተመዝግቧል፡፡

 የአፋር ክልል ምክርቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መሐመድ ከድር በበኩላቸው፣ በአጎራባች ወረዳዎቹ በቅንጅት በመሰራቱ ከዚህ በፊት በግጦሽ ሳርና በተለያዩ መሰል ምክንያቶች ይፈጠሩ የነበሩ ግጭቶች እንዲቀንሱ ማድረግ መቻሉን አመልክተዋል፡፡

 ይህን አጠናክሮ ለማስቀጠልና የህዝቦችን የጋራ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በአጎራባች ወረዳዎች ያሉ የቀበሌ ምክር ቤቶችን አቅም በቁሳቁስ፣ በሰው ኃይልና በአመለካከት መገንባት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡

 በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የአማራ ክልል ምክርቤት የህግና ፍትህ አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አማረ ሰጤ፣ በአጎራባች ወረዳዎቹ ሰላምና ልማትን ለማምጣት አበረታች ሥራዎች ቢሰሩም አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት የክልል አመራሮች ድርሻ የላቀ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

 በሰሜን ሸዋ ዞን የአንኮበር ወረዳ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ የማታወርቅ ድባቤ ወረዳቸው ከአፋር ክልል ሦስት ወረዳዎች ጋር እንደሚጎራበት ተናግረዋል።

 በዝናብ እጥረት ምክንያት ከአፋር ክልል አጎራባች ወረዳዎች ሰዎችና እንስሳት ወደ ወረዳው ሲመጡ ህዝቡ የምግብ አቅርቦት በማድረግ ተቀብሎ እንደሚያስተናገዳቸው አስታውሰዋል፡፡

 በሁለቱ ክልል አጎራባች ህዝቦችና በመንግስት ትብብር የመንገድ ሥራዎች ተሰርተው የንጹህ መጠጥና የአምቡላንስ አልግሎት በጋራ በመጠቀም ላይ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

 በአፋር ክልል በሚገኘው አዋሽ ፈንታሌና በሰሜን ሸዋ ስር ባለው አጎራባች ወረዳ የሚኖሩ ሕዝቦች 62 ሄክታር መሬት በማልማት ከ500 በላይ ቤተሰቦች በጋራ እየተጠቀሙ መሆናቸውንም አያይዘው ተናግረዋል፡፡

 በአፋር ክልል አድአር ወረዳ የቀበሌ 01 ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ሰይድ አሊ ቀበሌያቸው ከአማራ ክልል ባቲ ወረዳ ጋር አጎራባች በመሆኑ ከዚህ ቀደም በግጦሽ ሳር ምክንያት ግጭቶች ይፈጠሩ እንደነበር አስታውሰዋል።

 በአሁኑ ወቅት የሃይማኖት አባቶች፣ የጎሳ መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ከፀጥታ አደረጃጀቱ ጋር በመተባበር ባደረጉት ጥረት ችግሮቹን ሙሉ በሙሉ መፍታት እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡

 በአጎራባች ወረዳዎቹ መካከል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በመጎልበቱ የትምህርትና የጤና ተቋማትን በጋራ መጠቀም መቻሉንም አመልክተዋል፡፡

 የኦሮሚያ ክልል ምክርቤት አፈ ጉባኤ አቶ እሸቱ ደሴ በሁለቱ ክልል ምክር ቤቶች የሚመራውን የጋራ ፎረም መቀላቀላቸውን  ገልጸዋል።

 ይህም "ከኦሮሚያ ክልል ጋር በሚዋሰኑ ወረዳዎች ዘላቂ ሰላምንንና የጋራ ኢኮናሚያዊና ማሕበራዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ልምድ ለመቅሰም ያግዛል" ብለዋል፡፡

 የጋራ ፎረሙ ወንጀለኞችን ወደ ህግ የማቅረቡ ተግባር እንዲጠናከር ፣ ለችግሮች የመፍትሔ አማራጮችን ቀድሞ ማስቀመጥ፣ ብሔራዊ በዓላትን በጋራ በማክበር የህዝቦችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ማጠናከር ላይ አተኩሮ እንደሚሰራ አቅጣጫ አስቀምጧል።

 በውይይቱ ላይ የተሳተፈው የኦሮሚያ ክልልም የፎረሙ አባል በመሆን በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

 በውይይቱ ላይ የክልልና የወረዳ አፈ ጉባኤዎች፣ የክላስተር የፎረም አስተባባሪዎች አንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዋል ፡፡

 

 

 

 

Published in ፖለቲካ

ጅግጅጋ መስከርም 23/2010 በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ኤረር ወንዝ ላይ የተገነባው ድልድይ ግንባታ ተጠናቆ በክልሉ ርዕሰ መስተዳር ተመረቀ፡፡

 ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንዳሉት በክልሉ የሚገኙ ዞኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎችን እርስ በርስ በመንገድ ለማስተሳሰር የክልሉ መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው፡፡

 በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በዋቢ ሸበሌ ወንጌይ፣ ጌልዶህ፣ ሶራ እንዲሁም በሙላ፣ ቆራም፣ ደገህመደውና ቀብሪደሀር ወረዳዎች ድልድዮች በመገንባታቸው ሕብረተሰቡን በትራንስፖርት አገልግሎት ማስተሳሰር ተችሏል፡፡