ጎንደር, መጋቢት 6 ቀን 2002 (ጎንደር) - በሰሜን ጎንደር ዞን ጣቁሳ ወረዳ አርሶ አደሮች ለገበያ ካቀረቡት የቅመማ ቅመም ምርት 108 ሚሊዮን ብር ያህል ገቢ ማግኘታቸውን የወረዳው ግብርናና ገጠር ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አብራራው መንገሻ ሰሞኑን እንዳስረዱት አርሶ አደሮቹ ገቢውን ያገኙት በመኽር ወቅት ያለሙትን 89 ሺህ
ኩንታል የቅመማ ቅመም ምርት ለገበያ አቅርበው ነው።
አርሶ አደሮቹ አልምተው ለገበያ ያቀረቡት በርበሬ ፣ነጭና ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭና ጥቁር አዝሙድ እንዲሁም አብሽና ሌሎች
እንደሚገኙበት ገልፀዋል።
ከወረዳው በዚህ ዓመት የተሰበሰበው ምርት ከአምናው በ17 ሺህ 870 ኩንታል ብልጫ እንዳለው አስረድተዋል።
በአምስት የቅመማ ቅመም አብቃይ ቀበሌዎች በተካሄደው ልማት 10 ሺህ አርሶ አደሮች መሳተፋቸውንና ከእነዚህም ውስጥ 330
የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።
በወረዳው ለቅመማ ቅመም ልማት አመቺ የሆነውን ስድስት ሺህ ሄክታር መሬት ሙሉ በሙሉ አልምቶ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ
ለማድረግ መታቀዱን አቶ አብራራው አስታውቀዋል።
ሪፖ፡3፡45 ኤ1፡4፡15-4፡30
---END---