አዲስ አበባ, ሐምሌ 21 ቀን 2002 (አዲስ አበባ) - የተወካዮችና የፌዴሬሽን መክር ቤት አፈ ጉባኤዎች በጄቬቭና በኔዘር ላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንንና ትውልድ ኢትዮጵያውያንን አነጋገሩ፡፡የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ደግፌ ቡላ ከሃምሌ 12 እስከ 15 ባሉት ቀናት በተካሄደው 3ኛው የዓለም ፓርላማዎች ህብረት አፈ ጉባኤዎች ኮንፈረነስ ላይ ተካፍለዋል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጸው ሁለቱ አፈ ጉባኤዎች ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በመልካም አስተዳደር፣ በዴሞክራሲና በመሰረተ ልማት ማስፋፋት ረገድ በፈጣን የለውጥ ጎዳና ላይ እንደምትገኝ ለኢትዮጵያውያኑ ገልጸዋል፡፡
ከተሳታፊዎቹ ለተነሱ ወቅታዊ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አሁን በአገሪቱ ውስጥ ያለውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሃብታቸውን በአገራቸው ልማት ላይ እንዲያውሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
---END---