የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎችና ተወካዮች የመራጮችና እጩዎች ምዝግባ ሂደት ዴሞክራሲያዊ መሆኑን ገለጹ
ባቱ, መጋቢት 5 ቀን 2002 (ባቱ) -

በባቱና ሻሸመኔ ከተሞች በመጪው ግንቦት ወር በሚካሄደው ብሔራዊ ምርጫ የሚወዳደሩ አራት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎችና ተወካዮች የመራጮችና እጩዎች ምዝገባ ሂደት ዴሞክራሲያዊ መሆኑን አስታወቁ ፡፡

የኢዴፓ፣ መኢአድ ፣ ኢራፖና የኦአነግ እጩዎችና ተወካዮች በከተሞቹ በተቋቋሙ የምርጫ ጣቢያዎችና ክልሎች የመራጮችና እጩዎች ምዝገባ ሂደት ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መካሄዱን ገልጸዋል፡፡

በባቱ ከተማ የመኢአድ ተወካይ አቶ ተስፋዩ ግርማ በምርጫ ጣቢያዎችና ክልሎች የመራጮች ሆነ እጩዎች ምዝገባ በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መሆኑን አረጋግጠው፣ ፓርቲው ዓላማና ፕሮግራሙን ለሕዝብ እያስተዋወቀ ነው ብለዋል፡፡

በከተማው ኢዴፓን ወክለው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት የሚወዳዳሩት አቶ ደረሰ ዳባ በበኩላቸው የመራጮችና የእጩዎች

ምዝገባ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መካሄዱን ገልፀው፣ ፓርቲው ጽህፈት ቤት ከፍቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በከተማው ኢራፓን ወክለው ለክልል ምክር ቤት አባልነት የሚወዳደሩት አቶ ዴክሲሶ ገለቶ በበኩላቸው በመራጮችና በእጩዎች ምዝገባ

ሆነ እስካሁን ያለው ሂደት ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

በሻሸመኔ ከተማ ኦአነግን ወክለው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩ አቶ ያዕቆብ በድዬ በበኩላቸው የምዝገባው ሂደት

ምርጫው ሰላማዊ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ እንዲሆን የድርሻቸውን እንደሚወጡ አስታውቀዋል፡፡

የባቱ ምርጫ ክልል አስተባባሪ አቶ ዘለለው ሲሳይ የእጩ ተወዳዳሪዎች ስም ዝርዝር በቅፅ አምስት ተሞልቶ ለእይታ አመቺ በሆነ ስፍራ ተለጥፎ ለሕዝብ ይፋ መደረጉን ለኢዜአ. ገልጸዋል፡፡

ሪፖ4፣45

---END---

Headlines
የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎችና ተወካዮች የመራጮችና እጩዎች ምዝግባ ሂደት ዴሞክራሲያዊ መሆኑን ገለጹ
በአዲስ አበባ ከተማ በመገንባት ላይ ያለው የኦሮሞ ባህል ማዕከል ግንባታ 40 በመቶ ተጠናቀቀ
በአዶላ ሬዴ ወረዳ እንስሳት ያደለቡ 29 ሚሊዮን ብር ገቢ አገኙ
በሐውዜን ወረዳ የተለያዩ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ ነው
በወላይታ የሚገኙ የመስህብ ስፍራዎችን ከ40 ሺህ በላይ ቱሪሰቶች ጎበኙ
በደቡብ ክልል ከ174 ሺህ በላይ ግብር ከፋዬችን የጣት አሻራ ተመዝግበዋል
(c) The Ethiopian News Agency