ኢትዮጵያ ኤች አይ ቪ/ኤድስ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ እያደረገችው ያለው የህክምና አገልግሎት አበረታች ነው፣ የተባበሩት መንግስታት
አዲስ አበባ, ሐምሌ 21 ቀን 2002 (አዲስ አበባ) - በኢትዮጵያ ኤች አይ ቪ/ኤድስ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ እየተሠጠ ያለው የህክምና አገልግሎት እየተሻሻለ መምጣቱን በተባበሩት መንግስታት የኤድስ መካላከል ዋና ጻሃፊ ዋና ዳይሬክተር አስታወቁ፡፡

በተባበሩት መንግስታት ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከል ዋና ዳይሬክተሩ የሆኑት ሜሼል ሲድቢ ዛሬ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ውስጥ በመገኘት የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደማቸው የሚገኙ እናቶችን፣ የህጻናት ማወላጃ ሥፍራዎችንና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

ሚስተር ሚቼል በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት በአፍሪካ ከኤች አይቪ ጋር የሚኖሩ እናቶች ከቫይረሱ ነፃ የሆነ ልጅ እንዲወልዱ እየተደረገ ያለው ህክምና አሰጣጥ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም በተባበሩት መንግስታት በአፍሪካ የጋራ ኤች አይ ቪ/ኤድስ ፕሮግራም ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ በግሎባል ፈንድ በኩል 11 ቢሊዮን ዶላር የተመደበ መሆኑን ጠቁመው ከዚህ ውስጥ 60 በመቶ የሚሆነው የአፍሪካ ድርሻ እንደሆነም አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥትም በጤና በተለይ ደግሞ ኤች አይቪ ኤድስ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

በተለይ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እየተሠጠ ባለው ሁሉን አቀፍ ህከምና አገልግሎት መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡ ይህም በሽታውን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ጥረት ያሳያል ብለዋል፡፡

የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው ሆስፒታሉ አማኑኤል የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት ከተባለ ድርጅት ጋር በመተባበር ኤች አይቪ ኤድስ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ እየሠሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በዚህም በዘንድሮ ዓመት 8 መቶ በላይ ለሚሆኑ እናቶች የህክምና የምክር አገልግሎትሩ እየተደረገላቸው እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

ዶክተር ሊያ እንዳሉት በሆስፒታሉ ክትትል ከሚደረግላቸው እናቶች የሚወለዱ ህጻናት 99 በመቶ የሚሆኑት ከቫይረሱ ነጻ ሆነው እንደሚወለዱ ጠቁመዋል፡፡

ስ8.30መ11.45ያ12፡30---END--

---END---

Headlines
ኢትዮጵያ ኤች አይ ቪ/ኤድስ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ እያደረገችው ያለው የህክምና አገልግሎት አበረታች ነው፣ የተባበሩት መንግስታት
በደቡብ ጎንደር ከ26 ሺህ 531 ሄክታር የሚበልጥ መሬት በሩዝ ሰብል እየለማ
በሴቶች ዙሪያ ያሉ ችግሮች በራሳቸው ጥረት ሊፈቱ ይገባል ተባለ
በፊልቱ ወረዳ የተገነቡ የመጠጥ ውሀ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ጀመሩ
በአሳ ማምረት ስራ ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ከ68 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ አገኙ
ከጋምቤላ ክልል ከ45 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ገቢ ተሰበሰበ
(c) The Ethiopian News Agency