አዲስ አበባ, ሐምሌ 21 ቀን 2002 (አዲስ አበባ) - በመላው አገሪቱ ተግባራዊ የተደረገው የትምህርት ልማት ፓኬጅ ውጤት እያስመዘገበ መምጣቱን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፉአድ ኢብራሒም ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በተከፈተው 19ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ እንደገለጹት የትምህርት ልማት ፓኬጅ ውጤታማና ሁሉንም ያሳተፈ ነበር፡፡
መምህራን፣ተማሪዎች፣ ወላጆችና ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት በ2002 የትምህርት ዘመን ለትምህርት ልማት ፓኬጁ ስኬት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡
መንግስት በአሁኑ ወቅት ትምህርት የልማት ዋና መሳሪያ መሆኑን በማመን ክህሎቱ የተስተካከለና እውቀቱ የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር ጠንክሮ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ከፍያለው አዘዘ በዚሁ ወቅት እንዳሉት በአሁኑ ወቅት መንግስት ትምህርትን ለሁሉም ለማዳረስ ከሰራቸው በርካታ ስራዎች በተጨማሪ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅም ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው፡፡
በመሆኑም የትህርት ጥራት ፓኬጁ የሁሉንም ድጋፍ የሚጠይቅ በመሆኑ በ2003 የትምህርት ዘመን ለየት ያለ ትኩረት እንዲሰጠው ጉባኤው ቦሶስት ቀን ቆይታው ሊመክር እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲላሞ ኦቶሬ በበኩላቸው ቢሮው በተለይም መሰረታዊ የሆነውን የትምህርት ጥራት ችግሮችን በመቅረፍና በዘርፉ ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል መሰረታዊ የአሰራር ሒደት ለውጥ ተግባራዊ አድርጓል፡፡
በተጨማሪም በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት ተቋማት አመራርና አደረጃጀት የማሟላትና የማብቃት ስራም የተሰራ ሲሆን የትምህርት ስራውን ውጤታማ ከማድረግ አኳያም ግንባር ቀደም የትምህርት ልማት ሰራዊት ለመፍጠር ተችሏል ብለዋል፡፡
ቢሮው በዚሁ የትምህርት ዘመን የሶስት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና አንድ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምርጥ ተሞክሮዎችን በመለየትና በመቀመር ተሞክሮዎችን እያስፋፋ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
በዚሁ ጉባኤ መክፈቻ ላይ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፉአድ ኢብራሒም ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች ያዘጋጁትን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዓውደ ርዕይ መርቀው ከፍተዋል፡፡
ስ2፡30ሪ7፡00ያ 7፡40 ኤ፡7፡49 ጠሰድ 5፡29 ጥከ
---END---