ጎንደር, የካቲት 2 ቀን 2002 (ጎንደር) - ሰሜን ጎንደር ውስጥ ባለፉት ዓመታት የተካሄደው የሰፈራ ፕሮግራም ከ100 ሺህ የሚበልጡ ሰፋሪ አርሶ አደሮችን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ አልፎ ሀብት በማፍራት የተረጋጋ ህይወት እንዲመሩ ማስቻሉ ተገለጸ።
የሰፈራ ፕሮግራሙን ውጤታማነት ለመገምገም ሰሞኑን በጠገዴና በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳዎች ለሁለት ቀናት በተካሄደው የመስክ ጉብኝት
ላይ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አገኘሁ ተሻገር እንደገለጹት በዞኑ አምስት ወረዳዎች በተቋቋሙ 50 የሰፈራ ጣቢያዎች የሰፈሩ አባወራዎችና ቤተሰቦቻቸው የተሻለ ህይወት መምራት ጀምረዋል።
ሰፋሪ አርሶ አደሮቹና ቤተሰቦቻቸው በአጭር ጊዜ ከተረጂነት በመውጣት የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ አልፎ አንዳንዶቹ
እስከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ካፒታል በማፍራት ወደባለሀብትነት መሸጋገራቸውን አስረድተዋል።
የክልሉ ሴቶች ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ዝማም አሰፋ በበኩላቸው የሰፈራ ፕሮግራሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ መሆኑ መንግስት
የነደፈውን ፖሊሲ ትክክለኛነት በተጨባጭ ያረጋገጠ ነው ብለዋል።
አንዳንድ ሰፋሪ አርሶ አደሮች በሰጡት አስተያየት የሰፈራ ፕሮግራሙ ህይወታቸውን ከመታደግ በተጨማሪ የሀብት ባለቤት በመሆን
ኑሮአቸውን በተጨባጭ ለመለወጥ እንዳስቻላቸው ተናግረዋል፡፡
በጉብኝት ፕሮግራሙ ላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች የተገኙ ሲሆ፣ ሰፋሪ ከላኩት ከሰሜንና ደቡብ ወሎ እንዲሁም ከደቡብ
ጎንደርና ከኦሮሚያ ዞን የተውጣጡ አመራሮችም ሰፋሪዎቹ ያሳዩትን ተጨባጭ ለውጥ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ሪፖ፡3፡00 ኤ1፡7፡40-7፡50
---END---