ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የልዑካን ቡድን ተቀብለው አነጋገሩ
አዲስ አበባ, ነሐሴ 28 ቀን 2002 (አዲስ አበባ) - ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ በአሜሪካ ሉዚያና ከተማ ሴናተር የተመራውን የልዑካን ቡድን ማምሻውን በብሔራዊ በተመንግስት ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

ሴናተር ሜሪላንድ በእሳቸው የተመራው የልዑካን ቡድን በሦስት ቀን ቆይታው የተለያዩ የመሰረተ ልማትና የንግድ እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውሮ መጎብኘቱንና ማድነቁን ለፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የልዑካን ቡድኑ በሕጻናትና እናቶች ዙሪያ የሚሰሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን እንቅስቃሴ መጎብኘቱንም ገልጸውላቸዋል፡፡

የአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ ለአፍሪካ አርአያ የሚሆን በሕጻናት ዙሪያ የሚሰራ ማዕከል ለማቋቋም እቅድ እንዳለው ሴናተር ሜሪላንድ ለፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ በበኩላቸው የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት ከመንግሥት ለመንግስት በተጨማሪ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን እንደሚያጠናክር ገልጸዋል፡፡

ሪፖ፣ 1፡30፣ኤዲ፣ከ1፡30-1፡40፣ጥ

---END---

Headlines
ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የልዑካን ቡድን ተቀብለው አነጋገሩ
(c) The Ethiopian News Agency