ኤች አር 2003 ለኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባታ የሚፈይደው አንዳችም ጠቀሜታ የለውም፤ በየደራጃውም ሊወገዝ ይገባል
አዲስ አበባ, ጥቅምት 15 ቀን 2000 (አዲስ አበባ) - በቅርቡ ኤች አር 2003 የሚባል መጠሪያ የተሰጠውና ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም በተፃራሪ በቆሙ ኃይሎች ግፊት በአሜሪካ መንግስት ሴኔት እንዲፀድቅ እንቅስቃሴ እየተደረገበት ያለው የህግ ረቂቅ ለኢትዮጵያ የሚፈይደው አንዳች ነገር የለም ሲል የማስታወቂያ ሚኒስቴር ገለጸ።

ሚኒስቴሩ የመንግስትን አቋም በሚተነትነው ሳምንታዊ ጽሁፉ እንዳስታወቀው ከግል ስሜትና ጥቅም በመነጨ የራስን ፍላጎት በሌሎች ላይ ለመጫን በሚመስል መልኩ በአንዳንድ የአሜሪካ ኮንግሬስ አባላት ግፊት ተዘጋጅቶ ለሴኔቱ ውሳኔ የተላለፈው ይህ ህግ በአንድ ሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባትን ከማመልከቱም በላይ የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታን ያላገናዘበና ሚዛናዊነት የጎደለው ነው ብሏል።

ከአሜሪካ ኮንግሬስ አባላት ጎን ተሰልፈው ሕጉ እንዲፀድቅ እየሰሩ ያሉት በሻዕቢያ አስተባባሪነት የሚንቀሳቀሱት ኦነግና ኦብነግ መኖራቸው ለሕጉ መረቀቅ መነሻ ነው የተባለው ምክንያት ምን ያህል የተሳሳተ እንደሆነ እንደሚያመለክትም ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ጠይቀው ከእስር ከተፈቱ በኋላ ወደ አሜሪካ የተጓዙት የቅንጅት አመራር አባላት ለዚህ ሕግ መፅደቅ ደፋ ቀና ሲሉ እንደሚታዩም አመልከቷል፡፡

ዘላቂ እድገትን ለማረጋገጥ የልማት፤ የሰላምና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታው በተፋጠነበትና የኢትዮጵያን ህዳሴ በአዲሱ ሚሌኒየም ለማረጋገጥ ሰፊ ርብርብ በተያዘበት በዚህ ወቅት ይህንን ጥረት ለማደናቀፍ በሚያልሙ ኃይሎች የሚሸረብ ሴራ አልፎ አልፎ መከሰቱ አልቀረም ያለው መግለጫው ይህንን የህግ ረቂቅ የሚያንቀሳቅሱ ኃይሎችና ተከታዮቻቸው እጃቸውን ሊሰበስቡ ይገባል ብሏል።

እንደመግለጫው የኢትዮጵያና የአሜሪካ መንግስታት በበርካታ የጋራ ጉዳዮችና ጥቅሞች ላይ በቅርበት እየሰሩ ሲሆን የሁለትዮሽ ግንኙነቱና ትብብሩም ጠንካራ መሰረት ያለው ነው ። በመሆኑም ኤች አር 2003 የህግ ረቂቅ ያካተታቸው መሰረታዊ ሃሳቦች ከዚህ ጠንካራ ግንኙነት ጋር ፈጽሞ ሊጣጣሙ አይችሉም።

ስለሆነም ረቂቅ ህጉ ለኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባታ ብሎም ለሁለቱ ሀገሮች ህዝቦች ግንኙነትና የጋራ ጥቅም የሚፈይድው አንዳችም ጠቀሜታ እንደሌለው ታውቆ በየደራጃው ከወዲሁ ለወገዝ ይገባል ሲል ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ሪ11፡30 ያ12፡25

---END---

Headlines
ኤች አር 2003 ለኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባታ የሚፈይደው አንዳችም ጠቀሜታ የለውም፤ በየደራጃውም ሊወገዝ ይገባል
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የሶማሊያን የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓሊ መሐመድ ጌዲን አነጋገሩ
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሽብርተኝነት ለሰው ዘር ጠንቅ በመሆኑ ሊወገድ ይገባዋል ሲል ጥሪ አስተላለፈ
የቼክና የስሎቫክ ስድስት አገር አሳሾች በሕይወት መግኘት የሚያስደስት ነው
የቼክ ፕሬዚዳንት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በድጋሚ መመረጣቸውን በማስመልከት የደስታ መግለጫ አስተላለፉ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሹመት ሰጡ
ሰዓሊዋ በኢትዮጵያ ያደረገችው ቆይታ እንዳስደሰታት ገለጸች
ዩኒቪርሲቲው አዲስ ፋኩሊቲዎች ከፈተ
በተለያዩ የዓለም አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከ632 ነጥብ 6 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወደአገር ቤት ልከዋል
በቤተሰብ የውሃ አሰተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ የሚነጋገር ዓለም አቀፍ ጉባኤ አዲስ አበባ ውስጥ ይካሄዳል
ድርጅቱ ሞዴሎችን በመምረጥ የፋሽን ትርዒት ሊያቀርብ ነው
የመድሀኒት አስተዳዳርና ቁጥጥር ባለስልጣን ከአንድ የአሜሪካ ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ
በኦሮሚያ ክልል ባለፈው የምርት ዘመን 152 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ተገንቷል፡፡
ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ባህልና ሐይማኖት በተከተለ ሁኔታ የሚሌኒየም በዓላቸውን እያከበሩ ናቸው የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ
የፍትሕ ሚኒስቴር ተቋማዊ ለውጥ ማምጣቱን አስታወቀ
ቆነጃጅት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ
በልመና የተሠማሩ ሰዎች ወደመኖሪያቸው እንዲመለሱና እንዲቋቋሙ የበኩላቸውን ሚና እንደሚጫወቱ አርቲስቶች ገለጹ
ባለስልጣኑ የአደገኛ መድሀኒቶችና እጾች ህገወጥ ዝውውርና አጠቃቀምን ለመከላከል የአምስት ዓመት እቅድ አዘጋጀ
በትግራይ ክልል ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ 117ሺህ ሕጻናት ትምህርት ጀመሩ
በአርሲ ምርጥ ዘር በማባዛት ስራ የተሰማሩ አርሶ አደሮች እስከ 30 ሺህ ብር ድረስ ገቢ እያገኙ ነው
(c) The Ethiopian News Agency