ደብረ ብርሐን, መጋቢት 6 ቀን 2002 (ደብረ ብረሃን) - በሰሜን ሸዋ ዞን ለሚገኙ የወጣቶች ሊግ ፣ፌዴሬሽንና የማህበራት አመራር አባላት የምርጫው ስነ ምግባር ሕግ ስልጠና መሰጠቱን የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አስታወቀ ፡፡
የዞኑ ብአዴን ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ እሽቴ አስፋው እንደገለፁት ስልጠናው ትናንት የተሰጠው በዞኑና በየወረዳው ለተደራጁ የአመራር አባላት ነው፡፡
ስልጠናው ወጣቶች የምርጫውን ስነ ምግባር ህግ ተገንዝበው ምርጫው ሰላማዊ ፣ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ እንዲሆን የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ነው፡፡
እንዲሁም የተሟላ ግንዛቤ በመያዝ በፖለቲካ መስክ ያላቸውን ተሳትፎ በተግባር እንዲያረጋግጡ የሚረዳ መሆኑን ገልጿል፡፡
የሰልጠናው ተሳታፊዎች ሕጉን በየደረጃው ለሚገኙ አባላት ለማሳወቅ በምርጫ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚያበረታታ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
ሪፖ /3፣10/ ኤዲ/ 4.00-4.10 ጠሰድ=0.10 ጥ/መካ/
---END---