አሶሳ, የካቲት 2 ቀን 2002 (አሶሳ) በመጪው ግንቦት ለሚካሄደው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እስካሁን ከ210ሺ600 በላይ መራጮች መመዝገቡን በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ በዛብህ ዋቅጋሪ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቁ ከጥር 1እስከ የካቲት 1/2002 ድረስ ባለዉ የአንድወር ጊዜ ዉስጥ ይመዘገባል ተብሎ በእቅድ ከተያዘዉ 290ሺ መራጭ መካከል ከ210ሺ690 በላይ የሚሆነዉ ተመዝግቦ ካርድ ወስዶአል፡፡
በክልሉ በተቋቋሙ 624 ምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ከተመዘገቡት ከእነዚሁ መራጮች መካከል 100ሺ የሚጠጉት ሴቶች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
ቀሪዎቹ መራጮች እስከ የካቲት 10/2002 ድረስ ባለዉ ጊዜ ዉስጥ ይመዘገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክተዋል፡፡
በሌላ በኩልም በምርጫዉ ለመወዳደር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ቤጉህዴፓ/ 108 እጩዎችን ለህዝብ ተወካዮችና ለክልል ምክር ቤት ማስመዝገቡን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪ መላው ኢትዮጵያ ብሄራዊ ንቅናቄ /መኢብን/ ፣መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ ፣የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢዴፓ/መድን እና ቅንጅት 25 እጩዎችን ለለሁለቱም ምክር ቤቶች ማስመዝገባቸዉን አቶ በዛብህ ገልጠዋል ።
እንዲሁም አስር የግል ተወዳዳሪዎች ለህዝብ ተወካዮችና ለክልል ምክር ቤት በእጩነት መመዝገባቸውንም ሃላፊዉ አስታውቀዋል፡፡
ሪፖ6፡00 2ኤዲ ከ9፡00 - 9፡10 ጠሰድ = 00፡10ጥ/አጥ
---END---