ከአርሶ አደሩና ከመላዉ ህዝብ ክንድን አስተባብሮ የኢትዮጵያን ህዳሴ እዉን የማድረግ ተጋድሎ ይጠበቃል፡፡ማስታወቂያ ሚኒስቴር
አዲስ አባበ, ጥር 2 ቀን 2000 (አዲስ አበባ) - አርሶ አደሩና መላዉ ህዝብ ክንድን አስተባብሮና እጅ ለእጅ ተያይዞ በጋራ በመስራት በአዲሱ ሚልኒየም የኢትዮጵያን ህዳሴ እዉን የማድረግ ተጋድሎ እንደሚጠበቅ መንግስት አሳሰበ፡፡

የዘንድሮ የአርሶ አደሮች ቀን በብሔራዊ ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝቦች ክልል ርዕሰ መዲና አዋሳ ከተማ ይከበራል፡፡

የማስታወቂያ ሚኒስቴር የመንግስትን አቋም በሚተነትነው የአቋም መግለጫው ዛሬ እንዳሳሰበዉ ይህ በዓል ካለፉት አመታት በተሻለ መልኩ ለአምስተኛ ጊዜ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ይገኛል ተብሎ በሚጠበቅበትና ታሪካዊ የሚሊኒየም በዓል በድምቀት እየተከበረ ባለበት ወቅት መከበሩ በዓሉን ልዩ ያደርገዋል፡፡

በዕለቱ ውጤታማ ለሆኑ አርሶ አደሮች እንዲሁም በግብርና ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሞዴል የማህበረሰብ አባላት፣የወረዳና የቀበሌ አመራሮችና የልማት ሰራተኞች እንዲሸለሙ በመንግስት ተወስኗል፡፡

ይህም ለበአሉ ልዩ ድምቀት ከመስጠቱም በላይ በአገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ መሪ ተወናይ የሆነውን አርሶ አደር ጨምሮ ሌሎች የልማት አርበኞች ወደ ላቀ ልማትና ኢኮኖሚያዊ ውድድር እንደገቡ እንደሚያስችልና የተገኘው ውጤትም ተጠናክሮ እንዲቀጥል እገዛ ያደርጋል ብሏል፡፡

በመሆነም ባለፉት አራት ዓመታት የተመዘገበው ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ዘንድሮም ለአምስተኛ ጊዜ እንዲደገምና የዕድገቱ ተከታታይነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በተለያዩ የልማት መስኮች እየታዩ ያሉት ተጨባጭ ውጤቶችና ለውጦች በቂ ማስረጃዎች እንደሆኑም አመልክቷል፡፡

መንግስት በሰጠው ልዩ ትኩረትና ህብረተሰቡ ባደረገው ያለሰለሰ ጥረት በክልሎች በመስፋፋት ላይ የሚገኙት የህብረት ስራ ዩኔየኖች እንዲሁም የማይክሮ ፋይናስ ተቋማት በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ዕድገት ውስጥ እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡

በተለይ ዩኒየኖች የተለያዩ የግብርና ግብዓቶችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባትና በማከፋፈል እንዲሁም አነስተኛ የብድርና ቁጠባ ተቋማት ለአርሶ አደሩ የገንዘብ አቅርቦት በማመቻቸት ለልማት እንቅስቃሴው ስኬታማነት የተቀናጀ ጥረት በመደረግ ላይ እንደሆነም አስታውቋል፡፡

በ1982 ዓም በአንድ መንግስታዊ ድርጅትና በአንድ የግል ኩባንያ ብቻ ሲካሄድ የነበረው የዘር ማባዛትና ማስራጨት ስራ በአሁኑ ወቅት ከ16 በላይ በሆኑ በዘርፉ በተሰማሩ ድርጅቶች እየተከናወነ እንደሚገኝም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

እንዲሁም መንግስት በነደፈው የገጠር ፖሊሲ አማካኝነት የርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ምርታማነት ለማሳደግ በተተቋቀሙ የግብርናና የቴክኒክ ስልጠና ኮሌጆች ውስጥ እስከ 1999 ዓም ድረስ ባሉት ዓመታት 49ሺህ 435 የግብርና ኮሌጆች ሰልጥነው በየቀበሌው ተሰማርተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም 4ሺህ 435 የግብርና ባለሞያዎች በመስክ ልምምድ ላይ እንደሚገኙና ከዚህ ጎን ለጎን የገበሬውን አቅም ለማጎልበት እስከ 1999 ዓም ድረስ በቀበሌ ደረጃ 7ሺህ 401 የገበሬዎች ማሰልጠኛ ማዕከላት ግንባታና የውስጥ ቁሳቁስ የማሟላት ስራ ተከናውኗል፡፡

በዚህም በ1999ዓም ከውጭ ንግድ አገሪቱ ካገኘችው ገቢ 1ነጥብ 2 ቢለዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ውስጥ 90 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ ከግብርና ምርቶች መገኘቱ የግብርና ምርቶች የዓለምን ገበያ ሰብረው ለመግባታቸው እማኝ ሲሆን የአርሶ አደሩን ጥንካሬና የፖሊሲ ውጤታማነት በግልጽ የሚያሳይ እንደሆነም የማስታወቂያ ሚኒስቴር አመልክቶ ከእንግዲህም ራአያችንን ለማቃረብ ሁሉም ወገን በበለጠ መነሳሳት እንዳለበት አስምሮበታል፡፡

ሪ.5.35 ያ6.04ኤያ/7፣02ጥመ

---END---

Headlines
ከአርሶ አደሩና ከመላዉ ህዝብ ክንድን አስተባብሮ የኢትዮጵያን ህዳሴ እዉን የማድረግ ተጋድሎ ይጠበቃል፡፡ማስታወቂያ ሚኒስቴር
ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስታወቁ
የቻይና መንግስት የልዑካን ቡድን ብሄራዊ ሙዚየምን ጎበኘ
1429ኛው የአሹራ በዓል ጥር 9 ቀን 2000 ዓ.ም በነጃሺ ከተማ ይከበራል
በኢትዮጵያና ሱዳን መንግስታት መካከል የቤንዚን ግዥ ውል ስምምነት ተፈረመ
ሆላንድ የቤት መኪና መገጣጠሚያ ኩባንያ በቅርቡ በቡታጋዝ የሚነዱ መኪናዎች ለገበያ አቀርባለሁ አለ፡፡
በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በድሬደዋ በተመለከቱት የልማት ስራዎች ተደስተናል አሉ
የኤሌክትሪክ ሃይል ሽያጭ ስምምነት ተፈረመ
ጅማ ከተማን ጨምሮ በዞኑ እስካሁን ከ389 ሺህ የሚበልጡ ነዋሪዎች በመራጭነት ተመዘገቡ
መንግስት በሀድያና ከንባታጠምባሮ ዞኖች ለተጀመሩ የልማት ስራዎች መጠናከር አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ አስገነዘቡ
በቤንሻንጉልጉምዝ ክልል ከ219 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ካፒታል ያላቸው ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት ስራ ላይ ተሰማሩ
(c) The Ethiopian News Agency
㰊瑨汭㰾潢祤㰾楤⁶瑳汹㵥搢獩汰祡渺湯≥㰾晩慲敭猠捲∽瑨灴⼺洯獹祰楦敬⹳湣焯穡獷⽸湩敤⹸桰≰眠摩桴∽㈳∰栠楥桧㵴㈢〴㸢⼼晩慲敭㰾搯癩㰾戯摯㹹⼼瑨汭>