ብአዴን በትግራይ ክልል በቆላ ተንቤን ወረዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በማስገንባት ላይ ነው
አክሱም, የካቲት 19 ቀን 2002 (አክሱም) - የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን/ የትጥቅ ትግል በጀመረበት በትግራይ ማእከላዊ ዞን በቆላ ተንቤን ወረዳ በሁለት ሚሊዮን ብር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያስገነባ መሆኑን የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈቱ ቤት ኃላፊ አቶ በሪሁ ኪዳነ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት ንቅናቄው በወረዳው ጉያ ቀበሌ በመገንባት ላይ ያለው ትምህርት ቤት በአሁኑ ወቅት 80 ከመቶ ተጠናቋል፡፡

ትምህርት ቤቱ የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መፃህፍትና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ክፍሎች እንዳሉት ገልጠው በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ተጠናቆ አገልግሎት ሲጀምር በሁለት ፈረቃ አንድ ሺህ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተናገድ እንደሚችል አስታውቀዋል፡፡

በሌላ በኩል የወረዳው መስተዳድር ለብአዴን ያለውን ፍቅርና አክብሮት ለመግለጽ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ ተገንብቶ ሰሞኑን አገልግሎት መስጠት የጀመረውን ትምህርት ቤት የብአዴን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተብሎ እንዲጠራ መሰየሙን ገልፀዋል፡፡

አገልግሎት የጀመረው አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 300 ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር የሚችል ነው፡፡

ሪፖ፡ 5፡05 ኤ1፡5፡30-5፡45 6፣00---END---

Headlines
መንግሥት በሚከተለው ትክክለኛ የትምህርት ፖሊሲ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሁለንተናዊ ለውጥ አምጥቷል
ብአዴን በትግራይ ክልል በቆላ ተንቤን ወረዳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በማስገንባት ላይ ነው
በትግራይ ደቡባዊ ዞን ዘንድሮ በመስኖ ከለማዉ ከ8ሺህ 800 ሄክታር መሬት ላይ ምርት እየተሰበሰበ ነዉ
(c) The Ethiopian News Agency