ባህር ዳር, መጋቢት 6 ቀን 2002 (ባህር ዳር) - በምዕራብ ጎጃም ዞን በደንበጫ ወረዳ ባለፈው ግማሽ አመት ከ347 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ መዘጋጀቱን የወረዳው ማስታወቂያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። በጽህፈት ቤቱ የፕሬስ፣ ዜናና ፕሮግራም የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ደረጀ ብርቁ ሰሞኑን እንደገጹት በወረዳው በዓመቱ ከ429 ሺህ 420
ሜትር ኪዩብ በላይ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማዘጋጀት እቅድ ተይዟል ።
ከዚህ ውሰጥ የወረዳው አርሶ አደሮች እስካለፈው ወር ድረስ ከ347 ሺህ ሜትር ኪዩብ የተፈጥሮ ማዳበሪያ እንዳዘጋጁ ገልጸዋል።
የወረዳው አርሶ አደሮች ያዘጋጁት የተፈጥሮ ማዳበሪያ በፋብሪካ ለሚመረት ማደበሪያ ግዥ ይወጣ የነበረውን ከ16 ሚሊዮን ብር
በላይ ለማዳን ማስቻሉን አመልክተዋል።
በወረዳው አርሶ አደሮች ባለፈው ግማሽ አመት የተዘጋጀው የተፈጥሮ ማዳበሪያ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት በ210 ሺህ 500
ሜትር ኪዩብ ያህል ብልጫ እንዳለው አቶ ደረጀ አስገንዝበዋል።
በዕቅዱ መሰረት በአመቱ የሚዘጋጀው የተፈጥሮ ማዳበሪያ ከ21 ሺህ 400 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
ሪፖ/ኤዲ/ 3.00-3.10 ጠሰድ=0.10 ጥ/መካ/
---END---