በሱማሌ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ ለማሰራጨት ዝግጅት እየተደረገ ነው
ጅጀጋ, መጋቢት 4 ቀን 2002 (ጅጀጋ) - በሶማሌ ክልል ለሚካሄደው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ የሚያገለግሉ ቁሳቁስ ለየወረዳው ለማሰራጨት ዝግጅት መደረጉን በምርጫ

ቦርድ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የምርጫ ሰነዶችና ቁሳቁስ በክልሉ ለተወካዬች፣ለክልል፣ለወረዳና ለቀበሌ ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ ይመዝገባል ተብሎ

ለሚጠበቀው ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ህዝብ የሚያገለግሉ መሆኑን የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ መሀሙድ ሀቢብ ገልጸዋል፡፡

በክልሉ በተቋቋሙ የምርጫ ጣቢያዎች ከሚከፋፈሉት የምርጫ ቁሳቁስና ሰነዶች መካከል የመራጮችና የእጩ ተወዳዳሪዎች መመዝገቢያ ቅጾችና የመታወቂያ ካርዶች፣ድምፅ መስጫ ሳጥኖች እንደሚገኙባቸው አመልክተዋል፡፡

ለክልሉ የተመደበውን የምርጫ ቁሳቁስና ሰነዶች ለማሰራጨት ተሽከርካሪዎች ተመድበው እንቅሰቃሴ እየተደረገ መሆኑን

አብራርተዋል ፡፡

ለዚሁ ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ከመጋቢት 10 ቀን እስከመጋቢት 30 የመራጮችና የዕጩ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በየወረዳው የምርጫ ጽሕፈት ቤቶች ለመክፈት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ኃላፊው ጠቁመው፣በየደረጃው ለተመደቡ የምርጫ አስፈጻሚዎች ስለመራጮች ምዝገባ፣ የምርጫ ስነ ምግባር ሕግና በሌሎች ርእሶች ላይ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ህዝቡ በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በየአካባቢው በተቋቋሙ የምርጫ ጣቢያዎች እየቀረበ በመመዝገብ ወኪሎቹን ለመምረጥ እንዲዘጋጅ ሃላፊው አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም በምርጫው በግል የሚወዳደሩና በፖለቲካ ድርጅቶች የሚወከሉ እጩዎች በጊዜ ሠሌዳው ቀርበው እንዲመዘገቡ አስገንዝበዋል፡፡

ሪፖ/ኤዲ/ 5.25-5.34 ጠሰድ=0.15 ጥ/መካ/

---END---

Headlines
በሱማሌ ክልል የምርጫ ቁሳቁስ ለማሰራጨት ዝግጅት እየተደረገ ነው
በአዲስ አበባ አስተዳደር ውጤት ተኮር አሰራር ሂደት /ባላንስድ ስኮር ካርድ/ ጥናት በመጪው መስከረም በሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች ተግባራዊ ይሆናል
(c) The Ethiopian News Agency