አዲስ አበባ, ጥቅምት 15 ቀን 2000 (አዲስ አበባ) - ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዛሬ ለአንድ የፌዴራል መንግሥት የሥራ ኃላፊ ሹመት ሰጡ፡፡በዚሁ መሠረት ዶክተር መስፍን በላቸው የኢትዮጵያ ኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ማምሻውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አስታውቋል፡፡
ዶክተር መስፍን በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በኢንጂነሪንግ ፋክልቲ በመምህርነትና በተለያየ ኃላፊነት ያገለገሉና ከፍተኛ የሥራ ልምድ ያላቸው ናቸው፡፡
ሥራቸውን ከጥቅምት 16 ቀን 2ሺህ ዓ.ም አንስቶ እንደሚጀምሩም ጽሕፈት ቤቱ ገልጿል፡፡
ሪ12፡00 የ12፡18
---END---