አዲስ አበባ ውሰጥ ፍንዳታ የፈፀሙ ቀንደኛ አሸባሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
አዲስ አበባ, ሐምሌ 5 ቀን 2000 (አዲስ አበባ) - ግንቦት 12 ቀን 2000 ዓ.ም ከአራት ኪሎ ወደ ለገሃር ትጓዝ በነበረች ሚኒባስ ታክሲ ላይ የቦንብ ፍንዳታ የፈፀሙ አሸባሪዎች ማንነት መታወቁን እና ሚያዚያ 6 ቀን 2000 ዓ.ም በሁለት የኖክ ነዳጅ ማደያዎች ላይ የደረሰ ፍንዳታ ያቀነባበሩትና የመሩት ቀንደኛ አሸባሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የፌደራል ፖሊስ የጋራ ፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ዛሬ አስታወቁ፡፡

የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1- 01449 የሆነች ሚኒባስ ታክሲ ግንቦት 12 ቀን 2000 ዓ ም ከአራት ኪሎ ወደ ለገሃር በመጓዝ ላይ እያለች በግምት ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ10 ሲሆን በካርታ ሥራዎች ድርጅት አካባቢ እንደደረሰች ፍንዳታ ደርሶባት በውስጧ ከነበሩት ተሳፋሪዎች ውስጥ ስድስቱ ሲሞቱ አምስት ሰዎች ቆስለዋል፡፡

የድርጊቱን አፈፃፀም ለማጣራት ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ፍንዳታው የተፈፀመው በሚኒባስ ታክሲዋ ተሳፋሪ መስለው ገብተው በነበሩ የአሸባሪ የኦነግ አባላት በሆኑት ይስሐቅ ጉቴና አንድ ሌላ የግንባሩ አባል መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

የድርጊቱ ዋና ተዋናይ የሆነው ይስሐቅ ጉቴና ግብር አበሩ ሲ4 የተባለውን ፈንጂ ታክሲዋ ውስጥ አጥምደው ለመውረድ ዕቅድ የነበራቸው ቢሆንም የፈንጂው የፍንዳታ ጊዜ አሞላል ላይ በፈጠሩት ስሕተት ከታክሲዋ ከመውረዳቸው በፊት እጃቸው ላይ በመፈንዳቱ ሁለቱም አሸባሪዎች ከሌሎች አራት ንፁሐን ዜጎች ጋር ሕይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡

የአሸባሪው የኦነግ አባል የሆነው ይስሐቅ ጉቴ ወደ ኤርትራ በመሔድ ፈንጂ የማፈንዳት ሥልጠና እንደወሰደ በተደረገው ማጣራት ታውቋል፡፡ ግለሰቡ ለሽብር ሥራው ያመቸው ዘንድ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በቦሌ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 10 የቤት ቁጥር 213 የተመዘገበ ሐሰተኛ መታወቂያ ካርድ ዳንኤል ጃለታ በሚል ስም አጭበርብሮ መውሰዱ ተረጋግጧል፡፡

የዚህ አሸባሪ ግለሰብ ተባባሪ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ስምንት ሰዎችም በሕግ ቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ሌላው ሚያዚያ 6 ቀን 2000 ዓ.ም በአዲስ አበባ መገናኛ ለም ሆቴልና ገርጂ አካባቢ በሁለት የኖክ ነዳጅ ማዳያዎች ላይ ፍንዳታ በመፈፀም ለሰው ሕይወት መጥፋትና ለንብረት መውደም ምክንያት የሆኑት ቀንደኛ አሸባሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

የፍንዳታዎቹ ዋና አቀነባባሪና መሪ የሆነው የአሸባሪው የኦነግ አባል ያዴሳ ሰርቤሳ ቦንሳ እየተባለ የሚጠራ ሲሆን ግለሰቡ ለሽብር ሥራ የሚሰማሩ ሰዎችን በመመልመልና ለሥልጠና ወደ ኤርትራ በመላክ ለሽብር ሥራ የሚሆን ገንዘብ በማዘዋወርና በመሳሰሉት የፀረ ሰላም ተግባራት ላይ በዋነኝት ሲንቀሳቀስ የቆየ መሆኑ በምርመራው ተረጓግጧል፡፡

በሚያዚያ 6 ቀን 2000 ዓ.ም በሁለቱም የነዳጅ ማዳያዎች ላይ የተፈፀሙትን የሽብር ጥቃቶች በዋነኝነት ያስተባበረውና የመራው ይኸው ግለስብ መሆኑም ተረጋግጧል፡፡

ከዚህ አሸባሪ ግለሰብ ጋር በዋና ተባባሪነት በሽብር ተግባሮች የተሳተፈው የአሸባሪ ኦነግ አባል አሰፋ ሞሊሳ እየተባለ የሚጠራው ግለሰብ ሲሆን ግለሰቡ ከኤርትራ የፈንጂ ባለሙያዎች ለሽብር ሥራ ፈንጂ የማፈንዳት ሥልጠና የተሰጠው መሆኑን አስከትሎም ወደ አደስ አበባ በመምጣት ከሌሎች ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ፈንጂ እየሰራ ለሽብር ተግባር ለመለመሉዋቸው ሰዎች ያከፋፍል እንደነበር በምርመራው ታውቋል፡፡

ይህ ግለሰብ በ1998 ዓ.ም አስኮ አካባቢ አዲሱ ገበያ ፅዮን ሆቴል አጠገብ እና መድኃኔዓለም ትምህርት ቤት በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የፍንዳታ ጥቃት ለመፈፀም የሞከረ መሆኑ በምርመራው ታውቋል፡፡

በሚያዚያ 6 ቀን 2000 ዓ.ም በአዲስ ከተማ በሁለት የኖክ ነዳጅ ማዳያዎች ፍንዳታ ላይም በቀጥታ የተሳተፈ መሆኑን ተረጋግጧል፡፡

በነዚህ የሽብር ተግባሮች ላይ ተሳታፊ ከነበሩት ግብረ አበሮቹ መካከል እስካሁን ያልተያዙና በጥብቅ በፖሊስ ተፈላጊ ተጠርጣሪ አሸባሪ ግለሰቦች 1ኛ ሚሊዮን ድሪባ ወይም ሳሙኤል ገዳ፣

2ተኛ አማኑኤል ገመቹ ዱሬሳ እና

3ተኛ ደቻሳ አራርሳ ኢተፋ ሲሆኑ

እነዚህን ፀረ ሰላም ሽብርተኞች አድኖ ለመያዝ በሚደረገው እንቅስቃሴ እንደተለመደው ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጎን በመሰለፍ እገዛውን እንዲያበረክት እያሳሰብን በ0111- 572121፣ 0115-524077 ስልክ ቁጥሮች በመደወል ወይም በነፃ ጥሪ 987 እና 911 በመደወል ወይም በአቅራቢያው ለሚገኝው ፖሊስ ጥቆማ እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡ በቅርቡም የዚህን ጉዳይ ዝርዘር ዘገባ የያዘ ፕሮግራም እንደምናቀርብ እንገልጻለን

የብሄራዊ መረጃና ደህንነትና የፌደራል ፖሊስ የጋራ ፀረ ሽብር ግበረኃይል ግንቦት 17 በተሰጠ መግለጫ እንደተመለከተው ከአራት ኪሎ በመስቀል አደባባይ በኩል ወደ ለጋሃር ትጓዝ በነበረቺው ሚኒባስ ታክሲ ላይ ፈንጂ በማፈንዳት ለስድስት ሰዎች ህይወት ህልፈትና ለሰባት ሰዎች መቁሰል ምከንያት ከሆኑት መካከል የተወሰኑት በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

ሄኖክ ሪ2፡45 ያ 3፡00 ኤ2፡55 የ3፡10 ድሰ25 ጥ ከ

---END---

Headlines
አዲስ አበባ ውሰጥ ፍንዳታ የፈፀሙ ቀንደኛ አሸባሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ
(c) The Ethiopian News Agency
㰊瑨汭㰾潢祤㰾楤⁶瑳汹㵥搢獩汰祡渺湯≥㰾晩慲敭猠捲∽瑨灴⼺洯獹祰楦敬⹳湣焯穡獷⽸湩敤⹸桰≰眠摩桴∽㈳∰栠楥桧㵴㈢〴㸢⼼晩慲敭㰾搯癩㰾戯摯㹹⼼瑨汭>