ሰዓሊዋ በኢትዮጵያ ያደረገችው ቆይታ እንዳስደሰታት ገለጸች
አዲሰ አበባ, ጥቅምት 15 ቀን 2000 (አዲስ አበባ) - ካለፈው ጥቅምት 9 ቀን ጀምሮ በብሄራዊ ሙዚየም ''ንግስት ሳባ በትናንትና ጥላ ሥር'' የተባሉ የጥበብ ሥራዎቿን ለሀዝብ ያቀረበችው ስዊትዘርላንዳዊት አርቲስት በኢትዮጵያ ያደረገችው ቆይታ ከልብ ያስደሰታት መሆኑን ገለጸች፡፡

ሰዓሊ አልሳባ ጃሚላ ዛሬ በሙዚየሙ አዳራሽ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረገችው ቆይታ እንደተናገረችው በኢትዮጵያ የስዕል ሥራዎቿን ለማቅረብ ስትመጣ የሚሊኒየም በዓል እየተከበረ ስለመሆኑ የምታውቀው ነገር አልነበረም፡፡

ይሁንና የበዓሉን አፍሪካዊ ስሜት ካጤነች በኋላ ሃገሪቱ በአፍሪካና በመንግሥታት አንድነት ላይ የምትጫወተው ሚና ጉልህ መሆኑን ለመረዳት መቻሏን ተናግራለች፡፡

በዚህ ወቅት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣቷ መደሰቷን ገልጻ በስዕል ሥራዎቿ ልታመላክት የፈለገችውን የመንግሥታትና የሀዝቦች አንድነት ጅማሮ በኢትዮጵያ ውስጥ በገሃድ ማየት በመቻሏም ልዩ ስሜት እንዳደረባት ተናግራለች፡፡

ኢትዮጵያን የምታውቃት በቴሌቪዥንና በሌሎች መገናኛ ብዙሃን እንደነበርና አሁን ግን በገሃድ መጥታ ልታያት በመቻሏ ኩራት የተሰማት መሆኑንም አርቲስቷ ገልጻለች፡፡

አርቲስቷ በ30 የተለያዩ ሃገራት ከ130 በላይ ኤግዚቢሽን በማዘጋጀት ስለንግሥተ ሳባ ያዘጋጀቻቸውን የጥበብ ሥራዎች ለህዝብ ማቅረቧን ተናግራ በዚህም የቀድሞዋን አቢሲኒያና የአሁኗን ኢትዮጵያ ማስተዋወቅ መቻሏን ተናግራለች፡፡

ይሀን የስዕል ሥራ በመያዝ በሚቀጥሉት ጊዜያት የትውልድ ሃገሯ ከተማ የሆነችው ጄኔቫን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራትን እንደምታዳርስም አስታውቃለች፡፡

የስዕል ኤግዚቢሽኑ እስከ መጪው ጥቅምት 26 ድረስ ለህዝብ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡

ሪ11፡10 የ1፡33 ጥ ከ

---END---

Headlines
ኤች አር 2003 ለኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባታ የሚፈይደው አንዳችም ጠቀሜታ የለውም፤ በየደራጃውም ሊወገዝ ይገባል
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የሶማሊያን የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓሊ መሐመድ ጌዲን አነጋገሩ
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ሽብርተኝነት ለሰው ዘር ጠንቅ በመሆኑ ሊወገድ ይገባዋል ሲል ጥሪ አስተላለፈ
የቼክና የስሎቫክ ስድስት አገር አሳሾች በሕይወት መግኘት የሚያስደስት ነው
የቼክ ፕሬዚዳንት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በድጋሚ መመረጣቸውን በማስመልከት የደስታ መግለጫ አስተላለፉ
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሹመት ሰጡ
ሰዓሊዋ በኢትዮጵያ ያደረገችው ቆይታ እንዳስደሰታት ገለጸች
ዩኒቪርሲቲው አዲስ ፋኩሊቲዎች ከፈተ
በተለያዩ የዓለም አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከ632 ነጥብ 6 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወደአገር ቤት ልከዋል
በቤተሰብ የውሃ አሰተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ የሚነጋገር ዓለም አቀፍ ጉባኤ አዲስ አበባ ውስጥ ይካሄዳል
ድርጅቱ ሞዴሎችን በመምረጥ የፋሽን ትርዒት ሊያቀርብ ነው
የመድሀኒት አስተዳዳርና ቁጥጥር ባለስልጣን ከአንድ የአሜሪካ ድርጅት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ
በኦሮሚያ ክልል ባለፈው የምርት ዘመን 152 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ተገንቷል፡፡
ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን ባህልና ሐይማኖት በተከተለ ሁኔታ የሚሌኒየም በዓላቸውን እያከበሩ ናቸው የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ
የፍትሕ ሚኒስቴር ተቋማዊ ለውጥ ማምጣቱን አስታወቀ
ቆነጃጅት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኙ
በልመና የተሠማሩ ሰዎች ወደመኖሪያቸው እንዲመለሱና እንዲቋቋሙ የበኩላቸውን ሚና እንደሚጫወቱ አርቲስቶች ገለጹ
ባለስልጣኑ የአደገኛ መድሀኒቶችና እጾች ህገወጥ ዝውውርና አጠቃቀምን ለመከላከል የአምስት ዓመት እቅድ አዘጋጀ
በትግራይ ክልል ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ 117ሺህ ሕጻናት ትምህርት ጀመሩ
በአርሲ ምርጥ ዘር በማባዛት ስራ የተሰማሩ አርሶ አደሮች እስከ 30 ሺህ ብር ድረስ ገቢ እያገኙ ነው
(c) The Ethiopian News Agency