መቱ, መጋቢት 4 ቀን 2002 (መቱ) - የዘንድሮዉ ምርጫ ሰላማዊ ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ ሁኔታ እንዲከናወን ለሚካሄደው ዝግጅት መሳካት የበኩላቸዉን ድጋፍ እንደሚሰጡ የመቱ መምህራን ኮሌጅ ተማሪዎች አስታወቁ። የምርጫ ስነ ምግባር ሕጉን ለማስተዋወቅ የተዘጋጀዉ ስልጠና ትናንት ሲጠናቀቅ ተማሪዎቹ እንደገለጹት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች
የስነ ምግባር ሕጉን አክብረው መንቀሳቀስ አለባቸው ብለዋል ።
ምርጫዉ ነጻ፣ ሰላማዊ ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ለተጀመረው እንቅስቃሴ ዳር መድረስ የሚፈለግባቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጠው፣ በምርጫው በንቃት በመሳተፍ የሚበጃቸዉን ለመምረጥ መዘጋጀታቸዉንም አስታውቀዋል።
የዞኑ ኦህዴድ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጌታቸዉ ታምራት በዚሁ ጊዜ ባሰሙት ንግግር ኦህዴድ ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ድርጅቱ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት እንደተዘጋጀ አመልክተዋል።
ተማሪዎቹ ምርጫዉን የተሳካ ለማድረግ ለተጀመረው ጥረት የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ አሳስበው፣ ድርጅቱ እስካሁን በዞኑ ለሚገኙ
ከ120 ሺህ ለሚበልጡ አባላቱ በስነ ምግባር ሕጉ ላይ ስልጠና መስጠቱን ጠቁመዋል።
ለሶስት ቀናት ተካሂዶ ትናንት በተጠናቀቀው ስልጠና ከ1 ሺህ 100 የሚበልጡ የኮሌጁ ተማሪዎች ተካፍለዋል።
ሪፖ/ኤዲ/ 4.45-4.55 ጠሰድ=0.10 ጥ/መካ/
---END---