የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አስረኛ መደበኛ ጉባኤ ለ2003 ከ607ሚሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ
አሶሳ, ሐምሌ 21 ቀን 2002 (አሶሳ) - የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አስረኛ መደበኛ ጉባኤ የክልሉን የ2003 በጀት ከ607ነጥብ9 ሚሊዮን ብር በላይ በማጽደቅ ትናንት ተጠናቀቀ፡፡

ለሶስት ተከታታይ ቀናት በተካሄደዉ የክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ መዝጊያ ላይ የስራ ዘመናቸውን ላጠናቀቁ 99 የምክር ቤት አባላት የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል ።

የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አቶ ሰይፈዲን ሀሮን በጉባኤዉ ላይ እንደገለጹት ለበጀት ዓመቱ ለመደበኛና ካፒታል ከፀደቀው በጀት ውስጥ ከ358ነጥብ5ሚሊዮን ብር በላይ ለወረዳዎች የተመደበ ሲሆን ቀሪው ለክልል ቢሮዎችና ለመጠባበቂያ የሚዉል ነዉ ፡፡

ከጠቅላላው በጀት ከ462ነጥብ9ሚሊዮን ብር በላይ ከፌደራል መንግስት ድጎማ ፣150ሚሊዮን ብር ከክልሉ ከሚሰበሰብ ገቢ የሚገኝ ሲሆን ቀሪው ደግሞ ከውጪ እርዳታ የሚሸፈን መሆኑን አስታዉቀዋል ፡፡

ምክር ቤቱ ያፀደቀው በጀት ከ2002 ዓመት በጀት ጋር ሲነጻጸር በ145ነጥብ7ሚሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው አፈ-ጉባኤው አመልክተዋል፡፡

ጉባኤዉ በተጨማሪ የ33 የጠቅላይ ፣የከፍተኛና የወረዳ ፍርድ ቤቶችን ዳኞች ሹመት ያጸደቀ ሲሆን የስራ ዘመናቸውን ላጠናቀቁ 99 የምክር ቤት አባላት ምስክር ወረቀት ተሰጥቷል ፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አህመድ ናስር በጉባኤው ማጠቃለያ እንዳሉት የምክር ቤቱ አባላት በስራ ዘመናቸው ህብረተሰቡ የጣለባቸውን ሃላፊነት ለመወጣት ላሳዩት ያላሰለሰ ጥረት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በቀጣይም ምክር ቤቱ ለክልሉ ህዝብ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ለሚያደርገው የልማት፣ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ግንባታ እንቅስቃሴ በያሉበት የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል ፡፡

ሪፖ 2፡30 2ኤዲ ከ2፡30 - 2፡45 ጠሰድ = 00፡15 ጥአጥ

---END---

Headlines
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አስረኛ መደበኛ ጉባኤ ለ2003 ከ607ሚሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ
በጉጂ ዞን የዳማ ወረዳ አርሶ አደሮች 440 ኩንታል የአፕል ምርት ለገበያ አቀረቡ
ሲዳ የአማራ ገጠር ልማት ፕሮግራም በደቡብ ወሎ ዞን ሲያካሄድ የቆየዉን ፕሮጀክት አጠናቀቀ
በአማራ ክልል ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ጀመሩ
(c) The Ethiopian News Agency