የኤርትራ መንግስት በሶማሊያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን አሸባሪዎች የማሰልጠንና የማስታጠቅ ሥራውን ቀጥሏል
አዲስ አበባ, የካቲት 2 ቀን 2002 (አዲስ አበባ) - የኤርትራ መንግሥት በሶማሊያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን አሸባሪዎች የማሰልጠንና የማስታጠቅ ሥራውን መቀጠሉን የሶማሊያ የሽግግር መንግስት የመከላከያ ሠራዊት ቃል አቀባይ ገለጹ፡፡

የሽግግር መንግስቱ ቃል ዓቀባይ ኮሎኔል አዳም ካልሞይ ዛሬ በሞቃዲሾ ለጋዜጠኞች ይፋ እንዳደረጉት ኤርትራ 170 ያህል አሸባሪዎችን ኤርትራ ውስጥ አሰልጥኖ ባለፉት ጥቂት ቀናት ኢልሚዓን በምትባል ለሞቃዲሾ ቅርበት ባላት ወደብ ለአልሸባብ ሰራዊት አስረክቧቸዋል፡፡

የኤርትራ መንግሥት ባለፉት በርካታ ዓመታት የሶማሊያ አሸባሪዎችን በመርዳት፣ በማሰልጠንና አካባቢውን በማተራመሱ እንዲሁም የጂቡቲን ግዛት በኃይል ወርሮ እንዲወጣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት ወስኖበት ባለማክበሩ ባለፈው ታህሳስ ማዕቀብ እንደተጣለበት የሚታወቅ ነው ሲል የሶማሊያ የሽግግር መንግስት የመከላከያ ሰራዊት ቃልዓቀባይን ኢዜአ ዘግቧል።

---END---

Headlines
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በአፍሪካ የአሜሪካ ወታደራዊ ዕዝ አዛዥን ተቀብለው አነጋገሩ
የኤርትራ መንግስት በሶማሊያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን አሸባሪዎች የማሰልጠንና የማስታጠቅ ሥራውን ቀጥሏል
(c) The Ethiopian News Agency