ኢትዮጵያ ውስጥ አቅጣጫን የሚጠቁም የመረጃ አገልግሎት ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ, ጳጉሜን 1 ቀን 1999 (አዲስ አበባ) - ኢትዮጵያ ውስጥ ለተጓዦችና ለአገር ጎብኝዎች አቅጣጫዎችን በመጠቆም የመረጃ አገልገሎት የሚሰጥ ''ግሎባል ፖዚሽ ሶሉሽን'' /ጂፒኤስ/ የተባለ አዲስ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊሆን ነው፡፡ 27 ሺህ መንደሮችን፣ ከተሞችንና ወረዳዎችንና ያካተተ መሆኑን የፈጠራው ባለቤት ገለጹ፡፡

ይህንኑ ቴክኖሎጂ በሸራተን አዲስ በተግባር ሲሞከር የቱሪዝምና የባህል ሚኒስተሩ አምባሳደር ሙሐመድ ዲሪር እንደገለጹት የዚህ አይነቱ ዘመናዊ የመረጃ ቴክኖሎጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ተግባራዊ መሆኑለቱሪስቶች ጠቃሚ ነው ፡፡

የመረጃ መሳሪያው በተለይ ለተጓዦችና ለቱሪስቶች ወደሚፈልጉበት ለመሄድና አግልግሎት ለማግኘት ለሚያደርጉት ጥረት ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑን አምባሳደር መሐመድ ጠቁመዋል፡፡

በኢትዮጵያ ብዛት ያላቸው የቱሪስት መስህቦች በተለያዩ ከተሞችና አካባቢዎች ቢገኙም ሃብቶቹ የሚገኙበትን ትክክለኛ ስፍራ በካርታም ሆነ በሌላ መረጃ ለተጓዦች አቅጣጫ የሚያመለክት በቂ መረጃ አለመኖሩን ተናገረዋል፡፡

በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የጂፒኤስ አቅጣጫ ጠቋሚ መሳሪያ ከቱሪስት መስህቦች በተጨማሪ የአገልገሎት መስጫ ተቋማትን አድራሻና አቅጣጫ በማመላከት ረገድ አግር ጎብኚዎች እንዳይቸገሩ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል፡፡

የፈጠራው ባለቤት አቶ አካሉ ዓለሙ እንደጠቆሙት ቴክኖሎጂው ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስና ለመጀመሪያ ጊዜ ተግባር ላይ የዋለ ነው፡፡

መሳሪያው በሳተላይት የሚታገዝና ኢትዮጵያውስጥ የሚገኙ 27 ሺህ መንደሮች ፣ወረዳዎችንና ከተሞችን በጉዞ ወቅት የሚያመላክት መሆኑን ገለጸው አንድ አገልግሎት ፈላጊ ተጓዥ ካለበት ቦታ ሆኖ በቅርብ ርቀት ካለው ከተማ ምንአይነት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችል በቀላሉ ማወቅይቻለዋል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ሥፍራዎችን ጨምሮ የትራንሰፖርት ድርጅቶች፣የነዳጅ ማደያዎች ፣የሆቴሎች፣ የሬስቶራንቶች፣የባንክቤቶች እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን መሳሪያው የሚያቀርብ መሆኑንና ወደፊትም እየተሻሻለ እንደሚሄድ ተናግረዋል፡፡፡

---END---

Headlines
የጣሊያንና የፈረንሳይ ቱሪስች ቡድን በሚሊኒየም በዓል ላይ ለመሳተፍ ወደኢትዮጵያ ይመጣል
የሶማሊያ ሽግግር መንግስት የአገሪቱ ብሔራዊው የእርቅና ሠላም ጉባኤ ያሳለፋቸውን የመፍትሄ ሀሳቦች ተግባራዊ ለማድረግ ቃል ገባ
ኢትዮጵያ ውስጥ አቅጣጫን የሚጠቁም የመረጃ አገልግሎት ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ
በስዊድን የኢትዮጵያ ሚሌኒየም በደማቅ ሥነሥርዓት ተከበረ
ከፊንጫ ጌዶ ገፈርሳ 230 ኪሎ ቮልት የሃይል ማመንጪያ ማሰተላለፊያ ፕሮጀክት ስምምነት ተካሄደ
በሶማሌ ክልል ለተያዘው የበጀት ዓመት ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ተመደበ
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከ640 ኪሎ ሜትር የሚበልጥ መንገድ ስራና ጥገና ተካሄደ
በወሊሶ ወረዳ ከ681 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች ቦታ ተረከቡ
የደቡብ ኮሪያ አለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ ለመጠጥ ወሀ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከ1ነጥብ7ሚሊዮን ዶላር በላይ መደበ
የኢየሩሳሌም ህጻናትና ማህበረሰብ ልማት ድርጅት በ11 ሚሊዮን ብር በድሬደዋ የልማት ስራ ሊያከናውን ነው
በአሶሳ ከተማ በ140 ሚሊዮን ብር ዘመናዊ ስታዲዮም ለመገንባት እንቅስቃሴ ተጀመረ
የአሜሪካ መንግስት አዲስ ውበት ለተባለ አገር በቀል ድርጅት 25 ሺህ ዶላር ርዳታ ሰጠ
በጀጅጋ ከተማ ከ12ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ ሚሊኒዬም የሚል ስያሜ የተሰጠዉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ተጀመረ
በመቀሌ ዪኒቨርስቲ ሚሊንየሙን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ኤግዚቢሽን ተከፈተ
ድርጅቱ አደጋ ለመታደግ የምታገለግል 900ሺህ ዶላር ግምት ያለት ሄሊኮፕተር አስመረቀ
ኮርፖሬሽኑ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን የመደበኛ የሞባይል ስልኮች የኢንተርኔትና የመልቲ ሚዲያ ተጠቃሚ አደረገ
በትግራይ ሰባት ዓመት የሞላቸው ሕፃናት ትምህርት ማግኘት እንዲችሉ እየተመዘገቡ ነው
ዩጂ ዘጠና ዘጠኝ የተባለ የስንዴ ግንድ
በሚሌኒየሙ ዋዜማ ሊከሄዱ የነበሩ ዝግጅቶችየተላለፉት ለህዝቡ ደህንነትና የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ነው
(c) The Ethiopian News Agency