በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ 30 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ የተገነቡ የልማት ሥራዎች ተመረቁ
አዲስ አበባ, መጋቢት 5 ቀን 2002 (አዲስ አበባ) - በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ 30 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ የተገነቡ የልማት ሥራዎች ዛሬ ተመረቁ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ ኅብረተሰቡ የሚጠበቅበትን ግብር አጠናቅቆ መክፈል ከቻለ የከተማው አስተዳደር የሚያከናውናቸውን የልማት ሥራዎች በይበልጥ ማስፋፋት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ሥራና ከተማ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ ኃይሌ የልማት ሥራዎቹ ሲመረቁ እንዳስታወቁት የክፍለ ከተማው አስተዳደር በራሱ ወጪ ያከናወናቸው የልማት ሥራዎች 21 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ያህል ወጪ አድርጓል፡፡

ከልማት ሥራዎቹ መካከል የሁለት ባለ አራት ፎቅ ትምህርት ቤቶች ማስፋፊያ ሕንፃዎች ግንባታ ፣አምስት የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎች፣ ሁለት ባለ ሦስት ፎቅ የወጣት ማዕከል ይገኙባቸዋል፡፡

አንድ ዘመናዊ ባለ አራት ፎቅ የሽመና ማዕከልና አንድ ጤና ጣቢያ መገንባታቸውንም ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡

የስድስት ቀበሌዎች ሕዝብ በማስተባበር ደግሞ ከስምንት ነጥብ አንድ ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የአስፋልትና የገረጋንቲ መንገዶች ፣የእግረኛ መሸጋገሪያ ድልድይ ድጋፍና የውሃ ማስወገጃ ተሰርተዋል፡፡

ምረቃ ከተደረገላቸው ሌላ የስምንት ባለአራት ፎቅ የጤና ጣቢያዎች፣ የሰባት ባለ አራት ፎቅ ትምህርት ቤት ግንባታዎች እንዲሁም የአራት ባለሦስት ፎቅ የወጣት ማዕከሎችና ሌሎች የልማት ሥራዎች ግንባታ በመፋጠን ላይ እንደሚገኝ አቶ ገዛኸኝ ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ በምረቃው ላይ ባሰሙት ንግግር የከተማዋ አስተዳደር ከ2001 ጀምሮ የከተማዋን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

አስተዳደሩ በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ለማሰራር ያቀዳቸው የልማት ሥራዎች ለማሳካት የከተማዋ ነዋሪዎች ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

በመሆኑም የከተማዋ ነዋሪዎች የሚፈለግባቸውን ግብር በመክፈል ከተማዋን ለማልማት የሚካሄደውን ጥረት እንዲያግዙ አሳስበዋል፡፡

ስ 4፡00 ሪ 8፡00 ያ 9፡15 ተ 9፡35 ጠሰድ 5፡35 ጥከ

---END---

Headlines
ወጣቱ በመጪው ምርጫው ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግና አገሩን እንዲያለማ አንድ የቀድሞ ዲፕሎማት አሳሰቡ
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ 30 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ የተገነቡ የልማት ሥራዎች ተመረቁ
የልደታ ክፍለ ከተማ የኅብረተሰብ ክፍሎች ምርጫው ነፃ፣ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒነት እንዲኖረው ይጥራሉ
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የአገሪቱ ሕዝቦች አንድ አካል ሆነው በየዘርፉ ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለመሆን በቅተዋል-ሸህ አህመዲን ሸህ አብዱላሂ
በዓለማችን የረጅም ዕድሜ ባለቤት ናቸው የተባሉ አዛውንት ጆርጂያ ውስጥ ተገኙ
አልማ ዘንድሮ ባደረገው እንቅስቃሴ ከ419 ሚሊዮን ብር በላይ ለመለገስ ቃል ተገባ
በምዕራብ አርሲ ዞን የ219 ጤና ተቋማት ግንባታ በአብዛኛው እየተጠናቀቀ ነው
(c) The Ethiopian News Agency