በአማራ ክልል ከ84 ነጥብ 2 በመቶ ላይ መራጮች ተመዘገቡ
ባህር ዳር, የካቲት 2 ቀን 2002 (ባህር ዳር) በመጪዉ ግንቦት በሚካሄደዉ አገራዊና ክልላዊ ምርጫ በአማራ ክልል በመራጭነት ይመዘገባል ተብሎ ከሚጠበቀው ህዝብ ውስጥ እስከ ትላንት ድረስ ከ84 ነጥብ 2 በመቶ በላይ ህዝብ ተመዝግቦ የመራጭነት ካርድ መውሰዱን በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ገረመው ገብረፃድቅ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቁት ለመራጭነት ይመዘገባል ተብሎ ከሚጠበቀው ከ7 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ውስጥ ከ6 ሚሊዮን 613ሺህ በላይ የሚሆነው ተመዝግቦ የመራጭነት ካርዱን በእጁ አስገብቷል ።

በክልሉ በ138 የምርጫ ክልሎች ስር በተቋቋሙ 11ሺህ 225 የምርጫ ጣቢያዎች ቀርበዉ ከተመዘገቡትና የመራጭነት ካርድ ከወሰዱት መካከል ከ3 ነጥብ 2 ሚሊዮን የሚበልጡት ሴቶች መሆናቸውንም አስረድተዋል ።

በሌላ በኩል የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄን /ብአዴንን/ ጨምሮ 15 የፖለቲካ ፓርቲዎች 986 እጩዎችን ለተወካዮችና ለክልል

ምክር ቤቶች ማስመዝገባቸዉን አቶ ገረመዉ አስታዉቀዋል ።

ከእነዚህም መካከል 389 ለተወካዮች ምክር ቤት፣ 597ቱ ደግሞ ለክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩ ሲሆን በተጨማሪ በግል ለመወዳደር 997 ዕጩዎች መመዝገባቸዉን አስታዉቀዋል ።

ሪፖ 10፡00 ከ11፡20 - 11፡35 ጠሰድ = 00፡15 ጥአጥ

---END---

Headlines
በምእራብ ወለጋ ዞን 90 ከመቶ ህዝብ በመራጭነት ተመዝግቧል
ኢትዮጵያ በየዓመቱ ዘጠኝ ሺህ ሴት ምሁራንን ለማስመረቅ መቻሏ መንግሥት የሰጠውን ትኩረት ያሳያል
በአማራ ክልል ከ84 ነጥብ 2 በመቶ ላይ መራጮች ተመዘገቡ
የሰላሌ የወተት አምራቾች የህብረት ሥራ ዩኒየን አባላት ከፍተኛ ገቢ እያገኙ ሕይወታቸው መቀየሩን ተናገሩ
(c) The Ethiopian News Agency