የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሽብርተኝነት ለሰው ዘር ጠንቅ በመሆኑ ሊወገድ ይገባዋል ሲል ጥሪ አስተላለፈ
አዲስ አበባ, ጥቅምት 15 ቀን 2000 (አዲስ አበባ) - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሽብርተኝነት ለሰው ዘር ጠንቅ በመሆኑ ሊወገድ ይገባዋል ሲል ጥሪ አስተላለፈ፡፡

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንትና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት የተመራው ይኸው ጉባኤ አምስት ቀናት ቆይቶ ዛሬ ከመጠናቀቁ በፊት ጥሪውን ያስተላለፈው ስለዓለም ሰላም ጭምር ባደረገው ውይይት ነው፡፡

ጉባኤው በኤች አይ ቪኤድስ ጥቃት ያለ አሳዳጊና ያለጧሪ የቀሩትንና በበሽታው የተያዙ ወገኖችን ከማፅናናቱ ጎን ለጎን የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ መለገስ የሚቻልበትን ሁኔታ በተመለከተ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በተያያዘም በተለያየ ምክንያት ወላጅ አልባ የሆኑ ሕፃናት የሚረዱበትና፣ ጧሪ ያጡ አረጋዊያን የሚጦሩበት ድርጅት ማቋቋም እንደሚያስፈልግ በስፋት የተወያየው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባዔ በሁሉም አህጉረ ስብከት ድርጅቱ እንዲቋቋምም ወስኗል፡፡

ኢትዮጵያ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ጎራ ተቀላቅላ ከድህነት እንድትላቀቅ ለማስቻል መንግሥት ያወጣውን እቅድ የሚደግፍ መሆኑን የገለጸው የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ወጣቱ ትውልድ የስነ እምዕሮ ብቃቱን አሳድጎ ሥራ ፈጣሪ የሚሆንበትን፣ ባለሀብቶችና ኢንቨስተሮች የጀመሩትን የልማት ሥራ በማስፋፋት ለሰመረ ውጤት ይበቁ ዘንድ የሁሉም ሕብረተሰብ ተሳትፎ ወሳኝነት አለው ብሏል፡፡

ፅንስ ማስወረድ በመላው ዓለም እንደ መብት ተቆጥሮ በስፋት እየተከናወነ ነው ያለው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባዔ ፅንስ ማስወረድ በሃይማኖትና በክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር አግባብ ስላልሆነ ቤተክርስቲያናችን ፈፅማ ታወግዘዋለች ብሏል፡፡

በተለያየ ምክንያት በማረሚያ ቤት ይገኙ የነበሩ የሕግ ታራሚዎችን ለማስለቀቅ በተደረገው እንቅስቃሴ ምሕረት ተደርጎላቸው ከህብረተሰቡ ጋር ለመቀላቀል በመብቃታቸው ቅዱስ ሲኖዶስ አድናቆቱን ገልፆ ይህን እድል ለሰጣቸው ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግሥት ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚሌኒየም ፅህፈት ቤት ባዘጋጀውና ባለፈው ማክሰኞ በተከናወነው ቆም ብለን ድህነትን ለማጥፋት ቃል እንግባ የተሰኘ ፕሮግራም በመላ ሀገሪቱ መከናወኑን አስታውሶ ሁሉም ሕብረተሰብ ድህነትን ታሪክ ለማድረግ መረባረብ ይጠበቅበታል ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በስፋት ሲወያይ ቆይቶ ባለ አሥራ ሁለት ነጥብ ውሳኔ በማስተላለፍ መጠናቀቁን ከመንበረ ፓትርያርክ ኦዲዮ ቪዠዋል ክፍል የደረሰው ዘገባ ያመለክታል፡፡

ሪ 12፡50 የ1፡02

---END---

Headlines
ኤች አር 2003 ለኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባታ የሚፈይደው አንዳችም ጠቀሜታ የለውም፤ በየደራጃውም ሊወገዝ ይገባል
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የሶማሊያን የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓሊ መሐመድ ጌዲን አነጋገሩ
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሽብርተኝነት ለሰው ዘር ጠንቅ በመሆኑ ሊወገድ ይገባዋል ሲል ጥሪ አስተላለፈ
የቼክና የስሎቫክ ስድስት አገር አሳሾች በሕይወት መግኘት የሚያስደስት ነው
የቼክ ፕሬዚዳንት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በድጋሚ መመረጣቸውን በማስመልከት የደስታ መግለጫ አስተላለፉ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሹመት ሰጡ
ሰዓሊዋ በኢትዮጵያ ያደረገችው ቆይታ እንዳስደሰታት ገለጸች
ዩኒቪርሲቲው አዲስ ፋኩሊቲዎች ከፈተ
በተለያዩ የዓለም አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከ632 ነጥብ 6 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወደአገር ቤት ልከዋል
በቤተሰብ የውሃ አሰተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ የሚነጋገር ዓለም አቀፍ ጉባኤ አዲስ አበባ ውስጥ ይካሄዳል
ድርጅቱ ሞዴሎችን በመምረጥ የፋሽን ትርዒት ሊያቀርብ ነው
የመድሀኒት አስተዳዳርና ቁጥጥር ባለስልጣን ከአንድ የአሜሪካ ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ
በኦሮሚያ ክልል ባለፈው የምርት ዘመን 152 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ተገንቷል፡፡
ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ባህልና ሐይማኖት በተከተለ ሁኔታ የሚሌኒየም በዓላቸውን እያከበሩ ናቸው የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ
የፍትሕ ሚኒስቴር ተቋማዊ ለውጥ ማምጣቱን አስታወቀ
ቆነጃጅት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ
በልመና የተሠማሩ ሰዎች ወደመኖሪያቸው እንዲመለሱና እንዲቋቋሙ የበኩላቸውን ሚና እንደሚጫወቱ አርቲስቶች ገለጹ
ባለስልጣኑ የአደገኛ መድሀኒቶችና እጾች ህገወጥ ዝውውርና አጠቃቀምን ለመከላከል የአምስት ዓመት እቅድ አዘጋጀ
በትግራይ ክልል ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ 117ሺህ ሕጻናት ትምህርት ጀመሩ
በአርሲ ምርጥ ዘር በማባዛት ስራ የተሰማሩ አርሶ አደሮች እስከ 30 ሺህ ብር ድረስ ገቢ እያገኙ ነው
(c) The Ethiopian News Agency