በምእራብ ወለጋ ዞን 90 ከመቶ ህዝብ በመራጭነት ተመዝግቧል
ጊምቢ, የካቲት 2 ቀን 2002 (ጊምቢ) የበሔራዊ ምርጫ ቦርድን አርማ ተጠቀሙ

በምእራብ ወለጋ ዞን በግንቦት ወር ለሚካሄደዉ ሀገር አቀፍ ምርጫ ይሳተፋል ተብሎ ከሚጠበቀዉ ህዝብ 90 ከመቶው መመዝገቡን

የዞኑ ምርጫ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽሕፈት ቤቱ አስተባባሪ አቶ ከበደ በቀለ ዛሬ እንደገለጡት ይመዘገባል ተብሎ ከታቀደዉ 513 ሺህ ያህል ህዝብ መካከል እስካሁን

461 ሺህ ለመራጭነት የሚያበቃ ካርድ ወስዷል ፡፡

በዞኑ በሚገኙ 812 ምርጫ ጣቢያዎች እስካሁን ከተመዘገበው መራጭ መካከል 202 ሺህ 600 ያህሉ ሴቶች መሆናቸዉን አብራርተዋል፡፡

የቀረውን መራጭ በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ለመመዝገብ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡

በሌላ በኩል በዞኑ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክና የኦሮሞ ነፃነት አንድነት ግንባር 52 እጩዎች እንዳስመዘገቡ አስተባባሪው አስታዉቀዋል፡፡

ከተመዘገቡት አጩዎች መካከል 14ቱ ለህዝብ ተወካዬችና 38ቱ ደግሞ ለክልል ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሪፖ 8፡00 2ኤዲ ከ10፡00 - 10፡10 ጠሰድ =00፡10 ጥአጥ

---END---

Headlines
በምእራብ ወለጋ ዞን 90 ከመቶ ህዝብ በመራጭነት ተመዝግቧል
ኢትዮጵያ በየዓመቱ ዘጠኝ ሺህ ሴት ምሁራንን ለማስመረቅ መቻሏ መንግሥት የሰጠውን ትኩረት ያሳያል
በአማራ ክልል ከ84 ነጥብ 2 በመቶ ላይ መራጮች ተመዘገቡ
የሰላሌ የወተት አምራቾች የህብረት ሥራ ዩኒየን አባላት ከፍተኛ ገቢ እያገኙ ሕይወታቸው መቀየሩን ተናገሩ
(c) The Ethiopian News Agency