የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት ጉባኤ ተጀመረ
ድሬደዋ, የካቲት 2 ቀን 2002 (ድሬዳዋ) - የድሬደዋ አስተዳደር ተቋማዊ ለውጥ ለማስፈን ባለፈው ግማሽ አመት 57 የሥራ ሂደቶች የመሰረታዊ አሰራር ለውጥ የሙከራ

ስራ መጀመራቸውን የአስተዳደሩ ከንቲባ ዛሬ አስታወቁ፡፡

ከንቲባው አቶ አደም ፋራህ ዛሬ ለተጀመረው የአስተዳደሩ ምክር ቤት አምስተኛ መደበኛ ጉባኤ ባቀረቡት የግማሽ

አመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የሥራ ሂደቶቹ ወደሙከራ ትግበራ የገቡት ጥናቱን አጠናቅቀው እንደሆነ ገልጠዋለ፡፡

በተጨማሪም በመጀመሪያው ዙር የመሰረታዊ አሰራር ለውጥ ጥናት ያጠናቀቁ ሰባት የሥራ ሂደቶች የሙከራ ትግበራ ጨርሰው

ወደሙሉ ትግበራ መሸጋገራቸውን አብራርተዋል፡፡

አራተኛው ሀገራዊ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ እንደዲካሄድ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቱን ከንቲባው

አስታውቀዋል፡፡

አስተዳደሩ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል በሚያደርገው ጥረት ከ230 ሺህ በላይ የመማሪያ መጽሕፍትን ለመግዛት ዝግጅት ማድረጉን ገልጠው፣ ይህም በሁሉም ክፍሎች የተማሪና የመጽሐፍት ጥምረትን አንድ ለአንድ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

በአስተዳደሩ ገጠር ቀበሌዎች አምስት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን አስረድተዋል፡፡

እንዲሁም 25 ሺህ ሰዎች የኤች አይቪ የምክርና የደም ምርመራ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

በግማሽ አመቱ ከ3 ሺህ በላይ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች የፀረ ኤች አይቪ መድሀኒት እንዲወስዱ መደረጉንና ከእነዚህም

መካከል 111 ህፃናት መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ጉባኤው በነገው እለት የተለያዩ አዋጆችንና ሹመት በማጽደቅ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት 189 አባላት አሉት ፡፡

ሪፖ 5፣50/ኤዲ/ 7.10-7.20 ጠሰድ=0.10 ጥ/መካ/

---END---

Headlines
የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት ጉባኤ ተጀመረ
ተሸላሚ አርሶ አደሮች የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ጎበኙ
በሜጫ ወረዳ ከ6 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተገነቡ
በጅማ ዞን 10 ሚሊዮን ኩንታል የሚጠጋ ምርት ተገኘ
ከደቡብ ክልል ከ48 ሺህ ኩንታል በላይ ቡና ለማእከላዊ ገበያ ቀረበ
(c) The Ethiopian News Agency