ENA


በዳንግላ ወረዳ እንስሳትን አደልበው የሸጡ አርሶ አደሮች 9 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ትርፍ አገኙ።

  ባህር ዳር የካቲት 1/2005 በአዊ ዞን ዳንግላ ወረዳ በእንስሳት ማደለብ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ለአካባቢው ገበያ ካቀረቧቸዉ እንስሳት ከ9ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማግኘታቸውን የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ። አርሶ አደሮቹ ትርፉን ያገኙት ከመደበኛው የእርሻ ስራቸው ጎን ለጎን 3ሺህ 500 የዳልጋ ከብቶችንና 4ሺህ 370 በግና ፍየሎችን በአግባቡ አድልበው ለገበያ በማቅረባቸዉ ። የጽህፈት ቤቱ የእንስሳት ሃብት ልማት ጤና ጥበቃ የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ስሜነህ ነጋሽ ትርፉን ያገኙትም በልማቱ የተሳተፉ 2ሺህ 900 ወንድና ሴት አርሶ አደሮች ናቸዉ ። ተሳታፊዎቹ በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ካደለቡት አንድ በሬ በአማካይ ሁለት ሺህ 500 ብር፣ከአንድ በግ ወይም ፍየል ደግሞ ከ250 እስከ 300 መቶ ብር ድረስ ማትረፋቸውን ገልፀዋል። በወረዳው እስከዚህ ዓመት መጨረሻ የተሻሻሉ አሰራሮችንና ተሞክሮዎችን በማስፋፋት 10 ሺህ 300 የዳልጋ ከብትና 18 ሺህ በግና ፍየሎችን አድልበው ለገበያ ለማቅረብ እየሰሩ መሆናቸዉን አብራርተዋል። ከተሳታፊዎቹ መካከልም የባቻና ግራርጌ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ አዲሱ ሙሉና አቶ ቻላቸው አስረስ በበኩላቸው አድልበው ከሸጧቸው አምስት በሬዎችና አስር በግና ፍየሎች 14 ሺህ 500 ብር ትርፍ በማግኘት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።
 
 
 
 
  Leave Your Comments Here  
Name:  
Email:  
Comment: