ሽሬ እንዳስላሴ, የካቲት 2 ቀን 2002 (ሽሬ እንዳስላሴ) - የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት /35ኛ ዓመት የልደት በዓል ምክንያት በማድረግ የሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ነዋሪዎች ከደደቢት በረሀ ለተነሳዉ ችቦ ደማቅ አቀባበል አደረጉ ።የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት በመካሄድ አካሄዱ ።
የትጥቅ ትግሉ ከተጀመረበት ደደቢት በረሃ ጥር 29ቀን 2002 የተነሳዉ የተለኮሰ ችቦ ትናንት ከከተማው ሲደርስ ነዋሪዉ ህዝብ ሻማ በማብራት በደማቅ ሰነስርአት አቀባበል አድርጓል ።
የትጥቅ ትግሉ በተጀመረበት ደደቢት የተለኮሰው ችቦ ና መላውን ትግራይ የሚዞረው የዚሁ ችቦ ዓላማ ለሰላም ለፍትህ ለዴሞክራሲ ለልማትና ለነፃነት ኩብር ህይወታቸውን የሰጡ ሰማእታት ለማስታወስ መሆኑን የከተማዋ የህዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት ሓላፊ አቶ ፀጋይ ገ/ሚካኤል ገልፀዋል።
በተጨማሪ አዲሱ ትውልድ ዋነኛ ጠላት የሆነዉን ድህነትን ታሪክ በማድረግ የሰማእታት አደራ ግቡን እንዲመታ ቃል ኪዳኑን የሚያድስበትን መልእክት ለማስተላለፍ እንደሆነ ሓላፊው አስረድተዋል።
ለ35ዓመታት ትግሉን በመደገፍ ድርጅቱ አሁን ለደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ ካስቻሉት አባቶች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ካህሳይ ገብረ መድህን ለሽሬ እንዳስላሴ ወጣቶች ተወካይ ችቦውን አስረክበዋል ።
በዚህ ጊዜ ባስተላለፉት መልእክት ያለፉት ታጋዮች ህይወታቸዉን በመሰዋት ለዛሬዉ የሰላም የዴሞክራሲና የልማት መድረክ ያበቁን በመሆናቸዉ ወጣቱ ትውልድም በላቡ ልማትን በማፋጠን የኢትዮጵያን ህዳሴ እውን ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል።
የከተማዋ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር ወጣት ጎይቶኦም ታደሰ በበኩሉ የሰማእታትን አደራ በብቃት ለመወጣት የከተማዋ ወጣቶች ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጧል ።
ሪፖ 12፡00 2ኤዲ ከ12፡20 - 12፡40 ጠሰድ = 00፡20 ጥአጥ
---END---