ሽሬ እንዳስላሴ, የካቲት 2 ቀን 2002 (ሽሬ እንዳስላሴ) የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ 35 ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ የትጥቅ ትግሉ የተጀመረበት ደደቢት በረሃትናንት የተለኮሰው ችቦ ወደመላው ትግራይ ክልል የሚያደርገውን ጉዞ ጀመረ ።
የትጥቅ ትግሉ በተጀመረበት ደደቢት ተገኝተው ችቦውን የለኮሱት የክልሉ ሴቶች ጉዳይ ቢሮ ሓላፊ ወይዘሮ ሮማን ገብረ ስላሴና የትጥቅ
ትግሉ ሲጀመር በአካባቢው የነበሩ የ68 ዓመቱ አዛውንት አቶ ካህሳይ ገብረ መድህን ናቸው።
የደደቢት ችቦ በሚል ስያሜ ተለኩሶ ጉዞውን የጀመረው ችቦ ዓላማ ሰላም፣ ዴሞክራሲ፣ ፍትህና ልማት በሀገሪቱ እንዲሰፍን አኩሪ መስዋእትነት የከፈሉትን ሰማእታትና በህይወት ያሉትን ታጋዮች ፅናት አዲሱ ትውልድ ተገንዝቦ የኢትዮጰያን ህዳሴ እውን እንዲያደርግ መልእክት ለማስተላለፍ እንደሆነ የጉዞው አስተባባሪ አቶ ሰለሞን አባዲ ገልፀዋል።
ችቦው መላውን ትግራይ ካዳረሰ በኋላ የካቲት 10 በመቀሌ ከተማ በመድረስ በሰማእታት ሃውልት በክብር እንደሚቀመጥ ተናግረዋል።
በደደቢት በተከናወነው የችቦ መለኮስ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ዋና አስተዳሪ አቶ ሚካኤለ አብርሃ
በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት ለሰላም፣ ለዴሞክራሲና ለልማት ክቡር ህይወታቸውን የከፈሉት ሰማእታት አደራ እንዲሳካ
ድህነትን የማስወገድ የተጀመረው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡
ሪፖ፡ ያ፡ ኤ1፡3፡10-3፡20
---END---