ደብረ ብረሃን, መጋቢት 4 ቀን 2002 (ደብረ ብረሃን) - ብአዴን የደብረ ብርሀን ዩንቨርሰቲን ጨምሮ በከተማዉ ሶስት ኮሌጆች ለሚገኙ የንቅናቄው አባላት የምርጫዉ ስነ ምግባር ሕግ ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን ብአዴን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ እሸቴ አስፋዉ እንደገለጹት ስልጠናው የተሰጠው በደብረ ብርሀን ዩንቨርስቲ፣ የትምህርትና
ሙያ ማስልጠኛ ፣ የጤና ሳይንስና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ለሚገኙ ከ400 በላይ መምህራንና ሰራተኞች ነዉ፡፡
የስልጠናዉ የተዘጋጀው ምርጫዉ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለዉ እንዲሆን አባላቱ የምርጫ ሥነ ምግባር
ሕጉን ተገንዝበው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ታስቦ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በሥልጠናዉ በምርጫ ሥነ ምግባር ሕግና የምርጫ አፈጻጸም መመሪያዎች ላይ ያተኮረ ገለፃ ተደርጓል ።
ምርጫዉ የተሳካ እንዲሆን የንቅናቄው አባላት የድርሻቸዉን መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል
ብአዴን ምርጫዉ በተሳካ ሁኔታ አንዲካሄድ በዞኑና በወራዳዎች ጭምር ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የጋራ ምክር ቤት መስርቶ
እየሰራ መሆኑን ኃላፊዉ ጨምረዉ ገልጸዋል።
ሪፖ፡5፡00 ኤ1፡6፡20_6፡35
---END---